ሎጥ ይኖርባቸው የነበሩትን፥ በሸለቆ የሚገኙትን ከተሞች፥ እግዚአብሔር ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አስታወሰ፤ ስለዚህም ሎጥን ከጥፋት ወደሚድንበት ቦታ መራው።
ዮሐንስ 9:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን እንደማይሰማ የታወቀ ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያመልክና ፈቃዱንም የሚፈጽም ሰው ሲኖር እርሱን እግዚአብሔር ይሰማዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የሚሰማው፣ የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እንጂ፣ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር፥ ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛም እግዚአብሔርን የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እርሱን ይሰማዋል እንጂ ኃጥኣንን እንደማይሰማቸው እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኃጢአተኞችን እንዳይሰማ እናውቃለን። |
ሎጥ ይኖርባቸው የነበሩትን፥ በሸለቆ የሚገኙትን ከተሞች፥ እግዚአብሔር ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አስታወሰ፤ ስለዚህም ሎጥን ከጥፋት ወደሚድንበት ቦታ መራው።
አሁን ግን ሴቲቱን ለባልዋ መልሰህ ስጥ፤ እርሱ ነቢይ ስለ ሆነ እንዳትሞት ይጸልይልሃል፤ እርስዋን መልሰህ ባትሰጥ ግን እንደምትሞት ዕወቅ፤ አንተ ብቻ ሳትሆን ሕዝብህም በሙሉ ታልቃላችሁ።”
ስለዚህ አሁን ሰባት ኰርማዎችንና ሰባት አውራ በጎችን ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ እዚያም ስለ ራሳችሁ ኃጢአት የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ አገልጋዬ ኢዮብ ይጸልይላችኋል፤ እኔም ጸሎቱን ሰምቼ በበደላችሁ መጠን አልቀጣችሁም፤ እናንተ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ትክክል የሆነውን ነገር አልተናገራችሁም።”
ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሕዝቦቹን ለማጥፋት ዐቅዶ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የመረጠው ሙሴ በመካከል በመቆም፥ እንዳያጠፋቸውና ቊጣውንም እንዲመልስ እግዚአብሔርን ለመነ።
“እጆቻችሁን ወደ እኔ ለጸሎት ብትዘረጉ፥ ወደ እናንተ አልመለከትም፤ እጆቻችሁ በደም የተበከሉ ስለ ሆኑ የቱንም ያኽል ልመና ብታበዙ አልሰማችሁም፤
ከዚያ በኋላ ትጸልያላችሁ፤ እኔም ጸሎታችሁን እሰማለሁ፤ የእርዳታ ጩኸት ትጮኻላችሁ፤ እኔም አለሁ እላችኋለሁ፤ እናንተ የጭቈናን ቀንበር ብታስወግዱ፥ የጣት ጥቆማንና የተንኰልን ንግግር ብታቆሙ፥
ስለዚህም እነሆ እኔ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤ ከጥፋቱም ማምለጥ አይችሉም፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት ቢጮኹም እንኳ አልሰማቸውም።
እየጾሙ ቢጸልዩ እንኳ አላዳምጣቸውም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ሆነ የእህል ቊርባን ቢያቀርቡልኝ እንኳ በእነርሱ ደስ አልሰኝም፤ ይልቁንም በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲያልቁ አደርጋለሁ።”
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቆመው ቢማልዱ ለዚህ ሕዝብ ምሕረት አላደርግም፤ ስለዚህ ከፊቴ ወዲያ እንዲሄዱ አድርግ።
እናንተም ተጨንቃችሁ ወደ እግዚአብሔር የምትጮኹበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን እርሱ አይመልስላችሁም፤ ክፉ ሥራ ስለ ሠራችሁ ልመናችሁ አይሰማም።”
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።