9 አንድ ሰው ሕግን ባያከብር ጸሎቱ በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ይሆናል።
9 ሕግን ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።
9 ሕግን ከመስማት ጆሮውን የሚመልስ ጸሎቱ እንኳን ሳይቀር አስጸያፊ ናት።
ኃጢአቴን ሳልናዘዝ በልቤ ሰውሬ ቢሆን ኖሮ፥ እግዚአብሔር ጸሎቴን ባልሰማም ነበር።
እግዚአብሔር ኃጢአተኞች የሚያቀርቡለትን መሥዋዕት ይጸየፋል፤ የልበ ቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሰኘዋል።
በተሟገተ ጊዜ ተረትቶ ይመለስ፤ ጸሎቱ እንኳ እንደ ኃጢአት ይቈጠርበት፤
የድኾችን ጩኸት ለመስማት ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው እርሱም ተቸግሮ በሚጮኽበት ጊዜ የሚረዳው አያገኝም።
እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን እንደማይሰማ የታወቀ ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያመልክና ፈቃዱንም የሚፈጽም ሰው ሲኖር እርሱን እግዚአብሔር ይሰማዋል።
እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን እንዲራቡ አያደርግም፤ ክፉዎች ግን የተመኙትን እንዳያገኙ ያደርጋል።
ዐመፀኞች የሚያቀርቡት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው፤ በተለይም በክፉ አሳብ ተነሣሥተው የሚያቀርቡለት መሥዋዕት የበለጠ አጸያፊ ነው።
እናንተም ሆናችሁ ድርጊታችሁ በእርግጥ ከንቱ ነው፤ እናንተን ማምለክ የሚሹም አጸያፊዎች ናቸው።
በሕግ ሽፋን በተቀነባበረ ተንኰል ለተዛባ ፍትሕ ተባባሪ ትሆናለህን?
እየጾሙ ቢጸልዩ እንኳ አላዳምጣቸውም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ሆነ የእህል ቊርባን ቢያቀርቡልኝ እንኳ በእነርሱ ደስ አልሰኝም፤ ይልቁንም በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲያልቁ አደርጋለሁ።”