Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 21:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የድኾችን ጩኸት ለመስማት ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው እርሱም ተቸግሮ በሚጮኽበት ጊዜ የሚረዳው አያገኝም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሰው የድኾችን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን ቢዘጋ፣ እርሱም ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የድሀውን ጩኸት እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጮኻል አይሰማለትምም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ድሃን እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጣራል፥ የሚሰማውም የለም።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 21:13
20 Referencias Cruzadas  

ለድኾች የሚሰጥ ከቶ አይቸገርም፤ ድኾችን ላለማየት ዐይኖቹን የጨፈነ ግን በሰዎች ዘንድ የተረገመ ይሆናል።


“የሰዎችን በደል ይቅር ብትሉላቸው፥ እናንተንም የሰማዩ አባታችሁ ይቅር ይልላችኋል።


በዚያን ጊዜ እኔን ጥበብን ትጣራላችሁ፤ እኔ ግን አልመልስላችሁም፤ በየቦታውም ትፈልጉኛላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙኝም።


በሌሎች ላይ በምትፈርዱበት ፍርድ፥ በእናንተም ላይ ይፈረድባችኋል፤ እንዲሁም በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።


እነርሱ እንደ እባብ መርዘኞች ናቸው፤ እንደ ደንቆሮ እፉኝትም ጆሮአቸውን ይደፍናሉ።


የሚረዳቸውን በመፈለግ ይጮኻሉ፤ ነገር ግን ማንም አያድናቸውም፤ እግዚአብሔርንም ይጠሩታል፤ እርሱ ግን አይመልስላቸውም።


በዚህ ጊዜ እነርሱ በታላቅ ድምፅ ጮኹ፤ ጆሮአቸውንም ደፍነው በአንድነት ወደ እርሱ ሮጡ።


ለብሼው የነበረውንም ልብስ በማውለቅ አራግፌ “ከእናንተ መካከል ማንም ሰው የገባውን የተስፋ ቃል ቢያፈርስ እግዚአብሔር እንደዚህ ያድርገው፤ ቤት ንብረቱንም ወስዶ ባዶ እጁን ያስቀረው” አልኳቸው። በዚያም የተገኘው ሰው ሁሉ በአንድ ድምፅ “አሜን!” በማለት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ መሪዎቹም የገቡትን ቃል ፈጸሙ።


የቤቱ ጌታ ተነሥቶ በሩን ይዘጋዋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ በሩን በማንኳኳት፥ ‘ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ ማለት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም!’ ሲል ይመልስላችኋል።


ሰው በዚህ ዓለም ሀብት እያለው ችግረኛውን አይቶ ባይራራለት “እግዚአብሔርን እወዳለሁ” ማለት እንዴት ይችላል?


ይህም የሆነው የድኾችን ጩኸት ሰምቼ እታደጋቸውና፥ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውንም ልጆች እረዳቸው ስለ ነበረ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios