ዮሐንስ 11:53 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከዚያ ቀን ጀምሮ ኢየሱስን ለመግደል ተማከሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ ቀን ጀምሮም፣ ሊገድሉት አሤሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ከዚያ ቀን ጀምረው ሊገድሉት ተማከሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያችም ቀን ጀምሮ የካህናት አለቆች ሊገድሉት ተማከሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ከዚያ ቀን ጀምረው ሊገድሉት ተማከሩ። |
እኔም “ማለድ ብላችሁ ለመግባት በማሰብ በዚያ ማደራችሁ ጥቅም የለውም፤ እንዲህ ማድረጋችሁን የምትቀጥሉ ከሆነ በእናንተ ላይ የኀይል እርምጃ ለመውሰድ እገደዳለሁ” ብዬ አስጠነቀቅኋቸው፤ ከዚያን ጊዜም ጀምሮ በሰንበት ቀን መምጣታቸውን አቆሙ።
ከዚህም ጊዜ ጀምሮ እኔ ያሰለፍኳቸው ሰዎች እኩሌቶቹ ሲሠሩ፥ እኩሌቶቹ ጥሩር ለብሰው፥ ጦር ይዘው፥ ጋሻ አንግበው፥ ቀስት ደግነው ዘብ በመቆም እንዲጠብቁ አደረግሁ፤ መሪዎቻችንም ለሕዝቡ ሙሉ ድጋፍ ይሰጡ ነበር፤
ከዚህ በኋላ መኳንንቱ ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው ሞት ይገባዋል፤ በእንደዚህ ያለ አነጋገር እየተናገረ በከተማይቱ የቀሩት ወታደሮች ወኔ እንዳይኖራቸው አድርጎአል፤ በከተማይቱ ሰው ሁሉ ላይ የሚያደርገው ይኸው ነው፤ ሕዝቡን ለመጒዳት እንጂ ለመርዳት የሚፈልግ ሰው አይደለም።”
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ይላቸው ጀመር፦ “ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ አለብኝ፤ እዚያም ከሽማግሌዎች፥ ከካህናት አለቆችና ከሕግ መምህራን መከራ ይደርስብኛል፤ ይገድሉኛል፤ ግን በሦስተኛው ቀን እነሣለሁ።”
የአይሁድ የፋሲካና የቂጣ በዓል ሊከበር ሁለት ቀን ቀርቶት ነበር፤ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ኢየሱስን በተንኰል ይዘው የሚገድሉበትን ዘዴ ይፈልጉ ነበር።
ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን የሸንጎውን አባሎች ሰብስበው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ብዙ ተአምራት ስለሚያደርግ ምን ብናደርግ ይሻላል?