ኤርምያስ 9:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ተገደሉት ሕዝቤ ቀንና ሌሊት አለቅስ ዘንድ፥ ራሴ የውሃ ጒድጓድ፥ ዐይኖቼም የእንባ ምንጭ በሆኑ እንዴት በወደድሁ ነበር! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ታረዱት ወገኖቼ፣ ቀንና ሌሊት አለቅስ ዘንድ፣ ምነው፣ ራሴ የውሃ ምንጭ በሆነ! ምነው ዐይኖቼ የእንባ መጕረፊያ በሆኑልኝ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተወግተው ስለ ሞቱት ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን እንዳለቅስ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ተገደሉ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ለራሴ ውኃን፥ ለዐይኔም የዕንባን ምንጭ ማን በሰጠኝ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ! |
ስለ ያዕዜር እንደማለቅስ ስለ ሲብማ የወይን ሐረጎችም አለቅሳለሁ፤ ስለ ሐሴቦንና ስለ ኤልዓሌ እንባዬ ይረግፋል፤ ሕዝቡ የሚደሰትበት መከር አልተገኘባቸውም፤
አናዳምጥም ብትሉ ግን ስለ ትዕቢታችሁ ተደብቄ አለቅሳለሁ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ ምርኮኞች ሆነው በመወሰዳቸውም ምርር ብዬ አለቅሳለሁ፤ እንባዬም ባለማቋረጥ ይፈስሳል።
ስለዚህ ጉዳይ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብዬ እንድናገር አዘዘኝ። “ሕዝቤ እጅግ ቈስሎአል፤ በብርቱም ተጐድቶአል፤ ስለዚህ ዐይኖቼ ቀንና ሌሊት እንባ ያፈሳሉ፤ ባለማቋረጥም አለቅሳለሁ።
ይህን ሁሉ ከፈጸመች በኋላ እምነት የማይጣልባት የእስራኤል እኅት የሆነችው ይሁዳ፥ እንደገና ወደ እኔ ለመመለስ የምትሞክር መስላ የታየችው ከልብዋ ሳይሆን ከአንገት በላይ ነበር፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
ወይ ሥቃይ! ይህን ሁሉ ሥቃይ እንዴት መታገሥ እችላለሁ! ወይ ልቤ! የልቤ አመታት እንዴት ፈጠነ? የጥሩምባ ድምፅና የጦርነት ድምፅ እየሰማሁ፥ ዝም ብዬ መታገሥ አልችልም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን ትተው ሐሰተኞች አማልክትን ያመልካሉ፤ ታዲያ እኔ የእነርሱን ኃጢአት ይቅር የምለው ለምንድን ነው? እኔ ለሕዝቤ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ሁሉ በመስጠት እንዲጠግቡ አደረግሁ፤ እነርሱ ግን አመንዝሮች ሆኑ፤ ማደሪያቸውም በአመንዝሮች ቤት ሆነ።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “ሊያጠፋችሁ የመጣው ጠላት በድንገት አደጋ ሊጥልባችሁ ስለ ሆነ፥ ማቅ ለብሳችሁ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤ አንድ ልጁ እንደ ሞተበት ሰው ምርር ብላችሁ አልቅሱ፤
ከሕዝብሽ አንዳንዶቹ ገንዘብ ተቀብለው ሰው ይገድላሉ፤ አንዳንዶቹ ለገዛ ወገኖቻቸው ለእስራኤላውያን ሳይቀር በአራጣ ያበድራሉ፤ እነርሱንም በመበዝበዝ ያለ አግባብ ይበለጽጋሉ፤ እኔንም ፈጽሞ ረስተዋል፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።