የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያያይዘው የቅጽር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ።
ኤርምያስ 52:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ ባቢሎናውያን ከተማይቱን ከበው ሳለ ወታደሮቹ በሌሊት አምልጠው ነበር፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ በሚወስደው መንገድ በኩል በማለፍ ሁለቱን ቅጽሮች በሚያገናኘው በቅጽር በር ወጥተው ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከተማዪቱም ቅጥር ተነደለ፤ ሰራዊቱም ሁሉ ኰብልሎ ሄደ። ባቢሎናውያን በከተማዪቱ ዙሪያ ቢኖሩም፣ በንጉሡ የአትክልት ስፍራ አጠገብ በሁለት ቅጥሮች መካከል ባለው በር በሌሊት ከተማዪቱን ጥለው ሸሹ፤ ወደ ዓረባም አመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከተማይቱም ቅጥር ተጣሰ፥ ወታደሮችም ሁሉ ሸሹ፥ በሁለቱም ቅጥሮች መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማይቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ዓረባም በሚወስደው መንገድ ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተማዪቱም ተሰበረች፤ ሰልፈኞችም ሁሉ ሸሹ፤ በሁለቱም ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሥ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማዪቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ በዓረባም መንገድ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተማይቱም ተሰበረች፥ ሰልፈኞችም ሁሉ ሸሹ፥ በሁለቱም ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማይቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ፥ በዓረባም መንገድ ሄዱ። |
የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያያይዘው የቅጽር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ።
“እኔ ትእዛዝ እሰጣለሁ፤ እነርሱም ወደዚህች ከተማ ይመለሳሉ፤ አደጋ ጥለውም በመያዝ ያቃጥሉአታል፤ በይሁዳ የሚገኙ ከተሞችንም ሁሉ ማንም እንደማይኖርበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እነርሱን የሚያስተዳድረው መስፍን ዕቃውን ጠቅልሎ በትከሻው በመሸከም እነርሱ ግድግዳ ነድለው በሚያወጡለት ቀዳዳ ሾልኮ በጨለማ ይሰደዳል፤ ዐይኑንም ስለሚሸፍን ምድሪቱን አያይም።
በተሰደድን በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፥ ዐሥረኛው ወር በገባ በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም አምልጦ የመጣ አንድ ሰው ከተማይቱ በጠላት እጅ መውደቋን ነገረኝ።
“ከስደት የቀሩት ሁሉ ነፋስ የሚነካውን የቅጠል ኮሽታ በሰሙ ቊጥር በድንጋጤ በርግገው እንዲሸሹ አደርጋለሁ፤ በጦርነት ላይ ልክ ጠላት እንደሚያሳድዳቸው ያኽል ሆነው ይሸሻሉ፤ ምንም ዐይነት ጠላት በአጠገባቸው ሳይኖር ተደናቅፈው ይወድቃሉ፤
“እግዚአብሔር ለጠላቶችህ በአንተ ላይ ድልን ይሰጣቸዋል፤ በአንድ በኩል ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለማምለጥ በሰባት አቅጣጫ ትሸሻለህ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የሚደርሰውን ነገር በሚያዩበት ጊዜ በፍርሃት ይሸበራሉ፤