ኤርምያስ 52:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 የከተማይቱም ቅጥር ተጣሰ፥ ወታደሮችም ሁሉ ሸሹ፥ በሁለቱም ቅጥሮች መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማይቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ዓረባም በሚወስደው መንገድ ሄዱ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 የከተማዪቱም ቅጥር ተነደለ፤ ሰራዊቱም ሁሉ ኰብልሎ ሄደ። ባቢሎናውያን በከተማዪቱ ዙሪያ ቢኖሩም፣ በንጉሡ የአትክልት ስፍራ አጠገብ በሁለት ቅጥሮች መካከል ባለው በር በሌሊት ከተማዪቱን ጥለው ሸሹ፤ ወደ ዓረባም አመሩ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ ባቢሎናውያን ከተማይቱን ከበው ሳለ ወታደሮቹ በሌሊት አምልጠው ነበር፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ በሚወስደው መንገድ በኩል በማለፍ ሁለቱን ቅጽሮች በሚያገናኘው በቅጽር በር ወጥተው ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ከተማዪቱም ተሰበረች፤ ሰልፈኞችም ሁሉ ሸሹ፤ በሁለቱም ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሥ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማዪቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ በዓረባም መንገድ ሄዱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ከተማይቱም ተሰበረች፥ ሰልፈኞችም ሁሉ ሸሹ፥ በሁለቱም ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማይቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ፥ በዓረባም መንገድ ሄዱ። Ver Capítulo |