Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 26:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 “ከስደት የቀሩት ሁሉ ነፋስ የሚነካውን የቅጠል ኮሽታ በሰሙ ቊጥር በድንጋጤ በርግገው እንዲሸሹ አደርጋለሁ፤ በጦርነት ላይ ልክ ጠላት እንደሚያሳድዳቸው ያኽል ሆነው ይሸሻሉ፤ ምንም ዐይነት ጠላት በአጠገባቸው ሳይኖር ተደናቅፈው ይወድቃሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 “ ‘ከእናንተ በሕይወት የተረፉትን፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ድንጋጤ እሰድድባቸዋለሁ፤ ነፋስ የሚያንቀሳቅሰው የቅጠል ድምፅ ያስበረግጋቸዋል፤ የሚያሳድዳቸውም ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሮጣሉ፤ ይወድቃሉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ መካከል በተረፉት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እልክባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታስደነብራቸዋለች፤ እነርሱም ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድ​ሮች ሳሉ ከእ​ና​ንተ ተለ​ይ​ተው በቀ​ሩት ላይ በል​ባ​ቸው ድን​ጋ​ጤን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በነ​ፋ​ስም የም​ት​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የቅ​ጠል ድምፅ ታሸ​ብ​ራ​ቸ​ዋ​ለች፤ ከሰ​ይፍ እን​ደ​ሚ​ሸሹ ይሸ​ሻሉ ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 26:36
31 Referencias Cruzadas  

“ለምን ትቃትታለህ” ብለው ቢጠይቁህ “ስለሚመጣው ወሬ ነው” ትላቸዋለህ፤ “በዚያም ወሬ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፤ እጅ ሁሉ ይዝላል፤ ወኔ ሁሉ ይከዳል፤ ጒልበት ሁሉ እንደ ውሃ ይፈስሳል፤ እነሆ እየመጣ ነው፤ በእርግጥ ይፈጸማል” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።


ከጠላት ወታደር የአንድ ሰው ዛቻ ከእናንተ ሺህ ሰዎችን እንዲሸሹ ያደርጋል፤ እናንተን በሙሉ አምስት የጠላት ወታደሮች በተራራ ላይ እንዳለ የሰንደቅ ዓላማ ምሰሶና በኰረብታ ላይ ያለን ምልክት ጥቂቶቻችሁ ብቻ እስክትቀሩ ድረስ ያባርሩአችኋል።


ፊቴን በቊጣ እመልስባችኋለሁ፤ በጠላቶቻችሁም ትሸነፋላችሁ የሚጠሉአችሁም ይገዙአችኋል፤ ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።


ሕዝቤ በፍርሃት በመሞላት ተሰናክለው ይወድቃሉ፤ እንደ መብረቅ በሚያብለጨልጭ፥ ለመግደያ የተዘጋጀውን ሰይፍ፥ በየበራፋቸው አድርጌአለሁ።


የሰው ልጅ ሆይ! በሐዘን ጩኽ፤ ይህ ሰይፍ የተዘጋጀው ሕዝቤንና የእስራኤልን መሪዎች ለማጥፋት ነው። እነርሱም ከቀሩት ሕዝቤ ጋር ይገደላሉ፤ ስለዚህ በሐዘን ደረትህን ምታ።


ረጋ እንዲል፤ እንዳይፈራ፥ በእሳት ተቀጣጥሎ እንደሚነድ እንደ ግንድ ጢስ በሆኑት በሬዚንና በሶርያው በሬማልያ ልጅ ምክንያት እንዳይሸበር ንገረው።


ሶርያ ከእስራኤል መንግሥት ጋር በመተባበር የጦር ቃል ኪዳን መግባትዋን የይሁዳ ንጉሥ በሰማ ጊዜ እርሱና ሕዝቡ ደንግጠው ልባቸው በነፋስ እንደ ተመታ ዛፍ ተናወጠ።


ኃጢአተኞች ማንም ሳያሳድዳቸው ይሸሻሉ፤ ደግ ሰዎች ግን እንደ አንበሳ ደፋሮች ናቸው።


በዚያ አካባቢ የነበሩ ሕዝቦች እግዚአብሔር ባደረገው ነገር እጅግ ተሸብረው ነበር፤ የአሳም ወታደሮች በገራር ዙሪያ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ ደመሰሱ፤ ከተሞቹንም ሁሉ በመዝረፍ ብዙ ምርኮ ወሰዱ፤


እስራኤላውያንም ጎልያድን ባዩ ጊዜ በታላቅ ፍርሀት ሸሹ።


ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ ያሉ የአሞራውያን ነገሥታትና በሜዲትራኒያን ባሕር ዳርቻ ጠረፉን ተከትለው የሚኖሩ የከነዓናውያን ነገሥታት ሁሉ የእስራኤል ሕዝብ እስኪሻገሩ ድረስ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ወንዝ ውሃ እንዳደረቀላቸው በሰሙ ጊዜ፤ በፍርሃት ልባቸው ቀለጠ፤ ከዚያም በኋላ እስራኤላውያንን ለመቋቋም ድፍረት አጡ።


በነዚያ ኮረብታዎች ላይ የሚኖሩ አሞራውያንም መጥተው ተጋጠሙአችሁ፤ ሠራዊታቸውም እንደ ንብ መንጋ ግር ብለው መጥተው እስከ ሆርማ ድረስ አሳደዱአችሁ፤ ኮረብታማ በሆነችው በኤዶም አገርም ድል አደረጉአችሁ።


ያዕቆብና ልጆቹ ያንን ስፍራ ትተው ለመሄድ ተነሡ፤ እግዚአብሔር በዙሪያቸው በነበሩት ሰዎች ላይ ፍርሀትና ድንጋጤ ስላሳደረባቸው ሊያሳድዱአቸው አልደፈሩም።


ምድርንም በምታርስበት ጊዜ ምንም ፍሬ አትሰጥህም፤ በምድር ላይም ስደተኛ ሆነህ ትንከራተታለህ።”


እናንተ በነበራችሁባት ጊዜ በሰንበቶቻችሁ ያላገኘችውን ዕረፍት አሁን ሰው አልባ በሆነችበት ጊዜ ዐረፈች።


የዐይ ሰዎችም ወደ ሠላሳ ስድስት ያኽል ሰዎችን ገደሉባቸው፤ ከከተማይቱ ቅጥር በር ጀምሮ እስከ ሼባሪዎ ቊልቊለት ድረስ እየገደሉ አባረሩአቸው፤ የሕዝቡም ልብ ቀልጦ እንደ ውሃ ፈሰሰ።


ነፋስ እንደሚያረግፈው ቅጠልና እንደ ደረቅ ገለባ ለምን በማስፈራራት ታሳድደኛለህ?


እግዚአብሔር የሕዝቡን ጠላቶች ስለ ሰባበራቸው ከምንጊዜውም ይልቅ በፍርሃት ተጨነቁ፤ እግዚአብሔርም ስለ ጠላቸው ፈጽሞ ያፍራሉ።


መላውን የባቢሎን ሠራዊት ድል ብትነሡ እንኳ ከእነርሱ ተርፈው በድንኳን ያረፉ ቊስለኞች እንደገና በማንሰራራት ተነሥተው ከተማይቱን በእሳት አቃጥለው ያወድሟታል።”


ጀሌዎቻቸው ተሰናክለው አንዱ በአንዱ ላይ ይወድቃሉ፤ እርስ በርሱም አንዱ ሌላውን፥ ‘ከጠላት ሰይፍ አምልጠን ከሀገራችን ሕዝብ መቀላቀል እንድንችል እንፍጠን’ ይለዋል።”


የይሁዳ ሕዝብ ከጭንቀትና ከከባድ የባርነት ሥራ በኋላ ወደ ምርኮ ተወሰዱ፤ አሁን እነርሱ በሕዝቦች መካከል ሲኖሩ ዕረፍት አያገኙም፤ እነርሱ በጭንቀት ውስጥ እያሉ አሳዳጆቻቸው ደረሱባቸው።


የኢየሩሳሌም ክብር ሁሉ ጠፍቶአል፤ መሪዎችዋ መሰማሪያ እንዳጡ ዋልያዎች ናቸው፤ አሳዳጆቻቸው ሲያባርሩአቸው ጒልበታቸው እስኪዝል ድረስ ሸሹ።


አሳዳጆቻችን በሰማይ ከሚበርሩ ንስሮች የፈጠኑ ነበሩ፤ በተራሮች ላይ አሳደዱን፤ በበረሓም ሸመቁብን።


ምነው መዳን ለእስራኤል ከጽዮን በመጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፥ የያዕቆብ ልጆች ደስ ይላቸዋል፤ የእስራኤል ሕዝብ ሐሴት ያደርጋሉ።


የመዘዘውን ሰይፍ እንዲመልስ አድርገኸዋል፤ በጦርነትም አልረዳኸውም።


ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በጎ ነገርን ስለ ጠሉ ጠላት ያሳድዳቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios