ኤርምያስ 51:51 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ስለ ተሰደብን አፈርን፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ባዕዳን ሰዎች ስለ ገቡ ተዋርደን አንገታችንን ደፋን።’ በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ባዕዳን ሰዎች ወደ ተቀደሰው፣ ወደ እግዚአብሔር ቤት ስለ ገቡ፣ እኛ ተሰድበናል፤ ዕፍረትም ፊታችንን ሸፍኗል፤ ውርደትም ተከናንበናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድብን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም በጌታ ቤት ውስጥ ወዳሉት ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ገብተዋልና ውርደት ፊታችንን ሸፍኖታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድባችንን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም ወደ ቤተ መቅደሳችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብተዋልና ውርደት ፊታችንን ከድኖታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድብን ስለ ሰማን አፍረናል፥ ባዕዳን ሰዎችም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገብተዋልና ነውር ፊታችንን ከድኖታል። |
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል እንደገና ምሕረትን ያደርጋል፤ የራሱ ወገኖችም አድርጎ ይመርጣቸዋል፤ እንደገናም በአገራቸው እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል፤ መጻተኞችም እንኳ መጥተው ከእነርሱ ጋር ተስማምተው አብረው ይኖራሉ።
በባሕር አጠገብ ስለሚገኝ ምድረ በዳ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ከደቡብ በኩል የሚመጣው ዐውሎ ነፋስ ሁሉን ነገር ጠራርጎ እንደሚወስድ አስፈሪ ከሆነች ከአንዲት አገር ከባድ ጥፋት ይመጣል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በማንም ያልተደፈርሽ የባቢሎን ከተማ ሆይ! ወርደሽ በዐቧራ ላይ ተቀመጪ፤ ወርደሽ በዙፋን ላይ ሳይሆን፤ በመሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅምጥልና ለስላሳ መባልሽ ይቀራል።
ሀብታሞች ውሃ ለማግኘት ሠራተኞቻቸውን ይልካሉ፤ እነርሱም ወደ ውሃ ጒድጓዶች ይሄዳሉ፤ ነገር ግን ምንም ውሃ ስለማያገኙ፥ ባዶ እንስራ ተሸክመው ይመለሳሉ፤ ተስፋ ቈርጠው ግራ ስለሚጋቡ፥ በሐዘን ራሳቸውን ይሸፍናሉ።
ከአንተ ርቀን ብንሄድም እንኳ አሁን ንስሓ ገብተናል፤ በዕፍረትና በጸጸት ራሳችንን ዝቅ አድርገን ደረታችንን እንመታለን፤ በወጣትነት ዘመናችን ለፈጸምነው ኃጢአት ራሳችንን እንወቅሳለን።’
የኢየሩሳሌም ሕዝብ ጠላቶች ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የሕዝቡን ሀብት ዘረፉ፤ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ እንዳይገቡ የተከለከሉ አሕዛብ እንኳ ቤተ መቅደስዋን ሲወሩ ታዩ።
ጌታ ሆይ! ተመልከት! ከአሁን ቀደም እንደዚህ የጨከንክበት ሕዝብ አለ ወይ? ሴቶች የወለዱአቸውንና ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይብሉን! በጌታ ቤተ መቅደስ ውስጥስ ካህናትና ነቢያት ይገደሉን!
‘ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው አለኝ፤ የክብራችሁ ትምክሕት፥ የዐይናችሁ ተስፋና የልባችሁ ደስታ የሆነውን ቤተ መቅደሴን እንዲያረክሱ እተዋቸዋለሁ፤ በኢየሩሳሌም የቀሩት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በጦርነት ይገደላሉ።
እግዚአብሔርም “ሂዱና ቤተ መቅደሱን አርክሱ! አደባባዩንም በሬሳ የተሞላ አድርጉ!” አላቸው፤ እነርሱም ወጥተው በከተማይቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ገደሉ።
ሠራዊቱም ቤተ መቅደሱንና አካባቢውን ያረክሳሉ፤ የዘወትር መሥዋዕትም እንዳይቀርብ ያደርጋሉ፤ አጸያፊ የሆነ ርኩስ ነገር በማቆም ጥፋትን ያመጣሉ።
የይስሐቅና የልጅ ልጆቹ ከፍተኛ የመስገጃ ቦታዎች ይፈራርሳሉ፤ የእስራኤልም የተቀደሱ ቦታዎች ፈራርሰው ወና ይሆናሉ፤ የኢዮርብዓምን መንግሥት ፈጽሞ አጠፋለሁ።”
ይህ ሁሉ የሚደርስባችሁ የንጉሥ ዖምሪን ሥርዓት ስለ ጠበቃችሁና የንጉሥ አክዓብን አካሄድ ሁሉ ስለ ተከተላችሁ ነው፤ በእነርሱ ባህል ስለ ተመራችሁ አጠፋችኋለሁ፤ የከተማይቱን ነዋሪዎችም የሰው ሁሉ መሳቂያ አደርጋቸዋለሁ፤ በሕዝቤ ላይ የተሰነዘረውን ነቀፋ እንድትሸከሙ አደርጋችኋለሁ።”
ጠላቴም ይህን ሁሉ ያያል፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ይለኝ የነበረው ጠላቴ ኀፍረትን ይከናነባል፤ እኔ የጠላቴን ውድቀት አያለሁ፤ በመንገድ ዳር እንዳለ ጭቃ ሲረገጥም እመለከታለሁ።