አበኔርም፥ ኢዮአብን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ዘለዓለም ስንዋጋ እንኖራለንን? ፍጻሜውስ መራር መሆኑን አትገነዘብምን? ሰዎችህ እኛን ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንዲገቱ ትእዛዝ የማትሰጣቸው እስከ መቼ ነው?”
ኤርምያስ 46:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የግብጽ ከተሞች በሆኑት በሚግዶል፥ በሜምፊስ በጣፍናስ ይህን ቃል ዐውጅ፤ ‘ራሳችሁን ለመከላከል ተዘጋጁ፤ በዙሪያችሁ ያለው ሁሉ በጦርነት ይጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን በግብጽ ተናገር፤ በሚግዶልም አሰማ፤ በሜምፊስና በጣፍናስም እንዲህ ብለህ ዐውጅ፤ ‘በቦታችሁ ቁሙ፤ ተዘጋጁም፤ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰይፍ ይበላቸዋልና።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብጽ አውጁ፥ በሚግዶልም አሰሙ፥ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ እናንተም፦ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና ተነሥ ራስህንም አዘጋጅ በሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶልም አውሩ፤ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፦ ተነሥ ተዘጋጅም በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብጽ ተናገሩ፥ በሚግዶልም አሰሙ፥ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፥ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፦ ተነሥ ተዘጋጅም በሉ። |
አበኔርም፥ ኢዮአብን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ዘለዓለም ስንዋጋ እንኖራለንን? ፍጻሜውስ መራር መሆኑን አትገነዘብምን? ሰዎችህ እኛን ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንዲገቱ ትእዛዝ የማትሰጣቸው እስከ መቼ ነው?”
ለመሥዋዕት የቀረቡ የበግና የፍየል ጠቦቶች በሚሠዉበት ጊዜ ደማቸውና ስባቸው ሰይፉን እንደሚሸፍን የእርሱም ሰይፍ በኤዶማውያን ደምና ስብ ይሸፈናል፤ እግዚአብሔር ይህን መሥዋዕት በቦጽራ ከተማ፥ ይህንንም ታላቅ ዕርድ በኤዶም ምድር ያቀርባል።
በሰሜን ግብጽ ውስጥ ሚግዶል፥ ጣፍናስና ሜምፊስ ተብለው በሚጠሩት ከተሞችና በአገሪቱም ደቡባዊ ክፍል ተበታትነው ስለሚኖሩት እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር ተናገረኝ፤
ይህ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የመረጠው ቀን ነው፤ እርሱ ዛሬ የበቀል እርምጃ ይወስዳል፤ ጠላቶቹንም ይቀጣል። የእርሱም ሰይፍ ብዙዎችን ይበላል፤ በደማቸውም ይለወሳል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ሰሜን የሚገኙ ምርኮኞቹን መሥዋዕት ያደርጋቸዋል።
“የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ ስለ ዐሞናውያንና ስለ ስድባቸው እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውን እንዲህ ብለህ አስታውቃቸው፤ ‘አጥፊ ሰይፍ ተዘጋጅቶአል፤ ለመግደልና ለማውደም እንደ መብረቅም ለማብለጭለጭ ተወልውሎአል!’
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሜምፊስ ያሉትን ጣዖቶችና የሐሰት አማልክት ሁሉ አወድማለሁ፤ በግብጽ ምድር ላይ ገዢ ሆኖ የሚነሣ አይኖርም፤ በሕዝቡም ላይ ፍርሀትን አወርዳለሁ።
እነሆ ከጥፋት ለማምለጥ ሲሸሹ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፊስ ትቀብራቸዋለች፤ ያከማቹት የብር ሀብት ሁሉ ሳማ ለብሶ ይቀራል፤ መኖሪያቸውም እሾኽ ይበቅልበታል።
ነነዌ ሆይ! በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ ይላል የሠራዊት አምላክ፤ ሠረገሎችሽንም አቃጥላለሁ፤ ደቦሎችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል፤ በምድር ላይ በአንቺ ተጠቂ የሚሆን እንዳይኖር አደርጋለሁ፤ የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።