ኤርምያስ 43:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጣፍናስም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጣፍናስም የጌታ ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጣፍናስም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጣፍናስም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ |
“ጥቂት ታላላቅ ድንጋዮች ፈልገህ ካገኘህ በኋላ ከእስራኤል ልጆች ጥቂቱ እያዩህ በከተማይቱ ቤተ መንግሥት መግቢያ ፊት ለፊት ባለው ከሲሚንቶ በተሠራው ወለል ሥር ቅበረው።
በሰሜን ግብጽ ውስጥ ሚግዶል፥ ጣፍናስና ሜምፊስ ተብለው በሚጠሩት ከተሞችና በአገሪቱም ደቡባዊ ክፍል ተበታትነው ስለሚኖሩት እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር ተናገረኝ፤
“የግብጽ ከተሞች በሆኑት በሚግዶል፥ በሜምፊስ በጣፍናስ ይህን ቃል ዐውጅ፤ ‘ራሳችሁን ለመከላከል ተዘጋጁ፤ በዙሪያችሁ ያለው ሁሉ በጦርነት ይጠፋል።
የግብጽን ኀይል በመሰባበር የሚመኩበትን ብርታት በማስወግድበት ጊዜ ጣፍናስ በጨለማ ትጋረዳለች፤ ግብጽ በደመና ትሸፈናለች፤ የከተሞችዋ ኗሪዎችም ተማርከው ይወሰዳሉ።