ኤርምያስ 28:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሜን! እግዚአብሔር እንዳልከው ያድርግ! የቤተ መቅደሱን ዕቃዎች በማምጣትና የተማረኩትን ምርኮኞች በመመለስ እግዚአብሔር አንተ የተናገርከውን ትንቢት ይፈጽም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሜን፤ እግዚአብሔር ያድርገው፤ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ሁሉ፣ ተማርከው የተወሰዱትንም ምርኮኞች ሁሉ ከባቢሎን በመመለስ፣ እግዚአብሔር የተናገርኸውን ቃል ይፈጽም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነቢዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፦ “አሜን፥ ጌታ እንዲህ ያድርግ፤ የጌታን ቤት ዕቃዎችና ምርኮውን ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ ጌታ የተናገርኸውን የትንቢት ቃላት ይፈጽም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፥ “አሜን፥ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግ፤ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ፥ ምርኮውንም ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ እግዚአብሔር የተናገርኸውን ትንቢት ይፈጽም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነቢዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፦ አሜን፥ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግ፥ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ምርኮውንም ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ እግዚአብሔር የተናገርኸውን ትንቢት ይፈጽም። |
ይህም ከሆነ አሁን ያሉባትን በማርና በወተት የበለጸገችውን ለምለም ምድር የቀድሞ አባቶቻቸው እንዲወርሱ ባደረግሁ ጊዜ የሰጠኋቸውን የተስፋ ቃል እፈጽማለሁ።” እኔም “እሺ ጌታ ሆይ!” አልኩ።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ! በእነርሱ ላይ መቅሠፍትን እንድታመጣ ያሳሰብኩህ ጊዜ የለም፤ የመከራ ዘመን እንዲገጥማቸውም አልተመኘሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህንና የተናገርኩትን ሁሉ ታውቃለህ።
ታዲያ የደግ ሥራ ዋጋው ክፉ ነገር ማድረግ ነውን? አንተ በእነርሱ ላይ እንዳትቈጣ እኔ በፊትህ ቆሜ ስለ እነርሱ እንደማለድኩህ አስብ፤ እነርሱ ግን እነሆ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቈፈሩ።
“ሔልዳይ፥ ጦቢያና ይዳዕያ የተባሉት ስደተኞች የሰጡትን ብርና ወርቅ ይዘህ ሳትዘገይ አሁኑኑ ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ሂድ፤ እነዚህ ሁሉ ሰዎች ከባቢሎን የተመለሱ ምርኮኞች ናቸው፤
ይህም ውሃ ወደ ሰውነትሽ ገብቶ ሆድሽን ያሳብጠው፤ ማሕፀንሽንም ያኰማትረው።’ ሴትዮዋም ‘አሜን፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ያድርግብኝ’ ብላ ትመልሳለች።
እንዲህማ ካልሆነ አንተ በመንፈስ እግዚአብሔርን ስታመሰግን፥ አንተ የምትለውን የማያውቅ እንግዳ ሰው ለምስጋና ጸሎትህ “አሜን” ሊል እንዴት ይችላል?
“ለሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ፥ አሜን ከሆነው፥ ታማኝና እውነተኛ ምስክር ከሆነው፥ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ መገኛ ከሆነው የተነገረ ነው፤