ኤልሳዕም ወደ ቤትኤል ለመሄድ ከኢያሪኮ ተነሣ፤ በመንገድ ሳለ ከከተማይቱ በርከት ያሉ ልጆች ወጥተው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ “አንተ ራሰ መላጣ ከዚህ ውጣ!” እያሉ ጮኹበት።
ኤርምያስ 20:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! አታለልከኝ፤ እኔም ተታለልኩ፤ አንተ ከእኔ ትበረታለህ፤ ኀይልህም በእኔ ላይ እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ሰው ሁሉ በየዕለቱ በማሽሟጠጥ ይዘባበትብኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ አታለልኸኝ፤ እኔም ተታለልሁ፤ አንተ ከእኔ እጅግ በረታህ፤ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሙሉ ማላገጫ ሆንሁ፤ ሁሉም ተዘባበቱብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ! አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ፥ ከእኔም በረታህ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳቂያ ሆኛለሁ፥ ሁሉም ያላግጡብኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ! አታለልኸኝ፤ እኔም ተታለልሁ፤ ከእኔም በረታህ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳቂያ ሆኛለሁ፤ ሁሉም ያፌዙብኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ፥ ከእኔም በረታህ አሸነፍህም፥ ቀኑን ሁሉ መሳቂያ ሆኛለሁ፥ ሁሉም ያላግጡብኛል። |
ኤልሳዕም ወደ ቤትኤል ለመሄድ ከኢያሪኮ ተነሣ፤ በመንገድ ሳለ ከከተማይቱ በርከት ያሉ ልጆች ወጥተው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ “አንተ ራሰ መላጣ ከዚህ ውጣ!” እያሉ ጮኹበት።
እግዚአብሔርን ጠርቼው የመለሰልኝ ጊዜ ነበር፤ አሁን እኔ የወዳጆቼ መሳቂያ ሆኛለሁ፤ ስሕተት የሌለብኝ ፍጹሙ እኔ የሰው ሁሉ መሳለቂያ ሆኛለሁ።
እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምን ወለድሽኝ? ዕድል ፈንታዬ ከአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ ጋር መከራከርና መነታረክ ሆኗል፤ እኔ ገንዘብ ለማንም አላበደርኩም ወይም ከማንም አልተበደርኩም፤ ሆኖም ሰው ሁሉ ይረግመኛል።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ! በእነርሱ ላይ መቅሠፍትን እንድታመጣ ያሳሰብኩህ ጊዜ የለም፤ የመከራ ዘመን እንዲገጥማቸውም አልተመኘሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህንና የተናገርኩትን ሁሉ ታውቃለህ።
ነገር ግን “ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አላስታውስም፤ በስሙም አልናገርም” በምልበት ጊዜ፥ ከእርሱ የተሰጠኝ የትንቢት ቃል በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በውስጤ ሰውሬ ልይዘው ብሞክርም፤ አፍኜ ላስቀረው አይቻለኝም።
“እግዚአብሔር በካህኑ በዮዳሄ ቦታ ካህን አድርጎ ሾሞሃል፤ እነሆ የቤተ መቅደሱም የበላይ አለቃ አንተ ነህ፤ ስለዚህም ነቢይ ነኝ እያለ በማስመሰል የሚናገረውን አንዳንድ ዕብድ በአንገት ሰንሰለትና በእግር ግንድ እየጠፈሩ ማሰር የአንተ ተግባር መሆን አለበት፤
ንጉሡም “እኔ እኮ የምፈራው ከእኛ ከድተው ወደ ባቢሎን የገቡትን የአገራችንን ሰዎች ነው፤ ለእነርሱ አሳልፈው የሰጡኝ እንደ ሆነ ያሠቃዩኛል” ሲል መለሰልኝ።
የቅጣት ቀን ደርሶአል፤ እስራኤላውያንም የበቀል ቀን መቃረቡን ይወቁ፤ በእናንተ በደልና ጥላቻ ምክንያት ነቢይን እንደ ሞኝ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረበትን ሰው እንደ ዕብድ ትቈጥሩታላችሁ።
እንዲህም ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፦ “እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህን እንደምታደርግ ገና በአገሬ ሳለሁ ተናግሬ አልነበረምን? ከፊትህ ኰብልዬ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ያቀድኩትም በዚህ ምክንያት ነበር፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ በዘለዓለማዊ ፍቅር የተመላህ፥ ቊጣህን መልሰህ ምሕረት የምታደርግ አምላክ መሆንህን ዐውቅ ነበር።
እኔን ግን እግዚአብሔር በመንፈሱና በኀይሉ ሞልቶኛል፤ የእስራኤል ሕዝብ በደላቸውና ኃጢአታቸው ምን እንደ ሆነ አስታውቃቸው ዘንድ በግልጽ ትክክለኛ ፍርድን ለመስጠት ብርታትን ሰጥቶኛል።
ኤፒኮሮሶችና እስቶይኮች የተባሉ ፈላስፎችም ወደ እርሱ እየመጡ ይከራከሩ ነበር። አንዳንዶቹ “ይህ ለፍላፊ ምን ማለት ይፈልጋል?” ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ “ስለ አዳዲስ አማልክት የሚናገር ይመስላል” ይሉ ነበር፤ ይህንንም ያሉበት ምክንያት ጳውሎስ የኢየሱስንና የትንሣኤውን መልካም ዜና ስላበሠረ ነው።