Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 9:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ወይስ በሥራ እየጣርን መኖር የሚገባን በርናባስና እኔ ብቻ ነንን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ወይስ ያለመሥራት መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ወይስ ሥራን ለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወይስ ሥራን ለመ​ተው መብት የሌ​ለን እኔና በር​ና​ባስ ብቻ ነን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ወይስ ሥራን ለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 9:6
15 Referencias Cruzadas  

ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄደን ዛፍ በመቊረጥ የምንኖርበት ቤት በዚያ እንድንሠራ ፍቀድልን!” አሉት። ኤልሳዕም “እሺ መልካም ነው!” አላቸው።


ከእኛ እያንዳንዳችን የሚወለደውን የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን በማስረከብ፥ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን እናደርጋለን፤ እንዲሁም ከላሞቻችን፥ ከበጎቻችንና ከፍየሎቻችን የሚወለደውንም ጥጃና ግልገል ሁሉ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር እንለያለን።


በኢየሩሳሌም የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ይህን ስለ ሰማች በርናባስን ወደ አንጾኪያ ላከችው።


የአይሁድ መሪዎች ግን የአይሁድ እምነት ተከታዮች የሆኑትን ሀብታሞች ሴቶችና የከተማውን ታላላቅ ሰዎች አሳድመው በጳውሎስና በበርናባስ ላይ ስደት እንዲነሣ አደረጉ፤ ከአገራቸውም አስወጡአቸው።


በርናባስንም “ድያ” አሉት፤ ዋናው ተናጋሪ ጳውሎስ ስለ ነበረ እርሱን “ሄርሜን” አሉት።


የእርሱ ሥራ ልክ እንደ እነርሱ ድንኳን መስፋት ስለ ነበር ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ አብሮአቸው ይሠራ ነበር።


የቆጵሮስ ተወላጅ የሆነ፥ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዊ ነበረ፤ ሐዋርያት “በርናባስ” እያሉ ይጠሩት ነበር፤ ትርጓሜው “የመጽናናት ልጅ” ማለት ነው።


ስለዚህ ጉዳይ መከራከር የሚፈልግ ሰው ቢኖር እኛም ሆንን ወይም ሌሎች የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያን ከዚህ የተለየ ልማድ የለንም።


እናንተን ለማገልገል ከሌሎች አብያተ ክርስቲያን ርዳታ በመቀበሌ እነርሱን ዘርፌአቸዋለሁ።


ወንድሞች ሆይ! እንዴት እንደ ሠራንና እንደ ደከምን ታውቃላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ በምናበሥርበት ጊዜ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን በመሥራት እንደክም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos