ኤርምያስ 18:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወራሪዎችን በድንገት ላክባቸው፤ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ፤ እነርሱ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቆፍረዋል፤ የምያዝበትንም ወጥመድ አዘጋጅተዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊይዙኝ ጕድጓድ ስለ ቈፈሩ፣ ለእግሮቼም በስውር ወጥመድ ስለ ዘረጉ፣ በድንገት ወራሪ ስታመጣባቸው፣ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊይዙኝ ጉድጓድ ቆፍረዋልና፥ ለእግሮቼም ወጥመድ ሸሽገዋልና ድንገት በላያቸው ጭፍራ ባመጣህ ጊዜ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊይዙኝ ጕድጓድ ቈፍረዋልና፥ ለእግሮችም ወጥመድ ሸሽገዋልና፥ በቤታቸው ጩኸት ይሰማ፤ ድንገትም በላያቸው ወንበዴን አምጣባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊይዙኝ ጕድጓድ ቆፍረዋልና፥ ለእግሮቼም ወጥመድ ሸሽገዋልና ድንገት በላያቸው ጭፍራ ባመጣህ ጊዜ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ። |
ታዲያ የደግ ሥራ ዋጋው ክፉ ነገር ማድረግ ነውን? አንተ በእነርሱ ላይ እንዳትቈጣ እኔ በፊትህ ቆሜ ስለ እነርሱ እንደማለድኩህ አስብ፤ እነርሱ ግን እነሆ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቈፈሩ።
ብዙ ሰዎች ፈርተው በሹክሹክታ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ፤ “አሁን ኤርምያስን ለመክሰስ መልካም አጋጣሚ ነው!” ወዳጆቼ ናቸው የሚባሉት እንኳ ስሕተት እንዳደርግ ይጠባበቃሉ፤ “ኤርምያስ ሊታለል ይችል ይሆናል፤ ይህም ከሆነ እርሱን ይዘን እንበቀለዋለን፤” ይላሉ።
ምጥ የያዛት ሴት የምታሰማውን ጩኸት የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የመጀመሪያ ልጅዋን የምትወልድ በካር ሴት የምታሰማውን ድምፅ የመሰለ ኡኡታም አዳመጥኩ፤ ይህም ድምፅ ኢየሩሳሌም ትንፋሽ አጥሮአት እጅዋን ዘርግታ “ወዮልኝ! ጠፋሁ! እነሆ ሊገድሉኝ መጡ!” እያለች የምታሰማው ጩኸት ነበር።
“በሕዝቤ መካከል የሚኖሩ ክፉ ሰዎች አሉ፤ እነርሱም ወፎችን በወጥመድ እንደሚይዝ ሰው ናቸው፤ ስለዚህ ሰዎችን ለማጥመድ መረባቸውን ዘርግተው ያደባሉ።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “ሊያጠፋችሁ የመጣው ጠላት በድንገት አደጋ ሊጥልባችሁ ስለ ሆነ፥ ማቅ ለብሳችሁ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤ አንድ ልጁ እንደ ሞተበት ሰው ምርር ብላችሁ አልቅሱ፤