ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖች ንጉሥ ቤንሀዳድን እንዲህ አሉት፤ “የእስራኤል አማልክት የተራራ አማልክት ናቸው፤ እስራኤላውያን እኛን ማሸነፍ የቻሉት ስለዚህ ነው፤ በሜዳማ ስፍራዎች ጦርነት ብንገጥማቸው ግን እናሸንፋለን፤
ኤርምያስ 16:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! የምትጠብቀኝና ብርታትን የምትሰጠኝ አንተ ነህ፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ አምባዬ ነህ፤ ሕዝቦች ከምድር ዳርቻ ሁሉ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “የቀድሞ አባቶቻችን ከሐሰተኞች አማልክት በቀር ምንም አልነበራቸውም፤ ጣዖቶቻቸው ሁሉ የማይጠቅሙ ከንቱዎች ነበሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብርታቴና ምሽጌ፣ በመከራ ቀን መጠጊያዬ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤ አሕዛብ ከምድር ዳርቻ፣ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “አባቶቻችን ለአንዳች ነገር ያልረቧቸውን ከንቱ ጣዖቶች፣ የሐሰት አማልክትን ወረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ! ኃይሌ፥ አምባዬ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ፥ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር የማይረባቸውንም ወርሰዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ ሆይ! አንተ ኀይሌና ረዳቴ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ፤ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው፥ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር ለምንም የማይረባቸውን ጣዖትን ሠርተዋል” ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ኃይሌ፥ አምባዬ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ሆይ፥ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው፦ በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር የማይረባቸውንም ወርሰዋል ይላሉ። |
ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖች ንጉሥ ቤንሀዳድን እንዲህ አሉት፤ “የእስራኤል አማልክት የተራራ አማልክት ናቸው፤ እስራኤላውያን እኛን ማሸነፍ የቻሉት ስለዚህ ነው፤ በሜዳማ ስፍራዎች ጦርነት ብንገጥማቸው ግን እናሸንፋለን፤
ለድኾች፥ ለመጻተኞችና ለችግረኞች በችግራቸው ጊዜ መጠጊያ ሆነህላቸዋል፤ ከዐውሎ ነፋስ የሚድኑበት ተገንና ከፀሐይ ቃጠሎ የሚጠለሉበት ጥላ ሆነህላቸዋል፤ የጨካኞች ምት የክረምት ወጀብ ግድግዳን እንደሚገፋ ያለ ነው።
ከእነርሱ እያንዳንዱ ከነፋስ እንደሚከለሉበትና ከወጀብ እንደሚሰወሩበት መጠጊያ ይሆናል፤ በበረሓ እንደሚፈስሱ ጅረቶችና በምድረ በዳ እንደሚገኝ እንደ ትልቅ አለት መጠለያ ይሆናሉ።
ተቃጥሎ ዐመድ የሚሆነውን እንጨት እስከ ማምለክ ድረስ ሰው እንዴት ሞኝ ይሆናል? የሞኝነት አስተሳሰቡ አሳስቶታል፤ ራሱን ማዳን አይችልም፤ ወይም “ይህ በቀኝ እጄ ያለው ነገር ጣዖት እንጂ አምላክ አይደለም።” ብሎ መናገር አይችልም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የግብጽ ሀብትና የኢትዮጵያ ሸቀጥ ለእናንተ ተላልፎ ይሰጣል፤ ቁመታቸው ረጃጅም የሆነ የሳባ ሰዎችም በሰንሰለት ታስረው በመምጣት ይከተሉአችኋል፤ እጅ ነሥተውም፦ ‘እግዚአብሔር የሚገኘው በእናንተ ዘንድ ብቻ ነው፤ በሌላ አይደለም፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ይላሉ።”
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።
እንደነዚህ ያሉት ምስሎች በዱባ ተክል ውስጥ ለወፍ ማስፈራሪያ እንደሚተከሉ ነገሮች ናቸው፤ መናገር አይችሉም፤ መራመድ ስለማይችሉ ሰዎች ይሸከሙአቸዋል፤ ጒዳት ማድረስም ሆነ ጥቅም ማስገኘት ስለማይችሉ፥ ፈጽሞ አትፍሩአቸው።”
የሕዝቤን አካሄድ በሙሉ ልባቸው ተቀብለው እነርሱ ከዚህ በፊት ሕዝቤን በባዓል ስም መማል እንዳስተማሩአቸው ዐይነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የሚምሉ ከሆነ በሕዝቤ መካከል እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤
የእስራኤል ተስፋ አንተ ብቻ ነህ፤ ከመቅሠፍት የምታድነንም አንተ ነህ፤ ታዲያ በምድራችን እንደ እንግዳ፥ ለአንድ ቀን እንደሚያድር መንገደኛስ የሆንከው ለምንድን ነው?
ሐሰተኞች አማልክት ቢሆኑም እንኳ አማልክቱን የሚቀያይር ሕዝብ የለም፤ ሕዝቤ ግን ክብር ያጐናጸፍኳቸውን እኔን አምላካቸውን ምንም ሊያደርጉላቸው በማይችሉ ከንቱ አማልክት ለውጠውኛል።”
ካህናቱ ‘እግዚአብሔር ወዴት አለ?’ ብለው አልጠየቁም፤ የሕግ ምሁራን እንኳ አላወቁኝም፤ የሕዝብ ገዢዎች በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ነቢያትም በበዓል ስም ትንቢት ተናገሩ፤ ከንቱ የሆኑ ጣዖቶችንም አመለኩ።”
በኮረብቶች ራስ ላይ ቅጥ ያጣ የባዕድ አምልኮ ፈንጠዝያ መፈጸማችን ምንም አልጠቀመንም፤ ለእስራኤል መዳን የሚገኘው ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ብቻ ነው።
ለኢየሩሳሌም የማደርጋቸውን መልካም ነገሮች ሁሉ በሚሰሙት ሕዝቦች ፊት ለእኔ ገናናነት፥ ክብርና ምስጋናን ታስገኛለች፤ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ የማደርገውን መልካም ነገሮችና ለከተማይቱ የማመጣላትን ሀብትና በጎነት በሚሰሙበት ጊዜ አሕዛብ ሁሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ።”
ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሩቅ አገር በሚኖሩ ሕዝቦች መካከል እንዲኖሩ ባደርጋቸውና በተለያዩ አገሮች ብበትናቸውም እንኳ ለጥቂት ጊዜ ግን መገናኛቸው ቤተ መቅደስ እሆንላቸዋለሁ።
እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በኢየሩሳሌም ሆኖ፥ የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤ ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ለእስራኤል መጠጊያ ምሽግ ይሆናል፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ሕጌን ጥሰዋል፤ ትእዛዜንም አልጠበቁም፤ አባቶቻቸው ይከተሉአቸው የነበሩት የሐሰት አማልክት እነርሱንም አስተዋቸዋል፤
በዚያን ጊዜ ብዙ የአሕዛብ ነገዶች ከእግዚአብሔር ጋር ተባብረው ወገኖቹ ይሆናሉ። እርሱም በመካከላችሁ ይኖራል፤ እኔንም ወደ እናንተ የላከኝ እርሱ መሆኑን ትገነዘባላችሁ።
እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።
ይህም የሆነው የእግዚአብሔርን እውነት በሐሰት ስለ ለወጡ፥ በፈጣሪ ፈንታ ፍጡርን ስላመለኩና ስለ አገለገሉ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም የተመሰገነ ነው፤ አሜን።
ሰባተኛውም መልአክ እምቢልታውን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት የጌታ የአምላካችንና የመሲሑ ሆናለች፤ እርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤” የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ።