በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም እነግርሃለሁ” አለው።
ኤርምያስ 15:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ወደ እኔ በንስሓ ብትመለስ፥ እቀበልሃለሁ፤ እንደገናም አገልጋይ ትሆነኛለህ፤ ከንቱ ቃል መናገርህን ትተህ ቁም ነገር ያለውን መልእክት ብታስተላልፍ፥ እንደገና የእኔ ነቢይ ትሆናለህ፤ ሕዝቡ ወደ አንተ ይመጣሉ እንጂ አንተ ወደ እነርሱ አትሄድም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብትመለስ፣ መልሼ አቆምሃለሁ፤ ታገለግለኛለህም፤ የከበረውን ከማይረባው ለይተህ ብትናገር፣ አፍ ትሆነኛለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ እንጂ፣ አንተ ወደ እነርሱ አትመለስም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ፤ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፤ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፥ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፥ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም። |
በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም እነግርሃለሁ” አለው።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቆመው ቢማልዱ ለዚህ ሕዝብ ምሕረት አላደርግም፤ ስለዚህ ከፊቴ ወዲያ እንዲሄዱ አድርግ።
ነገር ግን “ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አላስታውስም፤ በስሙም አልናገርም” በምልበት ጊዜ፥ ከእርሱ የተሰጠኝ የትንቢት ቃል በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በውስጤ ሰውሬ ልይዘው ብሞክርም፤ አፍኜ ላስቀረው አይቻለኝም።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደ እኔ ለመመለስ ከፈለጋችሁ እነዚያን አጸያፊ ጣዖቶችን አስወግዳችሁ ለእኔ ብቻ ታማኞች ብትሆኑ፥
ሕዝብዋ ምግብ ማግኘት ፈልገው ይቃትታሉ፤ በሕይወት ለመኖር ሲሉ ሀብታቸውን ሁሉ በምግብ ይለውጣሉ፤ የኢየሩሳሌም ሕዝብ “እግዚአብሔር ሆይ! ተመልከተን! ውርደታችንን ሁሉ እይልን!” እያሉ ይጮኻሉ።
ካህናቱ ሕጌን ይጥሳሉ፤ ቅዱስ ለሆነ ነገርም አክብሮት የላቸውም፤ ቅዱሱን ከርኩሱ አይለዩም፤ ንጹሕ በሆነና ባልሆነ ነገር መካከል ያለውን አያስተምሩም፤ ሰንበትንም ያቃልላሉ፤ ከዚህ የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ እኔን አያከብሩኝም።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል አለው፦ “አካሄድህ እንደኔ ፈቃድ ቢሆን፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብታደርግ፥ በቤተ መቅደሴ የአስተዳዳሪነትን፥ በአደባባዮቼም የበላይነትን ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መላእክት ጋር በእኔ ፊት መግባትና መውጣት እንድትችል ባለሟልነትን እሰጥሃለሁ።
መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህን የምሥራች እንድነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬ መጥቻለሁ።
እንደገናም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “እናንተን የሚሰማ እኔን ይሰማል፤ እናንተን የማይቀበል እኔን አይቀበልም፤ እኔን የማይቀበልም የላከኝን አይቀበልም፤” አላቸው።
ከእንግዲህ ወዲህ እኛ ማንንም ሰው በሥጋዊ አመለካከት አንመለከትም፤ ከዚህ በፊት ክርስቶስንም የተመለከትነው እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋዊ አመለካከት ከሆነ ለወደፊቱ ግን ይህን አናደርግም።
ታዲያ፥ እኔ የምፈልገው ሰው እንዲያመሰግነኝ ነውን? ወይስ እግዚአብሔር እንዲያመሰግነኝ? ወይስ ሰውን ደስ ለማሰኘት የምፈልግ መስሎአችሁ ይሆን? ሰዎችን ለማስደሰት የምፈልግ ብሆን ኖሮ የክርስቶስ አገልጋይ ባልሆንኩም ነበር።