ኤርምያስ 12:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድረ በዳም ስላደረጉአት በፊቴ ባድማ ሆናለች፤ አገሪቱ በሙሉ ወደ በረሓነት ተለውጣለች፤ ስለ እርስዋም የሚገደው አንድ እንኳ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፊቴ ባድማ፣ ደረቅና ወና ይሆናል፤ መላዪቱም ምድር ጠፍ ትሆናለች፤ ስለ እርሷ የሚገድደው የለምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባድማ አድርገውታል፥ ፈርሶም ወደ እኔ ያለቅሳል፤ ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት ማንም የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ለፍጹም ጥፋት ሆናለች፤ ስለ እኔም ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች፤ በልቡም የሚያኖራት የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባድማ አድርገውታል፥ ፈርሶም ወደ እኔ ያለቅሳል፥ ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም። |
ስለዚህ የቊጣውን ግለትና አስፈሪውን ጦርነት በላያችን ላይ አወረደ፤ በዙሪያችን እሳት አቀጣጠለ፤ እኛ ግን ይህን ሁሉ አልተረዳነውም፤ አቃጠለን ልብም አላደረግነውም።
ጻድቃን ሲሞቱ ማንም ትኲረት አይሰጠውም፤ ደጋግ ሰዎች በሞት ሲወሰዱ ከክፉ ነገር እንዲድኑ የተወሰዱ መሆናቸውን ማንም ሰው ሊያስተውለው አይችልም።
አድምጡ አዲስ ዜና መጥቶአል! የሰሜን መንግሥት የይሁዳን ከተሞች ወደ ምድረበዳነት ለውጦ የቀበሮዎች መመሰጊያ ለማድረግ በመራወጥ ላይ ይገኛል።”
ቊጣህን አንተን በማያውቁና ስምህን በማይጠሩ ሕዝቦች ላይ አፍስሰው፤ እነርሱ ሕዝብህን ፈጅተዋል፤ ሁላችንንም ፈጽመው በመደምሰስ፥ አገራችንን አውድመዋል።
“ይሁዳ በሐዘን ላይ ነች፤ ከተሞችዋም በሞት ጣዕር ላይ ናቸው፤ ሕዝብዋም በሐዘን ምክንያት በመሬት ላይ ተቀምጠው ያለቅሳሉ፤ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ትጮኻለች።
ምድሪቱ እግዚአብሔርን በተዉ አመንዝሮች ተሞልታለች፤ ነቢያቱ ኀይላቸውን ያለ አግባቡ ይጠቀማሉ፤ የክፋትንም መንገድ ይከተላሉ፤ ከእግዚአብሔር ርግማን የተነሣ፥ ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ መስኮችም ደርቀዋል።
መቅሠፍት በመቅሠፍት ላይ ይደራረባል፤ አገሪቱ በሙሉ ፈራርሳ ጠፍ ሆናለች፤ ድንኳኖቻችን በድንገት ወደሙ፤ መጋረጃዎቻቸውም በቅጽበት ተቀደዱ።
ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማይም በጨለማ ይጋረዳል፤ ይህን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ሐሳቡም አይለወጥም፤ ቊርጥ ውሳኔ አድርጎአል፤ ወደ ኋላም አይመለስም።
እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ይህ ሁሉ መከራ ማስጠንቀቂያ ይሁናችሁ፤ አለበለዚያ ከፊቴ አስወግዳችኋለሁ፤ ከተማችሁን ወደ ምድረ በዳ ለውጬ ማንም እንዳይኖርባት አደርጋለሁ።”
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሁሉም ወና ስለ ሆኑና በእነርሱም ላይ የሚዘዋወርባቸው ስለሌለ፥ ስለ ተራራዎች አዝናለሁ፤ ስለ ሜዳዎችም አለቅሳለሁ፤ የከብቶች ድምፅ ዳግመኛ አይሰማም፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ሁሉ ሸሽተው ጠፍተዋል።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አደርጋታለሁ፤ የቀበሮዎችም መፈንጫ ትሆናለች፤ የይሁዳንም ከተሞች ማንም የማይኖርባቸው ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”
ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉና ለካህናቱ እንዲህ በላቸው፦ “ባለፉት ሰባ ዓመቶች በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር የጾማችሁትና ያዘናችሁት እኔን ለማክበር ነበርን?
ባታዳምጡ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት ቃሌን በልባችሁ ባታኖሩት መርገም እልክባችኋለሁ፤ በረከታችሁንም ወደ ርግማን እለውጣለሁ፤ እኔን ማክበር በልባችሁ ውስጥ ስለሌለ በእርግጥ ይህን ሁሉ አደርግባችኋለሁ።