ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ወደ አኪጦፌል መለስ ብሎ “እነሆ እኛ አሁን በዚህ ተገኝተናል፤ ታዲያ ምን እንድናደርግ ትመክረናለህ?” ሲል ጠየቀው።
ያዕቆብ 3:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምላስም እንደ እሳት ናት፤ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ ክፉ ዓለም ናት፤ አካላችንን ትበክላለች፤ ከገሃነም እንደሚወጣ እሳትም የኑሮአችንን ሂደት ሁሉ ታቃጥላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በሰውነታችን ክፍሎች መካከል ዐመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፤ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፤ በገሃነምም ይቃጠላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል። |
ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ወደ አኪጦፌል መለስ ብሎ “እነሆ እኛ አሁን በዚህ ተገኝተናል፤ ታዲያ ምን እንድናደርግ ትመክረናለህ?” ሲል ጠየቀው።
እስራኤላውያንም “እርሱ የእናንተ ወገን ቢሆንም እንኳ እናንተ ከምትፈልጉት ይበልጥ እኛ እንፈልገዋለን፤ ከመንግሥቱ ዐሥሩ እጅ የሚገባው ለእኛው ነው፤ እናንተ እኛን የምትንቁት ስለምንድን ነው? ንጉሡን ስለ መመለስ በመጀመሪያ ጥያቄ ያቀረብነው እኛ መሆናችንን ልትዘነጉ አይገባም!” አሉአቸው። ነገር ግን ከእስራኤል ሰዎች ይልቅ የይሁዳ ሰዎች ዳዊትን የራሳቸው ለማድረግ በብርቱ ተከራከሩ።
አቢያና ሠራዊቱ እስራኤላውያንን ድል አድርገው ከፍ ያለ ጒዳት አደረሱባቸው፤ በዚህ ጦርነት ከእስራኤል አምስት መቶ ሺህ ምርጥ ወታደሮች ተገደሉ።
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ኀይልና ግርማ ከሩቅ ይታያል፤ ነበልባልና ጢስ የቊጣው ምልክቶች ናቸው፤ በሚናገርበትም ጊዜ ቃሉ እንደ እሳት ይነዳል።
እናንተ ሁላችሁም ነገር በሰው ላይ እንደ እሳት የምታነዱና እንደ ችቦ የምትለኲሱ ናችሁ፤ ባነደዳችሁት እሳት ነበልባል ውስጥና በለኰሳችሁት ችቦ ትጠፋላችሁ ይህንንም ቅጣት የምትቀበሉት ከእኔ ነው።
ብዙ ሰዎች ፈርተው በሹክሹክታ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ፤ “አሁን ኤርምያስን ለመክሰስ መልካም አጋጣሚ ነው!” ወዳጆቼ ናቸው የሚባሉት እንኳ ስሕተት እንዳደርግ ይጠባበቃሉ፤ “ኤርምያስ ሊታለል ይችል ይሆናል፤ ይህም ከሆነ እርሱን ይዘን እንበቀለዋለን፤” ይላሉ።
ስለዚህም እግዚአብሔር ‘አንተን ከምድረ ገጽ አስወግድሃለሁ ይህ ሕዝብ በእኔ በአምላካቸው ላይ እንዲያምፁ በማድረግህ ምክንያት ይህ ዓመት ከመፈጸሙ በፊት ትሞታለህ’ ይላል።”
የእስራኤላዊቱ ልጅ የእግዚአብሔርን ስም ስለ ተሳደበ ወደ ሙሴ አቀረቡት፤ የእናቱም ስም ሰሎሚት የምትባልና ከዳን ነገድ የሆነው የዲብሪ ልጅ ነበረች።
እነዚያም ሴቶች ለሞአብ ጣዖት የተሠዋውን መሥዋዕት እንዲመገቡ ጋበዙአቸው፤ እስራኤላውያንም የመሥዋዕቱን ምግብ በልተው ፔዖር በሚባለው ተራራ ላይ ለሚገኘው በዓል ለተባለውም ጣዖት ሰገዱ፤
በፔዖር ሳለን የበለዓምን ምክር ተቀብለው ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት እንዲተዉ ያደረጉ ሴቶች መሆናቸውን ዘነጋችሁን? በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የአባር ቸነፈር መቅሠፍት ያመጣም ያ ስሕተት ነበር።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቈጣ ሁሉ ይፈረድበታል፤ ደግሞም ወንድሙን፥ ‘አንተ የማትረባ!’ ብሎ የሚሳደብ በሸንጎ ይፈረድበታል፤ ‘ደደብ!’ ብሎ የሚሳደብ ሁሉ በገሃነመ እሳት ይፈረድበታል።
ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ ‘አባት አብርሃም ሆይ! እባክህ ራራልኝ! በዚህ በእሳት ነበልባል ውስጥ በብርቱ እሠቃያለሁና የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ አልዓዛርን ላክልኝ!’
ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ “ሐናንያ ሆይ! በመንፈስ ቅዱስ ላይ እንድትዋሽና ከመሬቱም ሽያጭ ከፊሉን እንድታስቀር ያደረገህ ሰይጣን ስለምን ወደ ልብህ ገባ?
በእርሱ ላይ በሐሰት የሚመሰክሩ አንዳንድ ሰዎችንም አመጡ፤ የሐሰት ምስክሮችም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅደስና በሕግ ላይ የስድብ ቃል ከመናገር አይቈጠብም።
“በቅርብም ሆነ በሩቅ ካሉት፥ ከአንዱ የምድር ዳርቻ በአካባቢህ ካሉ ከአሕዛብ አማልክት አንተ ወይም አባቶችህ የማታውቁትን አንዱን እናምልክ በማለት ሌላ እንኳ ቀርቶ የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ በምሥጢር ይገፋፋህ ይሆናል።
ስለዚህ ወደ እናንተ ስመጣ እርሱ እየሰደበንና እያዋረደን ያደረገውን ክፉ ሥራ ሁሉ ለሁሉም እናገራለሁ፤ ይህም ሳይበቃው ቀርቶ፤ እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም። ሌሎችም እንዳይቀበሉአቸው ይከለክላል። ከቤተ ክርስቲያንም ያስወጣቸዋል።
ታላቁም ዘንዶ ወደታች ተጣለ፤ እርሱ መላውን ዓለም የሚያስተው ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው እባብ ነው። እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።
በመጀመሪያው አውሬ ፊት እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተአምራት ምክንያት በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር፤ በሰይፍ ቈስሎ ለዳነው ለአውሬው ክብር ምስል እንዲሠሩም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዛቸዋል።
የመብራት ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ አያበራም፤ የሙሽራውና የሙሽራይቱ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የዓለም ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤ በአስማትሽ ሕዝቦችን ሁሉ አሳስተሻል።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።