ብዛታቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የሆኑ ልጆችን ሰጠሃቸው፥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ትሰጣቸው ዘንድ ቃል የገባህላቸውን ምድር፥ በድል አድራጊነት እንዲይዙ ፈቀድክላቸው።
ኢሳይያስ 9:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ሕዝብህን አበዛህ፤ በደስታም እንዲሞሉ አደረግሃቸው፤ ሰዎች መከር በሚሰበስቡበት፥ ወይም ምርኮ በሚካፈሉበት ጊዜ ደስ እንደሚላቸው ሕዝብህም አንተ ባደረግኸው ነገር ደስ ይላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፤ የከበዳቸውን ቀንበር፤ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፤ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ሕዝብን በደስታ አወረድህ፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ምርኮንም እንደሚካፈሉ በፊትህ ደስ ይላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፥ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል። |
ብዛታቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የሆኑ ልጆችን ሰጠሃቸው፥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ትሰጣቸው ዘንድ ቃል የገባህላቸውን ምድር፥ በድል አድራጊነት እንዲይዙ ፈቀድክላቸው።
እኔ የሠራዊት አምላክ በዖሬብ አለት አጠገብ በምድያማውያን ላይ እንዳደረግሁት አሦራውያንን የምቀጣበት ጅራፍ ባሕሩን በበትሬ መትቼ ግብጻውያንን እንደቀጣሁ አሦራውያንን እቀጣለሁ። በግብጽ ላይ በትሬን እንዳነሣሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይም አነሣለሁ።
ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።
አምላክ ሆይ! የምድራችንን ወሰን በየአቅጣጫው በማስፋት መንግሥታችንን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ ሕዝባችንንም አበዛህ፤ ይህም አንተ የምትከብርበት ሆኖአል።
እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።
ምድረ በዳዎች በፈኩ አበቦች ይሞላሉ፤ የደስታ መዝሙርም ይዘምራሉ፤ እንደ ሊባኖስ ተራራ ግርማ ያላቸው ይሆናሉ፤ እንደ ቀርሜሎስም ተራራ ወይም እንደ ሻሮን ሸለቆ ክብርን የተጐናጸፉ ይሆናሉ። ሁሉም የእግዚአብሔርን ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባል ካላት ሴት ይልቅ ፈት የሆነችው ልጆች ብዛት ያላቸው ስለ ሆነ፥ ልጅ እንዳልወለደችና አምጣ እንደማታውቀው ሴት የሆንሽው ኢየሩሳሌም ሆይ! እልል እያልሽ ዘምሪ!
“እናንተም ከባቢሎን በደስታ ወጥታችሁ፥ በሰላም ወደ ሀገራችሁ እንድትመለሱ ትደረጋላችሁ፤ ተራራዎችና ኰረብቶች በፊታችሁ በመዘመር ይፈነድቃሉ፤ የሜዳ ዛፎችም በእጆቻቸው ያጨበጭባሉ።
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
ኀፍረታቸው እጥፍ ስለ ነበረ፤ ውርደትም የእነርሱ ዕድል ፈንታ መሆኑ ስለ ታወጀ ስለዚህ ድርሻቸው እጥፍ ይሆናል፤ ዘለዓለማዊ ደስታም ያገኛሉ።
አገልጋዮቼ ከልባቸው ደስታ የተነሣ ይዘምራሉ፤ እናንተ ግን ከልብ ሐዘን የተነሣ ታላቅሳላችሁ፤ ከመንፈስም ጭንቀት የተነሣ ዋይ፥ ዋይ ትላላችሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከሕዝቦች ሁሉ ስለምትበልጥ ስለ እስራኤል በደስታ ዘምሩ፤ ‘እግዚአብሔር ሕዝቡን አድኖአል፤ በእስራኤል ምድር የቀሩትን ሁሉ ተቤዥቶአል’ እያላችሁ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ።”
በባርነት እንዳትገዙ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ ተጭኖአችሁ የነበረውን የባርነት ቀንበር ሰብሬ፥ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአለሁ።”
በዚያን ጊዜ ብዙ የአሕዛብ ነገዶች ከእግዚአብሔር ጋር ተባብረው ወገኖቹ ይሆናሉ። እርሱም በመካከላችሁ ይኖራል፤ እኔንም ወደ እናንተ የላከኝ እርሱ መሆኑን ትገነዘባላችሁ።
በእነዚያ ቀኖች ዐሥር የሌላ አገር ሰዎች ወደ አንድ አይሁዳዊ ቀርበው የልብሱን ዘርፍ በመያዝ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለ ሰማን ከእናንተ ጋር እንሂድ’ ይሉታል።”
ኢየሱስ ክርስቶስን ያላያችሁት እንኳ ብትሆኑ ትወዱታላችሁ፤ አሁን እንኳ የማታዩት ብትሆኑ ታምኑበታላችሁ፤ በቃላት ሊገለጥ በማይቻልና በከበረ ደስታ ደስ ይላችኋል።
ሦስት መቶው የጌዴዎን ሰዎች እምቢልታቸውን በሚነፉበት ጊዜ እግዚአብሔር እያንዳንዱን የጠላት ወታደር በጓደኛው ላይና በሠራዊቱ ላይ ሰይፉን እንዲያነሣ አደረገ፤ ሠራዊቱም ፊታቸውን ወደ ጽሬራ በመመለስ እስከ ቤትሺጣ፥ ከዚያም አልፎ በጣባት አጠገብ እስካለው አቤልመሖላ ድረስ ሸሽተው ሄዱ።
ሁለቱ የምድያማውያን ነገሥታት ዜባሕና ጻልሙናዕ ሸሹ፤ ነገር ግን ጌዴዎን አሳዶ ማረካቸው፤ ሠራዊታቸውንም በሙሉ በድንጋጤ ላይ እንዲወድቁ አደረገ።
ከዚያም በኋላ ዳዊትን ወራሪዎቹ ወዳሉበት እየመራ አደረሰው። ወራሪዎቹም በየቦታው ተበታትነው በመብላትና በመጠጣት ተድላ ደስታ በማድረግ ላይ ነበሩ፤ ከፍልስጥኤምና ከይሁዳ ያገኙት ምርኮ እጅግ ብዙ ነበር፤