Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 9:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በጨለማ ይኖር የነበረ ሕዝብ እነሆ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገር ውስጥ ለሚኖሩትም ሁሉ ብርሃን ወጣላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ ምድር ላሉትም ብርሃን ወጣላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፤ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፤ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በጨ​ለማ የሄደ ሕዝብ ታላቅ ብር​ሃን አየ፤ በሞት ጥላና በጨ​ለማ ሀገ​ርም ለነ​በሩ ብር​ሃን ወጣ​ላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፥ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 9:2
22 Referencias Cruzadas  

ይኸውም ዳግመኛ ወደማልመለስበት ጭፍግግ ወዳለውና ድቅድቅ ጨለማ ወደ ሆነው አገር ከመሄዴ በፊት ነው።


ከእነርሱም መካከል አንዳንዶቹ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ውስጥ በሰንሰለትም ታስረው ይኖሩ ነበር።


ከነበሩበት ድቅድቅ ጨለማ አወጣቸው፤ የታሰሩበትንም ሰንሰለት ሰባበረ።


በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል።


እግዚአብሔር ሆይ! በሰላም እንድኖር የምታደርገኝ አንተ ብቻ ስለ ሆንክ እኔ በምተኛበት ጊዜ፥ በሰላም አንቀላፋለሁ።


ከእናንተ መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራና ለአገልጋዩ ቃል የሚታዘዝ ማነው? ብርሃን የሌለው በጨለማ የሚመላለስ በእግዚአብሔር ይታመን፤ እምነቱንም በአምላኩ ላይ ይጣል።


“ከእንግዲህ ወዲህ ፀሐይ በቀን፥ ጨረቃም በሌሊት አያበሩልሽም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናል።


እነዚያ የተሠቃዩት ግን ዳግመኛ ችግር አይደርስባቸውም። በቀድሞ ዘመን የዛብሎንና የንፍታሌም ምድር ተዋርዳ ትኖር ነበር፤ በኋለኛው ዘመን ግን ከሜዲቴራኒያን ባሕር ምሥራቅ ጀምሮ እስከ ዮርዳኖስ ማዶ ያለው በተለይም አሕዛብ ሰፍረውበት የነበረው የገሊላ ምድር ክብርን ይጐናጸፋል።


“ፕሊያዲስ” የተባሉትን ሰባቱን ከዋክብትና “ኦርዮን” ተብለው የሚጠሩትን የከዋክብት ክምችትን የፈጠረ፥ ሌሊቱን ወደ ቀን፥ ቀኑንም ወደ ሌሊት የሚለውጥ፥ የባሕሩን ውሃ አዞ፥ በምድር ላይ እንዲፈስ የሚያደርግ፥ ኀያላንንና ምሽጎቻቸውን የሚደመስስ እርሱ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።


በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ የሞት ጥላ በጣለበት ምድር ለሚኖሩትም ብርሃን ወጣላቸው።”


እርሱ ለአሕዛብ እውነትን የሚገልጥ ብርሃን ይሆናል፤ ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው።”


ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።


በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።


እንደገናም ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ እኔን የሚከተል ሁሉ የሕይወት ብርሃን ያገኛል፤ በጨለማም አይመላለስም” ሲል ተናገራቸው።


ቀድሞ እናንተ በጨለማ ውስጥ ትኖሩ ነበር፤ አሁን ግን የጌታ ስለ ሆናችሁ ብርሃን ናችሁ ስለዚህ በብርሃን እንደሚኖሩ ሰዎች ተመላለሱ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።


“ምርኮ አግኝተው በመካከላቸው እየተከፋፈሉ አይደለምን? አንድ ወይም ሁለት ቈነጃጅት ለያንዳንዱ ወንድ፥ ለሲሣራ በልዩ ልዩ ቀለማት ያጌጠ የልብስ ምርኮ፥ ለእኔም ለአንገቴ በአንገቴ ላይ በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ዝንጒርጒር ልብስ፥”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos