Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 31:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከሕዝቦች ሁሉ ስለምትበልጥ ስለ እስራኤል በደስታ ዘምሩ፤ ‘እግዚአብሔር ሕዝቡን አድኖአል፤ በእስራኤል ምድር የቀሩትን ሁሉ ተቤዥቶአል’ እያላችሁ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ያዕቆብ በደስታ ዘምሩ፤ ስለ ሕዝቦች አለቃ እልል በሉ፤ ምስጋናችሁን አሰሙ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ የእስራኤልን ቅሬታ፣ ሕዝብህን አድን’ በሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ስለ ያዕቆብ በደስታ ዘምሩ ስለ አሕዛብም አለቆች እልል በሉ፤ አውጁ፥ አመስግኑ፦ ጌታ ሆይ! ሕዝብህን የእስራኤልን ትሩፍ አድን በሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ! ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም አለ​ቆች ላይ እልል በሉ፤ አውሩ፤ አመ​ስ​ግ​ኑም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ አድ​ኖ​አል በሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ስለ ያዕቆብ ደስ ይበላችሁ ስለ አሕዛብም አለቆች እልል በሉ፥ አውሩ፥ አመስግኑ፦ እግዚአብሔር ሕዝቡን የእስራኤልን ቅሬታ አድኖአል በሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 31:7
37 Referencias Cruzadas  

በይሁዳ ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ወደ መሬት ሥር ሰዶ እንደሚያድግና እንደሚያፈራ ተክል ይሆናሉ።


አምላክ ሆይ! ሕዝብህን አድን፤ የአንተ የሆኑትንም ባርክ፤ እረኛቸውም ሁን፤ ለዘለዓለምም ተንከባከባቸው።


ምነው መዳን ለእስራኤል ከጽዮን በመጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፤ የያዕቆብ ልጆች ይደሰታሉ፤ የእስራኤል ሕዝብ ሐሴት ያደርጋሉ።


የቀሩትን ሕዝቤን ከበተንኳቸው አገር ሁሉ ሰብስቤ ወደ ትውልድ አገራቸው እመልሳቸዋለሁ፤ ብዙ ልጆች ስለሚወልዱ ቊጥራቸው እየጨመረ ይሄዳል።


በአሁኑም ዘመን ቢሆን፥ በጸጋ ተመርጠው የቀሩ ጥቂት እስራኤላውያን አሉ።


ኢሳይያስም ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ “የእስራኤል ልጆች ቊጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢበዛ እንኳ ከእነርሱ የሚድኑት ጥቂቶች ብቻ ናቸው።


እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ፥ ሞአብ እንደ ሰዶም አሞንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም በዳዋና በጨው ጒድጓድ ተወራ ለዘለቄታ ባድማ ትሆናለች፤ ከሞት የተረፈው ሕዝቤ ይበዘብዛቸዋል ንብረታቸውንም ይወርሳል።”


ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በቀሪውም ሕዝቡ ላይ በደልን የማይቈጥር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረት ማድረግ ስለሚያስደስትህ ቊጣህ ለዘለዓለም የሚቈይ አይደለም።


“የእስራኤል ሕዝብ! በጎች በበረት፥ የበግ መንጋም በማሰማሪያ ቦታ እንደሚሰበሰብ በእርግጥ ከእስራኤል ሕዝብ የተረፉትን በአንድነት እሰበስባለሁ፤ ምድሪቱም በሕዝብ የተሞላች ትሆናለች” ይላል እግዚአብሔር።


ክፉውን ነገር ጥሉ፤ መልካም የሆነውን ነገር ውደዱ፤ በየፍርድ አደባባዩም ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለተረፉት የእስራኤል ሕዝብ ምሕረት ያደርግላቸው ይሆናል።


የእግዚአብሔርንም ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ከጽዮን ተራራና ከኢየሩሳሌም መዳን ይገኛል፤ ከሚድኑትም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው ይገኙበታል።”


ለይሁዳ ሕዝቦች ግን ፍቅር አሳያቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ፤ የማድናቸውም በጦርነት ኀይል አይደለም፤ በሰይፍ፥ በቀስትና በፍላጻ ወይም በፈረስና በፈረሰኛ አይደለም።”


“ነገር ግን ጥቂቶቻችሁ እንድትተርፉ አደርጋለሁ፤ ጥቃቶቻችሁ ወደ ሌሎች ሕዝቦች በመሄድ ከጦርነት አምልጣችሁ በተለያዩ አገሮች ትበተናላችሁ።


ልጆቻቸው በወገኖች ዘንድ፥ የልጅ ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ። የሚያዩአቸው ሁሉ በእኔ በእግዚአብሔር የተባረኩ ዘሮች መሆናቸውን ያውቃሉ።


ሰማያት ሆይ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በማዳን ክብሩን ገልጦአልና በደስታ ዘምሩ፤ ምድርም ከታች እልል በዪ፤ ተራራዎች፥ ጫካዎችና በውስጣቸው የምትገኙ ዛፎች ሁሉ የደስታ ድምፅ እያሰማችሁ ፈንድቁ።


የአሦር ንጉሥ ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባለሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢውን ይቀጣ ይሆናል፤ ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ስለሚተርፉት እባክህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።”


በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።


የሠራዊት አምላክ ከጥፋት የሚተርፍ ዘር ባያስቀርልንማ ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን፥ እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር።


እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አድነን! ከመንግሥታት መካከል መልሰህ ወደ አገራችን አግባን፤ በዚያን ጊዜ እናመሰግንሃለን፤ ቅዱስ ስምህንም እናከብራለን።


እርሱ ጽዮንን ያድናል፤ የይሁዳንም ከተሞች ያድሳል፤ ሕዝቡም በዚያ ይኖራሉ፤ ምድሪቱንም የራሳቸው ያደርጋሉ።


እግዚአብሔር ይማረን፥ ይባርከንም፤ የፊቱ ብርሃን በላያችን ይብራ።


“ሕዝቦች ሆይ፥ እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋል፤ የሚጠሉትን ቀጥቶ የሕዝቡን ኃጢአት ያስተሰርያል፤ የምድሪቱን ርኲሰት ያነጻል ስለዚህ ከእርሱ ሕዝብ ጋር ደስ ይበላችሁ።”


አምላክህ እግዚአብሔር በብዙ ሕዝቦች መካከል እንደ ራስ መሪ ያደርግሃል እንጂ እንደ ጅራት ወደ ኋላ እንድትቀር አያደርግህም፤ ዛሬ እኔ የምሰጥህን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በታማኝነት ብትፈጽም ምንም ዐይነት ውድቀት ሳይደርስብህ ወደፊት ትገሠግሣለህ እንጂ ወደ ኋላ አትቀርም፤


በኮረብቶች ራስ ላይ ቅጥ ያጣ የባዕድ አምልኮ ፈንጠዝያ መፈጸማችን ምንም አልጠቀመንም፤ ለእስራኤል መዳን የሚገኘው ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ብቻ ነው።


ለእግዚአብሔር ዘምሩ! ጌታን አመስግኑ! እርሱ ችግረኞችን ከክፉ ሰዎች ኀይል ይታደጋል።


ስለዚህም ተመልሰው መጥተው በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በምሰጣቸውም የእህል፥ የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይት፥ የበግና የቀንድ ከብት በረከት ሁሉ ተድላ ደስታ ያደርጋሉ፤ በቂ ውሃ እንዳገኘች የተክል ቦታ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህ ወዲያም አያዝኑም።


በአንድ ወቅት በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ እንዴት ብቸኛ ሆነች! በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው እንዴት ባል እንደ ሞተባት ሴት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፥ አሁን እርስዋ እንደ ባሪያ ሆነች።


አፋችን በሳቅ ተሞላ፤ አንደበታችንም የደስታ መዝሙር ዘመረ፤ በዚህም ምክንያት አሕዛብ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” አሉን።


እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ በግልጽ ስለሚያዩ ከተማ ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የደስታ መዝሙር ሲዘምሩ አድምጪ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios