ኢሳይያስ 9:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፤ የከበዳቸውን ቀንበር፤ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፤ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 አምላክ ሆይ! ሕዝብህን አበዛህ፤ በደስታም እንዲሞሉ አደረግሃቸው፤ ሰዎች መከር በሚሰበስቡበት፥ ወይም ምርኮ በሚካፈሉበት ጊዜ ደስ እንደሚላቸው ሕዝብህም አንተ ባደረግኸው ነገር ደስ ይላቸዋል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ብዙ ሕዝብን በደስታ አወረድህ፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ምርኮንም እንደሚካፈሉ በፊትህ ደስ ይላቸዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፥ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል። Ver Capítulo |