ኢሳይያስ 19:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብጽ ሕዝብ በፍርሃት እንደ ሴት የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል፤ የሠራዊት አምላክ እነርሱን ለመቅጣት ኀይሉን በሚያሳይበት ጊዜ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴት ይሆናሉ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ በሚያንቀሳቅሰው ክንዱ ፊት ይፈራሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታም በእነርሱ ላይ ከሚያንቀሳቅሳት ከእጁ የተነሣ ይርዳሉ ይፈራሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከሚያወርድባቸው ፍርሀትና መንቀጥቀጥ የተነሣ ግብፃውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ከሚያንቀሳቅሳት ከእጁ መንቀሳቀስ የተነሣ ይሸበራሉ ይፈሩማል። |
እግዚአብሔር የግብጽን ባሕረ ልሳን ያደርቃል፤ ማንም ሰው በእግሩ መሻገር እንዲችል የኤፍራጥስን ወንዝ በኀይለኛ ነፋስ መትቶ ወደ ትናንሽ ሰባት ጅረቶች ይከፋፍለዋል።
ከጠላት ወታደር የአንድ ሰው ዛቻ ከእናንተ ሺህ ሰዎችን እንዲሸሹ ያደርጋል፤ እናንተን በሙሉ አምስት የጠላት ወታደሮች በተራራ ላይ እንዳለ የሰንደቅ ዓላማ ምሰሶና በኰረብታ ላይ ያለን ምልክት ጥቂቶቻችሁ ብቻ እስክትቀሩ ድረስ ያባርሩአችኋል።
በፈረሶቻቸው፥ በሠረገሎቻቸውና በቅጥር ወታደሮቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዝ! እነርሱም እንደ ሴቶች ይሁኑ፤ በሀብታሞቹ ላይ ሰይፍ መዛችሁ ሀብታቸውን ሁሉ ዝረፉ!
የባቢሎን ወታደሮች ጦርነቱን አቁመው በምሽጋቸው ተቀመጡ፤ የጀግንነትን ወኔ አጥተው እንደ ሴቶች ሆኑ፤ የከተማይቱ የቅጽር በሮች መወርወሪያዎች ተሰባብረዋል፤ ቤቶችም በእሳት ተቃጥለዋል።
በመከራ ባሕር ውስጥ ሲያልፉ እኔ እግዚአብሔር ማዕበሉን እመታለሁ፤ ጥልቅ የሆነውም የዓባይ ወንዝ ይደርቃል፤ ትዕቢተኛይቱ አሦር ትዋረዳለች፤ ግብጽም በትረ መንግሥትዋን ታጣለች።
“አሁን እኔ በእነርሱ ላይ እጄን አነሣለሁ፤ እነርሱም ባሪያዎች አድርገው ለገዙአቸው ምርኮኞች ይሆናሉ፤ ከዚያ በኋላ እናንተም የሠራዊት አምላክ እኔን እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
ጌታን መፍራት ምን መሆኑን ስለምናውቅ ሰዎችን እናስረዳለን፤ እኛ ምን መሆናችንንም እግዚአብሔር ያውቃል፤ እናንተም በልቡናችሁ ምን መሆናችንን እንደምታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ።