Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘካርያስ 2:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “አሁን እኔ በእነርሱ ላይ እጄን አነሣለሁ፤ እነርሱም ባሪያዎች አድርገው ለገዙአቸው ምርኮኞች ይሆናሉ፤ ከዚያ በኋላ እናንተም የሠራዊት አምላክ እኔን እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እነሆ፤ እጄን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል፤ ከዚያም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እኔን እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በመካከሏም ክብር እሆናለሁ፥ ይላል ጌታ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እነሆ፥ እጄን በላያቸው አወዛውዛለሁ፥ ተገዝተው ለነበሩት ብዝበዛ ይሆናሉ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እነሆ፥ እጄን በላያቸው አወዛውዛለሁ፥ ተገዝተው ለነበሩት ብዝበዛ ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 2:9
30 Referencias Cruzadas  

የግብጽ ሕዝብ በፍርሃት እንደ ሴት የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል፤ የሠራዊት አምላክ እነርሱን ለመቅጣት ኀይሉን በሚያሳይበት ጊዜ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፤


በዚያን ጊዜ በሩቅ የሚኖሩ ሰዎች የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲታደስ ለመርዳት ይመጣሉ። ቤተ መቅደሱ በታደሰ ጊዜ እኔን ወደ እናንተ የላከኝ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሆኑን ታውቃላችሁ። ይህም ሁሉ የሚፈጸመው ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቃል ፍጹም ታዛዦች የሆናችሁ እንደ ሆነ ነው።


“የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤተ መቅደስ መሠረት ጥለዋል፤ እጆቹም ይፈጽሙታል፤ ያን ጊዜ የሠራዊት አምላክ እኔን ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።


ስለዚህም ከየስፍራው የማገዶ እንጨት መሰብሰብም ሆነ፥ ከየጫካውም ዛፍ መቊረጥ አያስፈልጋቸውም፤ ምክንያቱም ወድቆ የቀረውን የጦር መሣሪያ ሁሉ ሰብስበው ማንደድ ይችላሉ፤ ቀድሞ የበዘበዙአቸውንና የዘረፉአቸውን አሁን በተራቸው መበዝበዝና መዝረፍ ይችላሉ፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።


የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል።


እግዚአብሔር የግብጽን ባሕረ ልሳን ያደርቃል፤ ማንም ሰው በእግሩ መሻገር እንዲችል የኤፍራጥስን ወንዝ በኀይለኛ ነፋስ መትቶ ወደ ትናንሽ ሰባት ጅረቶች ይከፋፍለዋል።


ይህንን ለእናንተ መናገሬ ግን ጊዜው ሲደርስ ምን እንዳልኳችሁ እንድታስታውሱ ነው።” “ይህን ሁሉ ከአሁን በፊት ያልነገርኳችሁ ከእናንተ ጋር ስለ ነበርኩ ነው፤


ይህ ከመሆኑ በፊት አሁን አስቀድሜ የምነግራችሁ፤ ከተፈጸመ በኋላ፥ በእኔ ማንነት እንድታምኑ ነው።


እናንተን የሚነካ የእርሱን ዓይን ብሌን እንደሚነካ ሆኖ ይቈጠራል። የክብር ጌታ በበዘበዙአችሁ ሕዝቦች ላይ በላከኝ ጊዜ የተናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው።


እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ፥ ሞአብ እንደ ሰዶም አሞንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም በዳዋና በጨው ጒድጓድ ተወራ ለዘለቄታ ባድማ ትሆናለች፤ ከሞት የተረፈው ሕዝቤ ይበዘብዛቸዋል ንብረታቸውንም ይወርሳል።”


በሊባኖስ ላይ ያደረስከው ዐመፅ ይደርስብሃል፤ በእንስሶች ላይ ያደረግኸው ጥፋት ያስደነግጥሃል፤ ይህም የሚሆነው ሰውን ስለ ገደልክ፥ አገሮችንና ከተሞችን፥ በእነርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ ስላጠፋህ ነው።


የብዙ ሕዝቦችን ንብረት ስለ ዘረፋችሁ ከእነርሱ የተረፉት የእናንተን ንብረት ይዘርፋሉ፤ ይህም የሚሆነው እናንተ ሰዎችን ስለ ገደላችሁ፥ ምድሪቱን ከተሞችንና በእነርሱ የሚኖሩትን ስላጠፋችሁ ነው።


ነገር ግን ስለ ሰላም የተናገረ ነቢይ ቢኖር ከእግዚአብሔር የተላከ ነቢይ መሆኑ የሚታወቀው ያ የተናገረው ትንቢት እውነት ሆኖ ሲገኝ ነው።”


ሕዝቦች ሁሉ ያገለግሉታል፤ እንዲሁም የገዛ ሕዝቡ የሚወድቅበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ ለልጁና ለልጅ ልጁ ጭምር ተገዢዎች ይሆናሉ፤ ከዚያም በኋላ የእርሱ ሕዝብ ለኀያላን ሕዝቦችና ለታላላቅ ነገሥታት አገልጋዮች ይሆናሉ።’


ሕዝባችሁ ግን የምሰሶው ገመድ እንደ ላላ ምሰሶውም እንዳልጸና፥ ሸራውም እንዳልተዘረጋ መርከብ ነው፤ ከዚያ በኋላ የተትረፈረፈ ምርኮ ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ገብተው ይበዘብዛሉ።


አንተ ማንም ጥፋት ሳያደርስብህ ጥፋተኛ የሆንክ! ማንም ሳይከዳህ ከዳተኛ የሆንክ ወዮልህ! ጥፋትን ማድረስህን ስታቆም ትጠፋለህ፤ ከዳተኛነትህንም ስታቆም ክዳት ይደርስብሃል።


ምንም ነገር በማይበቅልበት ተራራ ጫፍ ሆናችሁ ምልክት ስጡ፤ ወደ ትዕቢተኞቹ የባቢሎን ገዢዎች ወደሚያስገባው በር እንዲገቡ ትእዛዝ ስጡ።


ዛሬ ጠላት በኖብ ከተማ የሚገኝ ሲሆን፥ የኢየሩሳሌም ከተማ በሆነችው በጽዮን ኰረብታ ላይ ለማስፈራራት ክንዱን እየነቀነቀ ነው።


ወደ እኔ ቀርባችሁ ይህን ስሙ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ የተናገርኩት በምሥጢር አይደለም፤ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እኔ እዚያ ነበርኩ።” አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።


በዚያን ጊዜ ብዙ የአሕዛብ ነገዶች ከእግዚአብሔር ጋር ተባብረው ወገኖቹ ይሆናሉ። እርሱም በመካከላችሁ ይኖራል፤ እኔንም ወደ እናንተ የላከኝ እርሱ መሆኑን ትገነዘባላችሁ።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር መላውን ከተማና በእዚያም በሚሰበሰቡበት ሁሉ ላይ በቀን ጥቅጥቅ ያለ ደመናን፥ በየሌሊቱም በሚንበለበለው የእሳት ብርሃን ይልካል። የእግዚአብሔርም ክብር ከተማይቱን እንደ ትልቅ ድንኳን ሸፍኖ ይጠብቃታል።


በእናንተ መካከል ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ስለ ሆነ በጽዮን የምትኖሩ ሁሉ ‘እልል’ በሉ!”


በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር የሚከተለው መዝሙር ይዘመራል፦ ጠንካራ ከተማ አለን፤ እንደ ቅጥርና እንደ ምሽግ የጸና መዳኛም አድርጎላታል።


እዚያም ማንም ጀልባዎችን በማይቀዝፍባቸውና ትላልቅ መርከቦች በማይንሳፈፉባቸው በወንዞችና በሰፋፊ ጅረቶች እግዚአብሔር በታላቅ ግርማው ከእኛ ጋር ይሆናል።


ከእንግዲህ ወዲህ በምድርሽ የዐመፅ ድምፅ በድንበሮችሽም ጥፋት ወይም ውድመት አይሰማም፤ ነገር ግን ቅጥሮችሽን መዳን የቅጥር በሮችሽን ምስጋና ብለሽ ትጠሪአቸዋለሽ።


“ከእንግዲህ ወዲህ ፀሐይ በቀን፥ ጨረቃም በሌሊት አያበሩልሽም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናል።


እስቲ አድምጡ! “እግዚአብሔር ዳግመኛ በጽዮን አይገኝምን? የጽዮን ንጉሥ ዳግመኛ በዚያ አይኖርምን?” እያሉ ሕዝቤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ሲጮኹ እሰማለሁ። ንጉሣቸው እግዚአብሔርም፦ “ጣዖቶቻችሁን በማምለክና ለባዕድ አማልክታችሁም በመስገድ የምታስቈጡኝ ስለምንድን ነው?” ሲል ይመልስላቸዋል፤


ሕዝቤ ሆይ! እኔ በመካከላችሁ እንዳለሁ፥ አምላካችሁም እኔ ብቻ እንደ ሆንኩና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ ሕዝቤ ከእንግዲህ ወዲህ ኀፍረት አይደርስባቸውም።”


እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ያስተላለፈውን የቅጣት ፍርድ አንሥቶላችኋል፤ ጠላቶቻችሁንም አስወግዶላችኋል፤ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲህ ጥፋት ይደርስብናል ብላችሁ አትፈሩም።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይከላከልላቸዋል፤ እነርሱም ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤ የጠላትንም የወንጭፍ ድንጋይ ይረጋግጣሉ፤ የወይን ጠጅ ጠጥቶ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤ የጠላቶቻቸውም ደም የመሥዋዕት ደም በሳሕን ሞልቶ በመሠዊያ ላይ እንደሚፈስስ ይፈስሳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios