Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 19:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በዚ​ያም ቀን የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ወ​ር​ድ​ባ​ቸው ፍር​ሀ​ትና መን​ቀ​ጥ​ቀጥ የተ​ነሣ ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሴቶች ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴት ይሆናሉ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ በሚያንቀሳቅሰው ክንዱ ፊት ይፈራሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታም በእነርሱ ላይ ከሚያንቀሳቅሳት ከእጁ የተነሣ ይርዳሉ ይፈራሉም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የግብጽ ሕዝብ በፍርሃት እንደ ሴት የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል፤ የሠራዊት አምላክ እነርሱን ለመቅጣት ኀይሉን በሚያሳይበት ጊዜ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ከሚያንቀሳቅሳት ከእጁ መንቀሳቀስ የተነሣ ይሸበራሉ ይፈሩማል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 19:16
18 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ በመካከልሽ ያሉ ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፣ የአገርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ፈጽሞ ተከፍተዋል፥ እሳትም መወርወሪያዎችህን በልቶአል።


የባ​ቢ​ሎን ተዋ​ጊ​ዎች መዋ​ጋ​ትን ትተ​ዋል፤ በአ​ም​ባ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ጠፍ​ቶ​አል፤ እንደ ሴቶ​ችም ሆነ​ዋል፤ ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ነድ​ደ​ዋል፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተሰ​ብ​ረ​ዋል።


ሰይፍ በፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውና በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸው ላይ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም በተ​ቀ​ላ​ቀሉ ሕዝብ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም እንደ ሴቶች ይሆ​ናሉ፤ ሰይፍ በመ​ዝ​ገ​ቦ​ችዋ ላይ አለ፤ ይበ​ተ​ና​ሉም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የግ​ብ​ፅን ባሕር ያደ​ር​ቃል፤ በኀ​ይ​ለ​ኛም ነፋስ እጁን በወ​ንዙ ላይ ያነ​ሣል፤ ሰባት ፈሳ​ሾ​ች​ንም ይመ​ታል፤ ሰዎ​ችም በጫ​ማ​ቸው እን​ዲ​ሻ​ገሩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።


እነሆ፥ እጄን በላያቸው አወዛውዛለሁ፥ ተገዝተው ለነበሩት ብዝበዛ ይሆናሉ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።


ዛሬ በእጁ እን​ዲ​ኖሩ በመ​ን​ገዱ ለምኑ፤ የጽ​ዮን ልጅ ተራ​ራ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ኮረ​ብ​ቶች አጽኑ።


በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ነው።


ከአ​ንድ ሰው ዛቻ የተ​ነሣ ሺህ ሰዎች ይሸ​ሻሉ፤ እና​ን​ተም በተ​ራራ ራስ ላይ እን​ዳለ ምሰሶ፥ በኮ​ረ​ብ​ታም ላይ እን​ዳለ ምል​ክት ሆና​ችሁ እስ​ክ​ት​ቀሩ ድረስ፥ ከአ​ም​ስት ሰዎች ዛቻ የተ​ነሣ ብዙ​ዎች ይሸ​ሻሉ።”


በኀ​ይ​ላ​ቸው የሚ​ታ​መኑ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ታ​ቸ​ውም ብዛት የሚ​ኮሩ፤


እኔም በድ​ካ​ምና በፍ​ር​ሀት፥ በብዙ መን​ቀ​ጥ​ቀ​ጥም መጣሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ዐው​ቀን ሰዎ​ችን እና​ሳ​ም​ና​ለን፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እኛ የተ​ገ​ለ​ጥን ነን፤ እን​ዲ​ሁም በል​ቡ​ና​ችሁ የተ​ገ​ለ​ጥን እንደ ሆን እን​ታ​መ​ና​ለን።


ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምል​ክ​ትን አቁሙ፤ ድም​ፃ​ች​ሁ​ንም ከፍ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ አለ​ቆች በእጅ ጥቀሱ። በሮ​ች​ንም ክፈቱ።


በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ እንደ እርሱ ያል​ሆነ፥ ኋላም ደግሞ እንደ እርሱ የማ​ይ​ሆን ታላቅ ጩኸት ይሆ​ናል።


ከዔ​ሳው ተራራ ሰዎች ሁሉ ይጠፉ ዘንድ የቴ​ማን ሰል​ፈ​ኞ​ችህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


እግዚአብሔር ከተቀደሰ ማደሪያው ነቅቶአልና ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሆይ፥ በፊቱ ዝም በል።


እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕርንም ሞገድ ይመታል፥ የወንዙም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል፣ የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብጽም በትረ መንግሥት ይርቃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios