Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ናሆም 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ወታደሮችሽ ሁሉ እንደ ሴት ፈሪዎች ሆነዋል፤ የጠረፍሽ በሮች ለጠላቶችሽ ክፍት ሆነዋል፤ መወርወሪያዎቹም እሳት በልቶአቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እነሆ፤ ጭፍሮችሽ፣ ሁሉም ሴቶች ናቸው! የምድርሽ በሮች፣ ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ተከፍተዋል፤ መዝጊያዎቻቸውንም እሳት በልቷቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነሆ፥ በመካከልሽ ያለው ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፤ የምድርሽ በሮች ለጠላቶችሽ በሰፊው ተከፍተዋል፥ መወርወሪያዎችሽን እሳት በልቶአቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እነሆ፥ በመካከልሽ ያሉ ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፣ የአገርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ፈጽሞ ተከፍተዋል፥ እሳትም መወርወሪያዎችህን በልቶአል።

Ver Capítulo Copiar




ናሆም 3:13
11 Referencias Cruzadas  

የባቢሎን ወታደሮች ጦርነቱን አቁመው በምሽጋቸው ተቀመጡ፤ የጀግንነትን ወኔ አጥተው እንደ ሴቶች ሆኑ፤ የከተማይቱ የቅጽር በሮች መወርወሪያዎች ተሰባብረዋል፤ ቤቶችም በእሳት ተቃጥለዋል።


የግብጽ ሕዝብ በፍርሃት እንደ ሴት የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል፤ የሠራዊት አምላክ እነርሱን ለመቅጣት ኀይሉን በሚያሳይበት ጊዜ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፤


በወንዙ በኩል ያሉት የከተማይቱ ቅጽር በሮች ወለል ብለው ተከፈቱ፤ ቤተ መንግሥቱም በሽብር ተሞላ።


በፈረሶቻቸው፥ በሠረገሎቻቸውና በቅጥር ወታደሮቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዝ! እነርሱም እንደ ሴቶች ይሁኑ፤ በሀብታሞቹ ላይ ሰይፍ መዛችሁ ሀብታቸውን ሁሉ ዝረፉ!


እርሱ የበሮችሽን መወርወሪያ አጠንክሮ ይጠብቃል፤ በውስጥሽ ያሉትንም ሕዝቦችሽን ይባርካል።


ከናስ የተሠሩትን በሮች ሰባበረ፤ የብረት መወርወሪያዎችንም ቈራረጠ።


ሟርተኞቻቸው ሞኞች ይሆኑ ዘንድ ወታደሮቻቸውም በፍርሃት ይርበደበዱ ዘንድ ሰይፍ በእነርሱ ላይ ይመዘዝ!።


በእሳት ትቃጠያለሽ ሕዝብሽም በጦርነት ማለቁ አይቀርም፥ በአንበጣ እንደ ተበላ ሰብል ትጠፊያለሽ፤ ስለዚህ እንደ አንበጣና እንደ ኲብኲባ ተባዙ።


በኤዶም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይገደላሉ፤ የቴማንም ጀገኖች በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ።”


ነነዌ ተዋረደች፤ ንግሥቲቱ ተማርካ ተወሰደች፤ ሴቶች አገልጋዮችዋ የርግብ ድምፅ የመሰለ የሐዘን ድምፅ ያሰማሉ፤ ደረታቸውንም እየመቱ ያለቅሳሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios