ኢሳይያስ 16:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞአብ ስደተኞች በመካከላችሁ ይኑሩ፤ ሊያጠፉአቸው ከሚፈልጉ ወገኖች መጠጊያ ሁኑአቸው።” ጨቋኞች ከእንግዲህ ወዲያ አይኖሩም፤ ያገር መፈራረስም ያከትማል። ወራሪዎችም ይወገዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞዓባውያን ስደተኞች ከእናንተ ጋራ ይቈዩ፤ እናንተም ከአጥፊው መጠጊያ ሁኗቸው።” የጨቋኙ ፍጻሜ ይመጣል፤ ጥፋቱ ያከትማል፤ እብሪተኛም ከምድር ገጽ ይጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ዘንድ ይኑሩ፤ ስደተኞቹን ከሚሳድዷቸው መሸሸጊ ሁኛቸው። የሚያስጨንቁ አልቀዋል፥ ጥፋትም ቀርቷል፤ ጨቋኞች የነበሩ ከምድር ጠፍተዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሚከቧችሁ ጋር ጠላቶች እንዳይሆኗችሁ ከሞዓብ የተሰደዱትን ከእናንተ ጋር አታስቀምጡ፤ ሰልፈኞች አልቀዋልና፤ በሀገሪቱ ሁሉ የነበረውም አለቃ ጠፍቶአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ጋር ይቀመጡ፥ ከሚያጠፋቸው ፊት መጋረጃ ሁኛቸው። የሚያስጨንቁ አልቀዋል፥ ጥፋትም ቀርቷል፥ ይጨቍኑ የነበሩ ከምድር ጠፍተዋል። |
አንተ ማንም ጥፋት ሳያደርስብህ ጥፋተኛ የሆንክ! ማንም ሳይከዳህ ከዳተኛ የሆንክ ወዮልህ! ጥፋትን ማድረስህን ስታቆም ትጠፋለህ፤ ከዳተኛነትህንም ስታቆም ክዳት ይደርስብሃል።
ጨቋኞችሽ የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ በወይን ጠጅ እንደሚሰክሩ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ። ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ የእስራኤል ኀያል አምላክ መሆኔን የዓለም ሕዝብ ሁሉ ያውቃል።”
ምድርን የመሠረተና ሰማያትን የዘረጋ ፈጣሪአችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ሊያጠፉአችሁ ከተዘጋጁ ከጨቋኞቻችሁ ቊጣ የተነሣ፥ ዘወትር በፍርሃት ትኖራላችሁ። የእነርሱስ ቊጣ የት አለ?
በፍትሕና በእውነት ላይ ትመሠረቺአለሽ፤ ግፍና ጭቈና ከአንቺ ይርቃል የሚያስፈራሽም የለም፤ ሽብርም ከአንቺ ይርቃል፤ ወደ አንቺም አይቀርብም።
ምግባችሁን ከተራበ ሰው ጋር እንድትካፈሉ፥ ማደሪያ የሌለውን ድኻ በቤታችሁ እንድትቀበሉ፥ የተራቈቱትን እንድታለብሱ፥ ከቅርብ ዘመዶቻችሁም ራሳችሁን እንዳትደብቁ አይደለምን?
በቀድሞ ዘመን ምድያማውያንን ድል እንዳደረግህ ሁሉ፥ አሁንም በሕዝብህ ላይ የተጫነውን የአገዛዝ ቀንበርና በትከሻቸው ላይ የተቃጣውን በትር ሰባበርክ፤ ሕዝብህን በማስጨነቅ ይገዛ የነበረውን ድል አደረግህ።
ይህ በዚህ እንዳለ በሞአብ፥ በዐሞን፥ በኤዶምና በሌሎችም አገሮች የሚኖሩ እስራኤላውያን የባቢሎን ንጉሥ ጥቂት የአይሁድ ቅሪቶችን ማስቀረቱንና ለእነርሱም ገዳልያን ገዢ አድርጎ መሾሙን ሰሙ፤
ምሽጎችዋም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ የሚያደርግ ሞአብን የሚደመስሳት እነሆ እዚህ ስለ አለ፥ በዲቦን ከተማ የምትኖሩ ሁሉ ከክብር ቦታችሁ ወርዳችሁ በምድር ትቢያ ላይ ተቀመጡ፤
እግዚአብሔር እንደ ተናገረ አጥፊው በከተሞች ሁሉ ላይ ይመጣል፤ አንድም የሚያመልጥ ከተማ የለም። ሸለቆውንና ሜዳውን እንዳልነበሩ ያደርጋል።
የሚሸሹትን ለመግደል በመስቀልኛ መንገድ ላይ ባላደባህባቸውም ነበር፤ የተረፉትንም በመከራቸው ቀን ለጠላት አሳልፈህ መስጠት ባልተገባህም ነበር።”
የይሁዳ ሕዝብ ጠላቶቻቸውን ረግጠው ከመንገድ ጭቃ ጋር እንደሚለውሱ እንደ ብርቱ ጦረኞች ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ስለ ሆነ በርትተው በመዋጋት ፈረሰኞችን ሳይቀር ድል ይነሣሉ።
ከዚህ በኋላ ምድሬን ዙሪያዋን ከብቤ እጠብቃለሁ፤ የወራሪ ኀይል መተላለፊያም አላደርጋትም። ሕዝቤ ምን ያኽል እንደ ተሠቃየ ስለ ተመለከትኩ ከእንግዲህ ወዲህ ጨቋኞች አይወሩአቸውም።”
ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”
“እስራኤላዊውም ሆነ ወይም ከአገርህ ከተማዎች በአንዱ የሚኖር የውጪ አገር ተወላጅ ድኻና ችግረኛ ሆኖ የተቀጠረውን ማናቸውንም ሰው አትበዝብዘው።
ከቤተ መቅደሱ ውጪ ያለውን ክፍት ቦታ ግን ተወው፤ እርሱ ለአሕዛብ የተሰጠ ስለ ሆነ አትለካው፤ አሕዛብ ቅድስቲቱን ከተማ ለአርባ ሁለት ወር ይረግጡአታል፤