Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 48:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር እንደ ተናገረ አጥፊው በከተሞች ሁሉ ላይ ይመጣል፤ አንድም የሚያመልጥ ከተማ የለም። ሸለቆውንና ሜዳውን እንዳልነበሩ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በእያንዳንዱ ከተማ ላይ አጥፊ ይመጣል፤ አንድም ከተማ አያመልጥም። እግዚአብሔር ተናግሯልና፣ ሸለቆው ይጠፋል፤ ዐምባውም ይፈርሳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታም እንደ ተናገረው፥ አጥፊው ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል አንዲትም ከተማ አትድንም፤ ሸለቆውም ይጠፋል ሜዳውም እንዳልነበረ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ ጥፋት ወደ ከተማ ሁሉ ይመ​ጣል፤ አን​ዲ​ትም ከተማ አት​ድ​ንም፤ ሸለ​ቆ​ውም ይጠ​ፋል፤ ሜዳ​ውም ይበ​ላ​ሻል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ አጥፊ ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል አንዲትም ከተማ አትድንም፥ ሸለቆውም ይጠፋል ሜዳውም ይበላሻል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 48:8
10 Referencias Cruzadas  

በምድራችሁ ላይ የሚገኙት ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ብዛታቸው ከባሕር አሸዋ የሚበልጥ ሆኖአል፤ በእኩለ ቀን በወጣቶች እናቶች ላይ ሞትን አመጣለሁ በእነርሱም ላይ ሽብርንና ጭንቀትን በቅጽበት አመጣለሁ።


‘እነሆ በስተሰሜን ወዳሉት ነገዶችና አገልጋዬ ወደ ሆነው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መልእክተኛ እልካለሁ፤ ይሁዳንና በውስጥዋ የሚኖሩትን፥ እንዲሁም በጐረቤት ያሉትን ሕዝቦች ይወጉ ዘንድ አመጣቸዋለሁ፤ ይህችን አገር ከነጐረቤቶችዋ አጠፋለሁ፤ ለማየት የሚያስፈሩና መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ምሽጎችዋም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ የሚያደርግ ሞአብን የሚደመስሳት እነሆ እዚህ ስለ አለ፥ በዲቦን ከተማ የምትኖሩ ሁሉ ከክብር ቦታችሁ ወርዳችሁ በምድር ትቢያ ላይ ተቀመጡ፤


አጥፊዎች በባቢሎን ላይ ስለ ዘመቱ ወታደሮችዋ ተማረኩ፤ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እኔ ለሁሉም እንደየሥራው ዋጋውን የምከፍል አምላክ ስለ ሆንኩ፥ ባቢሎን በፈጸመችው ግፍ መጠን ፍዳዋን እከፍላታለሁ።


እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “ሊያጠፋችሁ የመጣው ጠላት በድንገት አደጋ ሊጥልባችሁ ስለ ሆነ፥ ማቅ ለብሳችሁ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤ አንድ ልጁ እንደ ሞተበት ሰው ምርር ብላችሁ አልቅሱ፤


ቤትየሺሞት፥ ባዓልመዖንና ቂርያታይም የተባሉት ዝነኞቹ ከተሞች ሳይቀሩ የሞአብ ጠረፍ የሚጠበቅባቸው ከተሞችን ሁሉ በጠላት እንዲመቱ አደርጋለሁ።


እንዲሁም ሐሴቦንን፥ በደጋማ አገር ያሉትን ከተሞች፥ ዲቦን፥ ባሞትበዓል፥ ቤትበዓልመዖን፥


በደጋማው አገር የሚገኙትን ከተሞችና መኖሪያውን በሐሴቦን አድርጎ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖንን ግዛት ሁሉ ይጨምራል። ሙሴም ንጉሥ ሲሖንንና የምድያም መሪዎች የነበሩትን፥ ኤዊን፥ ሬቄምን፥ ጹርን፥ ሑርንና ሬባዕን ድል ነሣ፤ እነዚህ ሁሉ ምድሪቱን የሚያስተዳድሩት የንጉሥ ሲሖን ገባሮች በመሆን ነበር።


ግዛታቸውም ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከሆነው ከዓሮዔር ተነሥቶ እንዲሁም በሸለቆው መካከል ካለው ከተማ ከሜዴባ ሜዳ እስከ ዲቦን ድረስ ይደርሳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos