ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት እንደ አመንዝራ ሆነች! ቀድሞ ፍትሕ የሰፈነባትና የጻድቃን መኖሪያ ነበረች፤ አሁን ግን በነፍስ ገዳዮች የተሞላች ሆናለች።
ሆሴዕ 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናታቸው አመንዝራ ስለ ሆነች እነርሱን ባሳፋሪ መንገድ ፀንሳቸዋለች፤ እርስዋም ይህን ያደረገችው ምግቤንና ውሃዬን፥ የሱፍና የተልባ እግር ልብሴን፥ ዘይቴንና መጠጤን የሚሰጡኝ ስለ ሆነ ፍቅረኞቼን ተከትዬ እሄዳለሁ ብላ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናታቸው አመንዝራ ናት፤ በውርደትም ፀንሳቸዋለች፤ እርሷም፣ ‘እንጀራዬንና ውሃዬን ይሰጡኛል፤ ሱፌንና የሐር ልብሴን፣ ዘይቴንና መጠጤን ይሰጡኛል፤ ስለዚህ ውሽሞቼን ተከትዬ እሄዳለሁ’ አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለበለዚያ ዕራቁትዋን እንድትሆን እገፍፋታለሁ፥ እንደ ተወለደችበትም ቀን አደርጋታለሁ፥ እንደ ምድረ በዳና እንደ ደረቅ ምድር አደርጋታለሁ፥ በጥምም እገድላታለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናታቸው አመንዝራለችና፤ የወለደቻቸውም፥ “እንጀራዬንና ውኃዬን፥ ቀሚሴንና መደረቢያዬን፥ ዘይቴንና የሚገባኝን ሁሉ የሚሰጡኝ ወዳጆችን እከተላቸው ዘንድ እሄዳለሁ” ብላለችና አሳፈረቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕራቁትዋን እንዳልገፍፋት፥ እንደ ተወለደችበትም ቀን እንዳላደርጋት፥ እንደ ምድረ በዳና እንደ ደረቅ ምድር እንዳላደርጋት፥ |
ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት እንደ አመንዝራ ሆነች! ቀድሞ ፍትሕ የሰፈነባትና የጻድቃን መኖሪያ ነበረች፤ አሁን ግን በነፍስ ገዳዮች የተሞላች ሆናለች።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወንድ ሚስቱን ፈቶ እንደሚያባርር እኔ እናንተን ሕዝቤን ያባረርኩ ይመስላችኋልን? ይህስ ከሆነ የፍችው ደብዳቤ የት አለ? ሰው ልጆቹን ለባርነት እንደሚሸጥ እኔም እናንተን ለምርኮ አሳልፌ የሸጥኳችሁ ይመስላችኋልን? ከሆነስ ለማንኛውም አበዳሪዬ ሸጥኳችሁ? እናንተ ለምርኮ የተሰጣችሁት በኃጢአታችሁ ምክንያት ነው፤ የተሰደዳችሁትም በፈጸማችሁት በደል ነው።
የይሁዳ ሕዝብ ሆይ፥ በከተሞቻችሁ ልክ ብዙ አማልክት አሉአችሁ፤ በኢየሩሳሌምም መንገዶች ልክ አጸያፊ ለሆነው በዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ መሥዋዕት የምታቀርቡበት ብዙ መሠዊያዎችን ሠርታችኋል።
ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ለምንድነው? “ልብሴስ ተቀዶ የተደፈርኩት ስለምንድነው?” ብለሽ ብትጠይቂ፤ ይህ ሁሉ የደረሰብሽ ኃጢአትሽ እጅግ የከፋ በመሆኑ ምክንያት እንደ ሆነ ዕወቂ።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ሆይ! ከብዙ ጊዜ በፊት ለኔ መታዘዝና እኔን ማገልገል ትተሻል፤ በእርግጥም በተራራው ላይና በየዛፉ ጥላ ሥር ሌሎች አማልክትን በማምለክ አመንዝረሻል።
እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ይህ ሁሉ መከራ ማስጠንቀቂያ ይሁናችሁ፤ አለበለዚያ ከፊቴ አስወግዳችኋለሁ፤ ከተማችሁን ወደ ምድረ በዳ ለውጬ ማንም እንዳይኖርባት አደርጋለሁ።”
በሥልጣናቸው ሥር እንድትሆኚ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነርሱም መድረክሽንና ከፍተኛ ቦታዎችሽን ያፈራርሳሉ፤ ልብስሽን ገፈው ጌጣጌጥሽንም ወስደው ያራቊቱሻል፤ ባዶ እጅሽንም ያስቀሩሻል።
እግዚአብሔር በሆሴዕ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን ማስተላለፍ ሲጀምር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ሕዝቤ ከእኔ ተለይቶ አጸያፊ የሆነ የዝሙት ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፤ እንግዲህ አንተም ሂድና ዘማዊት ሴት አግባ፤ ከእርስዋም የዝሙት ልጆችን ውለድ።”
ልጆቼ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲያ እናታችሁ ሚስቴ ስላልሆነችና እኔም ባልዋ ስላልሆንኩ የዝሙት አመለካከትዋንና አመንዝራነትዋን እንድታስወግድ ውቀስዋት።
እርስዋ እህልን፥ የወይን ጠጅን፥ የወይራ ዘይትን የሰጠኋት፥ እኔ እንደ ሆንኩ ከቶ አልተገነዘበችም፤ እኔ ያበዛሁላትን ብርና ወርቅ “በዓል” ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት አቀረበች።
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “እስራኤላውያን ወደ ሌሎች አማልክት ሄደው የዘቢብ ጥፍጥፍ ማቅረብ ቢወዱ እንኳ ከዚሁ ጋር እግዚአብሔር ይወዳቸዋል፤ አንተም እንደዚሁ ፍቅረኛ ወደ አላት አመንዝራ ሴት ሄደህ ውደዳት።”
እናንተ ካህናት ሆይ! በቀን ብርሃን ትደናበራላችሁ፤ ነቢያትም ሌሊት ከእናንተ ጋር በጨለማ ይደናበራሉ፤ ስለዚህ እናት አገራችሁን አጠፋታለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤልን ባገኘሁ ጊዜ የወይን ዘለላን ከምድረ በዳ እንደ ማግኘት ነበር፤ የቀድሞ አባቶቻችሁን ባየሁ ጊዜ ቀድሞ የጐመራውን የበለስ ፍሬ እንደማየት ነበር፤ ወደ በዓል ጴዖር በደረሱ ጊዜ ግን ራሳቸውን ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ለይተው አቀረቡ፤ እነርሱም እንደዚያ እንደሚወዱት ጣዖት የረከሱ ሆኑ።
“በጠላታችን በሶምሶን ላይ ድልን እንድንቀዳጅ አድርጎናል” ብለው የደስታ በዓል ለማዘጋጀትና ለአምላካቸውም ለዳጎን ታላቅ መሥዋዕት ለማቅረብ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች በአንድነት ተሰበሰቡ፤