Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አሞጽ 8:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በዚያን ጊዜ ቆነጃጅት ልጃገረዶችና ጠንካራ ወንዶች ወጣቶች እንኳ ከመጠማት የተነሣ ይዝላሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “በዚያ ቀን፣ “ቈነጃጅት ሴቶችና ብርቱዎች ጕልማሶች፣ ከውሃ ጥም የተነሣ ይዝላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “በዚያ ቀን ቆነጃጅት ድንግሎችና ጉልማሶች በጥም ይዝላሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በዚያ ቀን መልከ መል​ካ​ሞቹ ደና​ግ​ልና ጐበ​ዛ​ዝቱ በጥም ይዝ​ላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በዚያ ቀን መልካካሞች ደናግል ጐበዛዝትም በጥም ይዝላሉ።

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 8:13
13 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደ ተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች።


ወጣቶች እንኳ ይደክማሉ፥ ይታክታሉም፤ ጐልማሶችም ዝለው ይወድቃሉ፤


ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ወጣቶቻቸውን ይቀጣል፤ ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶችና አሳዳጊ ለሌላቸው ለሙት ልጆቻቸው አይራራም፤ ሁሉም እያንዳንዱ ከሐዲና ክፉ አድራጊ ሆኖአል፤ ከእያንዳንዱም ሰው አንደበት የሚነገረው ቃል ተንኰል የሞላበት ነው፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ ገና አልበረደም፤ ስለዚህ እነርሱን ለመቅጣት እጁ እንደ ተቃጣ ነው።


ምሽጎችዋም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ የሚያደርግ ሞአብን የሚደመስሳት እነሆ እዚህ ስለ አለ፥ በዲቦን ከተማ የምትኖሩ ሁሉ ከክብር ቦታችሁ ወርዳችሁ በምድር ትቢያ ላይ ተቀመጡ፤


“በትእዛዙ ላይ ያመፅሁ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔር ባደረገው ነገር እውነተኛ ነው፤ እናንተ ሕዝቦች ሁሉ አድምጡ ሥቃዬንም ተመልከቱ፤ ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ተማርከው ተወስደዋል።


የኢየሩሳሌም ከተማ ሽማግሌዎች ጸጥ ብለው በምድር ላይ ተቀመጡ፤ እነርሱ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነስንሰው ማቅ ለበሱ፤ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፉ።


ወጣቶችና ሽማግሌዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ሞተው በየመንገዱ ዳር ወደቁ፤ ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች በጠላት ሰይፍ ተጨፈጨፉ፤ በቊጣህ ቀን ያለ ምሕረት እንዲታረዱ አደረግህ።


ባትመለስ ግን እንደ ተወለደችበት ቀን እርቃንዋን አስቀራታለሁ፤ እንደ ደረቀ ባዶ ምድር አደርጋታለሁ፤ በውሃ ጥምም እገድላታለሁ።


እናታቸው አመንዝራ ስለ ሆነች እነርሱን ባሳፋሪ መንገድ ፀንሳቸዋለች፤ እርስዋም ይህን ያደረገችው ምግቤንና ውሃዬን፥ የሱፍና የተልባ እግር ልብሴን፥ ዘይቴንና መጠጤን የሚሰጡኝ ስለ ሆነ ፍቅረኞቼን ተከትዬ እሄዳለሁ ብላ ነው።


የምድሪቱም መልካምነትና ውበት ምንኛ አስደናቂ ይሆናል! በእርስዋ የሚገኘው እህልና የወይን ጠጅ ወጣት ወንዶችና ሴቶችን ያለመልማቸዋል።


በየመንገዱ ላይ ጦርነት ልጅ አልባ ያደርጋቸዋል፤ በቤት ውስጥ ፍርሀት ይሰፍናል፤ ወጣት ወንዶችና ሴቶች፥ ሕፃናትና ሽማግሌዎችም ያልቃሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos