ሎጥ ይኖርባቸው የነበሩትን፥ በሸለቆ የሚገኙትን ከተሞች፥ እግዚአብሔር ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አስታወሰ፤ ስለዚህም ሎጥን ከጥፋት ወደሚድንበት ቦታ መራው።
ዘፍጥረት 8:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ፤ ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም መጒደል ጀመረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ኖኅንና በመርከቧ ውስጥ ከርሱ ጋራ የነበሩትን የዱርና የቤት እንስሳት ሁሉ ዐሰበ፤ በምድር ላይ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም ጐደለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ኖኅን፥ በመርከብም ከእርሱ ጋር የነበረውን አራዊቱን ሁሉ፥ እንስሳውንም ሁሉ፥ አዕዋፍንም ሁሉ፥ የሚንቀሳቀሰውንም ሁሉ ዐሰበ፤ እግዚአብሔርም በምድር ላይ ነፋስን አመጣ፤ ውኃውም ጐደለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ኖኅን፤ በመርከብም ከእርሱ ጋር የነበረውን አራዋቱን ሁሉ፤ እንስሳውንም ሁሉ አሰበ። |
ሎጥ ይኖርባቸው የነበሩትን፥ በሸለቆ የሚገኙትን ከተሞች፥ እግዚአብሔር ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አስታወሰ፤ ስለዚህም ሎጥን ከጥፋት ወደሚድንበት ቦታ መራው።
እንዲሁም ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሁሉ፥ ማለትም ከወፎች፥ ከእንስሶችና ከአራዊት፥ ከአንተ ጋር ከመርከቡ ውስጥ ከወጡት ፍጥረቶችና ዘሮቻቸው ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤
ሌዋውያኑም በሕጉ መሠረት ራሳቸውን አንጽተው የሰንበት ቀን በቅድስና የተጠበቀች መሆንዋን ለማረጋገጥ የቅጽር በሮቹን እንዲቈጣጠሩ አዘዝኳቸው። እግዚአብሔር ሆይ! ስለዚህም ሁሉ እንድታስበኝና ስለ ጽኑ ፍቅርህም እንድትታደገኝ እለምንሃለሁ።
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፥ ይህ ሕዝብ ክህነትን፥ የክህነትን ሥርዓትንና አንተ ከካህናትና ከሌዋውያን ጋር ያደረግኸውን ቃል ኪዳን እንዴት እንዳረከሰ ተመልከት!
መሥዋዕት የሚቃጠልበትን ማገዶ በተወሰነው ክፍለ ጊዜ ሁሉ ማቅረብ የሚቻልበትን ሁኔታ አደራጀሁ፤ ሰዎቹም ከሚሰበስቡት ሰብል ሁሉ ከእህሉም ሆነ ከፍራፍሬው በመጀመሪያ የደረሰውን እንዴት ማቅረብ እንደሚገባቸው አዘጋጀሁ። አምላኬ ሆይ! ይህን ሁሉ አስብ፤ ይህን በማድረጌም ቸርነት አድርግልኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ቀን ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፤ “እስከ መሠረትዋ አፈራርሳችሁ ጣሉአት!” እያሉ መጮኻቸውንም አስታውስ።
እግዚአብሔር ሆይ፥ ሰዎችንና እንስሶችን ከአደጋ ታድናለህ፤ ጽድቅህ እንደ ተራራዎች እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ፍርድህም እንደ ባሕር ጥልቅ ነው።
ሙሴ እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በብርቱ የምሥራቅ ነፋስ ባሕሩን ወደ ኋላ መለሰው፤ ነፋሱም ሌሊቱን ሙሉ በመንፈሱ፥ ባሕሩን ወደ ደረቅ ምድር ለወጠው፤ ውሃውም ከሁለት ተከፈለ፤
ነነዌ ክፉና ደጉን የማይለዩ ከአንድ መቶ ኻያ ሺህ ሕዝብ በላይ የሚኖሩባት ከተማ ነች፤ ብዙ እንስሶችም አሉባት፤ ታዲያ እኔ ለዚህች ታላቂቱ ከተማ አልራራምን?”
እግዚአብሔር ሆይ! ስላደረግኸው አስደናቂ ሥራ ሁሉ ሰምቼ እጅግ ፈራሁ፤ አሁንም በዘመናችን የቀድሞውን ሥራህን ደግመህ አድርግ፤ በየዘመናቱም እንዲታወቅ አድርግ፤ በምትቈጣበት ጊዜ እንኳ ምሕረትህን አታርቅ።
በመከራ ባሕር ውስጥ ሲያልፉ እኔ እግዚአብሔር ማዕበሉን እመታለሁ፤ ጥልቅ የሆነውም የዓባይ ወንዝ ይደርቃል፤ ትዕቢተኛይቱ አሦር ትዋረዳለች፤ ግብጽም በትረ መንግሥትዋን ታጣለች።
“በአገራችሁ ላይ ጦርነት አንሥቶ አደጋ የጣለባችሁን ጠላት ለመከላከል ስትሄዱ በእኔ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ዘንድ እንድትታወሱ በመለከቶቻችሁ የማስጠንቀቂያ ድምፅ ንፉ፤ እኔ አምላካችሁም አድናችኋለሁ።
መልአኩም እንዲህ አለው፤ “አህያህን እንዲህ አድርገህ ሦስት ጊዜ የመታሃት ለምንድን ነው? እኔ መጥቼ መንገድህን የዘጋሁት በጥፋት ጐዳና እንዳትሄድ ልከለክልህ ብዬ ነው፤
ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የአሕዛብ ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔር ታላቂቱን ባቢሎንን አስታወሰ፤ የብርቱ ቊጣው ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ እንድትጠጣም አደረጋት።
በማግስቱም ሕልቃናና ቤተሰቡ በማለዳ ተነሥተው ለእግዚአብሔር ከሰገዱ በኋላ በራማ ወደሚገኘው ቤታቸው ሄዱ፤ ሕልቃናም ከሚስቱ ከሐና ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እግዚአብሔርም አስታወሳት፤