Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


የዳዊት መዝሙር የእግዚአብሔር የድምፁ ኀይል

1 እናንተ የሰማይ መላእክት ሁሉ፥ ክብርና ኀይል የእግዚአብሔር ነው በሉ።

2 ክብር ለእግዚአብሔር መሆኑን ግለጡ፤ በቅድስናና በግርማ ሞገስ ለተመላ አምላክ ስገዱ።

3 የእግዚአብሔር ድምፅ በውቅያኖሶች ላይ ያስተጋባል፤ የክብር አምላክ እግዚአብሔር ከሚናወጠው ማዕበል በላይ ያንጐደጒዳል።

4 የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ ድምፁም ባለ ግርማ ነው።

5 የእግዚአብሔር ድምፅ የሊባኖስን ዛፍ ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዛፍ ይሰብራል።

6 የሊባኖስን ተራራዎች እንደ እንቦሳ እንዲፈነጩ ያደርጋቸዋል፤ የስርዮንንም ተራራ እንደ ጐሽ ጥጃ እንዲዘል ያደርገዋል።

7 የእግዚአብሔር ድምፅ መብረቅን ብልጭ ያደርጋል።

8 የእግዚአብሔር ድምፅ በረሓን ያናውጣል፤ የቃዴስንም በረሓ ያንቀጠቅጣል፤

9 የእግዚአብሔር ድምፅ አጋዘንን እንድትወልድ ያደርጋል የዛፎችን ቅጠል ያረግፋል፤ በመቅደሱም ያሉ ድምፁን ሲሰሙ “ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!” ይላሉ።

10 እግዚአብሔር የጥልቁ ባሕር ገዢ ነው፤ በንጉሥነቱም ለዘለዓለም ይገዛል።

11 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይልን ይሰጣል፤ በሰላም ይባርካቸዋል።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos