ዘፍጥረት 37:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱ ግን “ለልጄ እያለቀስሁ ወደ ሙታን ዓለም እወርዳለሁ” በማለት መጽናናትን እምቢ አለ። ስለዚህ ስለ ልጁ ማዘኑን ቀጠለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጽናና ባለመቻሉ “በሐዘን እንደ ተኰራመትሁ ልጄ ወዳለበት መቃብር እወርዳለሁ” አለ። ስለ ልጁም አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፥ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ “ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም እንደዚህ ስለ እርሱ አለቀሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰብስበው መጡ። ኀዘኑንም ያስተዉት ዘንድ አባታቸውን ማለዱት። ኀዘኑንም መተውን እንቢ አለ፥ እንዲህም አላቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃብር እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም ስለ እርሱ አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንዶች ልጆቹም ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሠ መጽናናትን እንቢ አለ እንዲህም አለ፦ ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ። አባቱም ስለ እርሱ አለቀሰ። |
ላባም ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “እነዚህ ሴቶች የእኔ ልጆች ናቸው፤ ልጆቻቸውም የእኔው ናቸው፤ እነዚህም መንጋዎች የእኔ ናቸው፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ የምታየው ሁሉ የራሴ ነው፤ ነገር ግን ልጆቼንም ሆነ ልጆቻቸውን ለማስቀረት ምንም ማድረግ አልቻልኩም፤
ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጒዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው።
የቤተ መንግሥቱ ባለሟሎች ወደ እርሱ ቀርበው ከመሬት ላይ ሊያስነሡት ሞከሩ፤ እርሱ ግን ከመሬት ላለመነሣትና ከእነርሱም ጋር ምንም ነገር ላለመቅመስ ወሰነ፤
አሁን ግን ከሞተ በኋላ ስለምን እጾማለሁ? ሕፃኑን እንደገና በሕይወት እንዲኖር ማድረግ ይቻለኛልን? እኔ አንድ ቀን ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ ተመልሶ አይመጣም።”
የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ፥ የሹሐ አገር ሰው የሆነው ቢልዳድና የናዕማ አገር ሰው የሆነው ጾፋር፥ እነዚህ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ነበሩ። እነርሱም በኢዮብ ላይ የደረሰውን ሥቃይ በሰሙ ጊዜ ሐዘናቸውን ሊገልጹለትና ሊያጽናኑት ከየአገራቸው ተጠራርተው በአንድነት ወደ ኢዮብ መጡ።
በችግር ጊዜ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ሌሊቱን ሙሉ ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ይሁን እንጂ ለመጽናናት አልቻልኩም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ ታለቅሳለች፤ ልጆችዋ በሕይወት ስለሌሉ መጽናናትን እምቢ አለች።