Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 37:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ወን​ዶች ልጆ​ቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ። ኀዘ​ኑ​ንም ያስ​ተ​ዉት ዘንድ አባ​ታ​ቸ​ውን ማለ​ዱት። ኀዘ​ኑ​ንም መተ​ውን እንቢ አለ፥ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃ​ብር እያ​ዘ​ንሁ እወ​ር​ዳ​ለሁ።” አባ​ቱም ስለ እርሱ አለ​ቀሰ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጽናና ባለመቻሉ “በሐዘን እንደ ተኰራመትሁ ልጄ ወዳለበት መቃብር እወርዳለሁ” አለ። ስለ ልጁም አለቀሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፥ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ “ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም እንደዚህ ስለ እርሱ አለቀሰ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱ ግን “ለልጄ እያለቀስሁ ወደ ሙታን ዓለም እወርዳለሁ” በማለት መጽናናትን እምቢ አለ። ስለዚህ ስለ ልጁ ማዘኑን ቀጠለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ወንዶች ልጆቹም ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሠ መጽናናትን እንቢ አለ እንዲህም አለ፦ ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ። አባቱም ስለ እርሱ አለቀሰ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 37:35
18 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም መል​ካም ሽም​ግ​ል​ናን ሸም​ግሎ፥ ዘመ​ኑ​ንም ፈጽሞ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።


ላባም ለያ​ዕ​ቆብ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ለት፥ “ሴቶቹ ልጆች ልጆች ናቸው፤ ወን​ዶ​ቹም ልጆች ልጆች ናቸው፤ መን​ጎ​ቹም ከብ​ቶች ናቸው፤ ይህ የም​ታ​የው ሁሉ የእኔ ነው፤ የል​ጆ​ችም ሀብት ነው፤ ዛሬም በእ​ነ​ዚህ በሴ​ቶች ልጆ​ችና በወ​ለ​ዱ​አ​ቸው ልጆ​ቻ​ቸው ላይ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ?


ይስ​ሐ​ቅም ሸም​ግሎ ዕድ​ሜ​ንም ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ፤ ልጆ​ቹም ዔሳ​ውና ያዕ​ቆብ ቀበ​ሩት።


እኛም እን​ዲህ አል​ነው፥ “ሰላ​ማ​ው​ያን ሰዎች ነን እንጂ ሰላ​ዮች አይ​ደ​ለ​ንም፤


እር​ሱም አለ፥ “ልጄ ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ወ​ር​ድም፤ ወን​ድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀር​ቶ​አ​ልና፤ በም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ ምና​ል​ባት ክፉ ነገር ቢያ​ገ​ኘው ሽም​ግ​ል​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።”


እስ​ራ​ኤ​ልም፥ “ልጄ ዮሴፍ ገና በሕ​ይ​ወት ከሆነ ይህ ለእኔ ታላቅ ነገር ነው፤ ሳል​ሞት እን​ዳ​የው እሄ​ዳ​ለሁ” አለ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ከፊ​ትህ አል​ተ​ለ​የ​ሁም፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር​ህን ደግሞ አሳ​የኝ” አለው።


የቤ​ቱም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተነ​ሥ​ተው ከም​ድር ያነ​ሡት ዘንድ በአ​ጠ​ገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር እን​ጀራ አል​በ​ላም።


አሁን ግን ሞቶ​አል፤ የም​ጾ​መው ስለ ምን​ድን ነው? በውኑ እን​ግ​ዲህ እመ​ል​ሰው ዘንድ ይቻ​ለ​ኛ​ልን? እኔ ወደ እርሱ እሄ​ዳ​ለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይ​መ​ለ​ስም” አለ።


ለኢ​ዮ​አብ፥ “ንጉሡ ስለ አቤ​ሴ​ሎም ያዝ​ናል፤ ያለ​ቅ​ሳ​ልም” ብለው ነገ​ሩት።


አባ​ታ​ቸው ኤፍ​ሬ​ምም ብዙ ቀን አለ​ቀሰ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም ሊያ​ጽ​ና​ኑት መጡ።


ሦስ​ቱም የኢ​ዮብ ወዳ​ጆች ይህን የደ​ረ​ሰ​በ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰም​ተው ከየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነ​ር​ሱም ቴማ​ና​ዊው ንጉሥ ኤል​ፋዝ፥ አው​ኬ​ና​ዊው መስ​ፍን በል​ዳ​ዶስ፥ አሜ​ና​ዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነ​ር​ሱም ሊጐ​በ​ኙ​ትና ሊያ​ጽ​ና​ኑት በአ​ን​ድ​ነት ወደ እርሱ መጡ።


አፌን በም​ሳሌ እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ከቀ​ድሞ ጀምሮ ያለ​ው​ንም ምሳሌ እና​ገ​ራ​ለሁ።


የሰ​ማ​ነ​ው​ንና ያየ​ነ​ውን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የነ​ገ​ሩ​ንን፥ ለሚ​መጣ ትው​ልድ ከል​ጆ​ቻ​ቸው አል​ሰ​ወ​ሩም።


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የኀ​ዘን፥ የል​ቅ​ሶና የጩ​ኸት ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆ​ችዋ አለ​ቀ​ሰች፤ የሉ​ምና ስለ ልጆ​ችዋ መጽ​ና​ና​ትን እንቢ አለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos