እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ።
ዘፍጥረት 13:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ ለዘለዓለምም የእናንተ ይሆናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐይንህ የሚያየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘለዓለም እሰጣለሁና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘለዓለም እሰጣለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና። |
እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ።
በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
ደግሞም እግዚአብሔር አብራምን “ይህችን አገር በውርስ ለአንተ እንድሰጥህ ዑር ከምትባለው ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው።
ከአባቴ ቤትና ከትውልድ አገሬ አውጥቶ ይህን ምድር ለዘሬ እንደሚሰጥ በመሐላ ቃል የገባልኝ እግዚአብሔር፥ የሰማይ አምላክ ከዚያ ለልጄ ሚስት ማግኘት እንድትችል መልአኩን በፊትህ ይልካል።
እግዚአብሔርም በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአንተና ለትውልድህ እንዲሆን ይህን የተኛህበትን ምድር እሰጥሃለሁ፤
አብርሃምን እንደ ባረከ አንተንና ዘርህን ይባርክ! ይህንንም ለአብርሃም ሰጥቶት የነበረውንና አንተም ስደተኛ ሆነህ የኖርክበትን ምድር ርስት አድርጎ ይስጥህ!”
ደግሞም ‘ዘርህን አበዛለሁ፤ ተወላጆችህም ብዙ ሕዝቦች ይሆናሉ፤ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህ ለዘለዓለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ’ አለኝ።”
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እናንተን ግን እግዚአብሔር በረድኤት ይጐበኛችኋል፤ ከዚህም አገር አውጥቶ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በመሐላ ቃል ወደ ገባላቸው ምድር ይመልሳችኋል።
አንተ አምላካችን ነህ፤ ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህች ምድር በገባ ጊዜ ቀደም ሲል በዚህ ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አስወጥተህ ወዳጅህ ለነበረው ለአብርሃም ዘሮች ምድሪቱን የሰጠህ አንተ ነህ፤
አገልጋዮችህን አብርሃምን፥ ይስሐቅንና ያዕቆብን አስብ፤ ዘራቸውን እንደ ሰማይ ከዋክብት ልታበዛውና የተስፋይቱንም ምድር ርስት ለዘለዓለም አድርገህ ልትሰጣቸው በመሐላ የገባህላቸውንም ቃል ኪዳን አስብ።”
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተና ከግብጽ ምድር መርተህ ያወጣኻቸው ሕዝብ ሁሉ ከዚህ ሰፈር ተነሥታችሁ፥ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለተወላጆቻቸው ጭምር ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር ሂዱ።
ይሁን እንጂ የእግር ማሳረፊያ እንኳ የሚያኽል ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን ይህችን አገር ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ርስት አድርጎ እንደሚሰጠው ቃል ገብቶለት ነበር፤ ይህን ቃል የገባለትም አብርሃም ገና ልጅ ሳይኖረው ነበር።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለዘሮቻቸው አወርሳት ዘንድ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው የተስፋ ምድር ይህች ናት፤ እነሆ፥ እርስዋን በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ወደዚያች መግባት ግን አይፈቀድልህም።”
እግዚአብሔር የእነርሱን ምድር እንድትወርስ የፈቀደልህ አንተ ደግ በመሆንህና ትክክለኛውን ነገር በማድረግህ አይደለም፤ እርሱ እነርሱን ነቃቅሎ የሚያባርርበት ምክንያት እነርሱ ክፉዎች ስለ ሆኑና እንዲሁም ለቀድሞ አባቶችህ፥ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ለመጠበቅ ሲል ነው።