29 ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእርስዋም ለዘለዓለም ይኖራሉ።
29 ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በርሷም ለዘላለም ይኖራሉ።
29 ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፥ በእርሷም ለዘለዓለም ይኖራሉ።
ዘወትር በብልጽግና ይኖራሉ፤ ልጆቻቸውም ምድርን ይወርሳሉ።
ትሑቶች ምድርን ይወርሳሉ፤ ብልጽግናንና ሰላምን በማግኘት ይደሰታሉ።
እግዚአብሔር ታዛዦቹን በየቀኑ ይጠብቃቸዋል፤ የሰጣቸውም ስጦታ ለዘለዓለም ከእነርሱ ጋር ይኖራል።
ከክፉ ነገር ራቅ፤ መልካም ነገርንም አድርግ፤ አንተም በሰላም ለዘለዓለም ትኖራለህ።
ክፉ አድራጊዎች ይገደላሉ፤ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ግን ምድርን ይወርሳሉ።
በዚህች ምድር መኖር የሚችሉት ልበ ቅኖችና ደጋግ ሰዎች ናቸው።
ርዳታ ለማግኘት በምትጮኹበት ጊዜ እስቲ የሰበሰባችኋቸው ጣዖቶቻችሁ ያድኑአችሁ! እነርሱን የነፋስ ሽውታ ያስወግዳቸዋል፤ እስትንፋስም ይወስዳቸዋል፤ በእኔ የሚተማመን ግን ምድሪቱ የእርሱ ትሆናለች፤ የተቀደሰ ተራራዬንም ርስት ያደርጋል።”
ሕዝብሽ ጻድቃን ይሆናሉ፤ ምድሪቱን ለዘለዓለም ይወርሳሉ፤ እኔ እመሰገን ዘንድ እነርሱን የፈጠርኳቸውና የተካኋቸው እኔ ነኝ።
አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፤ ለእርሱም ታዛዥ ሁን፤ በእርሱም እመን፤ ይህም ለአንተ ሕይወት ከመሆኑም በላይ ለቀድሞ አባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል በገባላቸው መሠረት ገብተህ በምትኖርባት ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራለህ።”
ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ እንዲከናወንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ለረጅም ዘመናት እንድትኖሩ፥ እግዚአብሔር ያዘዛችሁን ሁሉ ፈጽሙ።
ነገር ግን እኛ በሰጠን ተስፋ መሠረት የጽድቅ ሥራ የሚመሠረትበትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንጠባበቃለን።
ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል፤ እኔ አምላክ እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል፤