በግብጽ ንጉሥ ላይ በባለሥልጣኖቹና በምድሩ በሚኖሩትም ሕዝብ ሁሉ ላይ ድንቅ ተአምራትን ገልጠህ አሳየህ። ይህንንም ያደረግኸው የቀድሞ አባቶቻችን እንዴት እንደሚጨቈኑ በማየትህ ነው፤ ይህንንም በማድረግህ እስከ ዛሬ ድረስ ዝናህ የገነነ ሆኖአል።
ዘፀአት 7:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እኔ የንጉሡን ልብ አደነድናለሁ፤ ከዚህም የተነሣ እኔ የቱንም ያኽል ምልክቶችንና ተአምራትን በግብጽ ምድር ባደርግ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ግን የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ፤ ታምራዊ ምልክቶችንና ድንቆችን በግብጽ ላይ በብዛት ባደርግም እንኳ፣ አይሰማችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ፥ ምልክቶቼንና ድንቆቼን በግብጽ ምድር ላይ አበዛለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፤ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፤ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ። |
በግብጽ ንጉሥ ላይ በባለሥልጣኖቹና በምድሩ በሚኖሩትም ሕዝብ ሁሉ ላይ ድንቅ ተአምራትን ገልጠህ አሳየህ። ይህንንም ያደረግኸው የቀድሞ አባቶቻችን እንዴት እንደሚጨቈኑ በማየትህ ነው፤ ይህንንም በማድረግህ እስከ ዛሬ ድረስ ዝናህ የገነነ ሆኖአል።
ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራት በንጉሡ ፊት አደረጉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ ስላደነደነ እስራኤላውያን ከምድሪቱ እንዲወጡ አልፈቀደላቸውም።
እኔም ልቡን ስለማደነድነው ያሳድዳችኋል፤ ስለዚህም በንጉሡና በሠራዊቱ ላይ የምጐናጸፈው ድል ለእኔ ክብር ይሆናል፤ በዚያን ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” እስራኤላውያንም እንደ ተነገራቸው አደረጉ።
ስለዚህም እጅግ አስፈሪ የሆኑ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የኀይል ክንዴን ዘርግቼ ግብጻውያንን እቀጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ እንድትወጡ ይፈቅድላችኋል።
እንደገናም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ አሁን ወደ ግብጽ መመለስህ ስለ ሆነ፥ በሰጠሁህ ኀይል የምታደርጋቸውን ተአምራት በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ፤ ሆኖም እኔ የፈርዖንን ልብ ስለማደነድን ሕዝቡን በቀላሉ አይለቅም።
እግዚአብሔርም “እጅህን እንደገና ወደ ብብትህ አስገባ” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ብብቱ አስገባ፤ መልሶም ባወጣው ጊዜ ተመልሶ እነሆ፥ እንደ ሌላው ሰውነቱ ጤናማ ሆነ።
እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።
“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! ይህን ቃል አዳምጡ፤ እናንተ ራሳችሁ እንደምታውቁት የናዝሬቱ የኢየሱስ ማንነት እግዚአብሔር በእናንተ መካከል በእርሱ አማካይነት በፈጸማቸው ታላላቅ ሥራዎች፥ ተአምራትና ምልክቶች ተረጋግጦአል።
እንዲሁም በታላላቅ ተአምራትና በድንቅ ሥራዎች፥ በመንፈስ ቅዱስም ኀይል ከኢየሩሳሌምና ከአካባቢዋ ጀምሮ እስከ እልዋሪቆን ድረስ የክርስቶስን ወንጌል አስተምሬአለሁ።
ወይስ በፈተና፥ በተአምራትና በድንቅ ነገሮች፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራ ኀይል፥ በዐይናችሁ እያያችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ ያለ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?
በገዛ ዐይኖችህ ያየሃቸውን ታላላቅ መቅሠፍቶች፥ ተአምራትንና ድንቅ ሥራዎችን፥ እንዲሁም እግዚአብሔር አምላክህ አንተን ነጻ ያወጣበትን ታላቅ ኀይሉንና ሥልጣኑን አስታውስ፤ ግብጻውያንን ባጠፋበት ዐይነት ዛሬ አንተ የምትፈራቸውን እነዚህንም ሕዝቦች ሁሉ ያጠፋቸዋል።