እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር ቃል ኪዳን የገባበት የድንጋይ ጽላት ለሚገኝበትም ታቦት ማኖሪያ የሚሆን ቦታ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አዘጋጅቼአለሁ።”
ዘፀአት 24:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሙሴ በገበቴ ያለውን ደም ወስዶ በሕዝቡ ላይ በመርጨት “ይህ እንግዲህ እግዚአብሔር እነዚህን ሁሉ ትእዛዞች በሰጣችሁ ጊዜ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን የሚያጸናበት ደም ነው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴ ደሙን ወሰደ፤ ሕዝቡም ላይ ረጭቶ፣ “ይህ እነዚህን ቃሎች በሰጠ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ የገባው የኪዳኑ ደም ይህ ነው” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ደሙን ውስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፦ “በእነዚህ ቃሎች ሁሉ ጌታ ከእናንተ ጋር ያደረገው የኪዳኑ ደም እነሆ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፤ በዚህ ቃል ሁሉ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ያደረገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ደሙን ውስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፦ በዚህ ቃል ሁሉ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ያደረገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ አለ። |
እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር ቃል ኪዳን የገባበት የድንጋይ ጽላት ለሚገኝበትም ታቦት ማኖሪያ የሚሆን ቦታ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አዘጋጅቼአለሁ።”
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር እንደ ወጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ ሙሴ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ካኖራቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።
ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።”
ይህም ቃል ኪዳን እነርሱን ከግብጽ ለማውጣት እጃቸውን በያዝኩ ጊዜ እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እኔ አምላካቸው ብሆንም እንኳ እነርሱ ቃል ኪዳኔን አልጠበቁም፤ እኔም ችላ አልኳቸው፤
“እንደገናም በአጠገብሽ ሳልፍ ጊዜሽ የፍቅር ዕድሜ ነበር፤ የተራቈተውን ሰውነትሽንም በመጐናጸፊያዬ ሸፍኜ ቃል ገባሁልሽ፤ ከአንቺም ጋር እንደ ጋብቻ ያለ ቃል ኪዳን ገብቼ የእኔ የግሌ አደረግሁሽ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።
ሙሴ ከቅባት ዘይት ጥቂት እና በመሠዊያው ላይ ከነበረውም ከደሙ ጥቂት ወስዶ በአሮንና በልጆቹ እንዲሁም በልብሳቸው ሁሉ ላይ ረጨው፤ በዚህም ሁኔታ ሙሴ እነርሱንና ልብሶቻቸውን ለእግዚአብሔር የተለዩ አደረገ።
ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ ‘እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ’ ብዬ በሰጠሁት የተስፋ ቃል መሠረት አሁንም መንፈሴ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነ አይዞአችሁ አትፍሩ” ብሎ ነገራቸው።
እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሠረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።
ታዲያ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፥ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳን ደም ያረከሰ፥ የጸጋን መንፈስ የሰደበ፥ እንዴት ያለ የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል!
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ በዐቀደው መሠረት ለተመረጣችሁት፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመታዘዝና በደሙ ተረጭታችሁ ለመንጻት በመንፈስ ቅዱስ ለተቀደሳችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።