Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 31:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ይህም ቃል ኪዳን እነርሱን ከግብጽ ለማውጣት እጃቸውን በያዝኩ ጊዜ እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እኔ አምላካቸው ብሆንም እንኳ እነርሱ ቃል ኪዳኔን አልጠበቁም፤ እኔም ችላ አልኳቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ከግብጽ አወጣቸው ዘንድ፣ እጃቸውን ይዤ በመራኋቸው ጊዜ፣ ከአባቶቻቸው ጋራ እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ የእነርሱ ባል ሆኜ ሳለሁ፣ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና።” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 እጃቸውን ይዤ ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ አደረግሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እኔ ገዢአቸው ብሆንም እንኳ ያን ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጃ​ቸ​ውን በያ​ዝ​ሁ​በት ቀን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር እንደ ገባ​ሁት ያለ ቃል ኪዳን አይ​ደ​ለም፤ እነ​ርሱ በኪ​ዳኔ አል​ጸ​ኑ​ምና፥ እኔም ቸል አል​ኋ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፥ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 31:32
43 Referencias Cruzadas  

ቃል ኪዳን ያደረገውም ከአባቶቻችን ጋር ብቻ ሳይሆን፥ አሁን በሕይወት ካለነውም ከእኛ ሁሉ ጋር ነው።


እናንተ ወደዚህ ቦታ እስክትመጡ ድረስ አንድ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምድረ በዳው እንደ ተንከባከባችሁ አይታችኋል።’


አሁንም እነሆ፥ ለእኔ ብትታዘዙና ቃል ኪዳኔንም ብትጠብቁ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆን የተለያችሁ ሕዝብ ትሆናላችሁ፤


“እንደገናም በአጠገብሽ ሳልፍ ጊዜሽ የፍቅር ዕድሜ ነበር፤ የተራቈተውን ሰውነትሽንም በመጐናጸፊያዬ ሸፍኜ ቃል ገባሁልሽ፤ ከአንቺም ጋር እንደ ጋብቻ ያለ ቃል ኪዳን ገብቼ የእኔ የግሌ አደረግሁሽ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


ሙሽሪት ያለችው ሰው ሙሽራ ነው፤ የሙሽራው ሚዜ ግን ከሙሽራው አጠገብ ቆሞ ይሰማዋል፤ የእርሱንም ድምፅ በመስማት ይደሰታል፤ ስለዚህ የእኔም ደስታ ይህ ነው፤ እርሱም አሁን ፍጹም ሆኖአል።


እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “እስራኤላውያን ወደ ሌሎች አማልክት ሄደው የዘቢብ ጥፍጥፍ ማቅረብ ቢወዱ እንኳ ከዚሁ ጋር እግዚአብሔር ይወዳቸዋል፤ አንተም እንደዚሁ ፍቅረኛ ወደ አላት አመንዝራ ሴት ሄደህ ውደዳት።”


“እናንተ እምነት የማይጣልባችሁ ሕዝብ ሆይ! የእኔ ስለ ሆናችሁ ተመለሱ፤ ከእናንተ መካከል ከየአንዳንዱ ከተማ አንዳንድ፥ ከእያንዳንዱም ቤተሰብ ሁለት ሁለት መርጬ ወደ ጽዮን ተራራ አመጣችኋለሁ።


ትእዛዞቼን ባትጠብቁ፥ ሕግጋቴን ብትንቁ፥ ቃል ኪዳኔን ብታፈርሱና ሥርዓቶቼን ብትጸየፉ፥


ይህም ቃል ኪዳን እጃቸውን ይዤ ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እነርሱ በቃል ኪዳኔ ስላልጸኑ እኔም ችላ አልኳቸው ይላል ጌታ።


እንደ አንዲት ንጽሕት ልጃገረድ በድንግልናዋ ለአንድ ባል እንደምትታጭ እኔም እናንተን ለክርስቶስ ስላአጨኋችሁ ስለ እናንተ መንፈሳዊ ቅናት እቀናለሁ።


እርሱም ማየት የተሳነውን ሰው እጅ ይዞ እየመራ ከመንደር ወደ ውጪ አወጣው፤ በሰውየውም ዐይኖች ላይ ምራቁን እንትፍ ብሎ እጁን ጫነበትና “አንዳች ነገር ታያለህን?” ሲል ጠየቀው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን እስራኤልን ገና በሕፃንነቱ ወደድኩት፤ ልጄን ከግብጽ ጠራሁት።


ልጆቼ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲያ እናታችሁ ሚስቴ ስላልሆነችና እኔም ባልዋ ስላልሆንኩ የዝሙት አመለካከትዋንና አመንዝራነትዋን እንድታስወግድ ውቀስዋት።


ከእነርሱም ታላቂቱ ኦሆላ ትባል ነበር፤ እርስዋም ሰማርያ ነች፤ ታናሽቱ ደግሞ ኦሆሊባ ትባል ነበር እርስዋም ኢየሩሳሌም ነች፤ እኔ ሁለቱንም አግብቼ ልጆች ወለዱልኝ።


“ከሥልጣኔ ሥር አደርጋችኋለሁ፤ ወደ ቃል ኪዳኔ ግዴታም አመጣችኋለሁ።


በዚያም ቃል ኪዳን መሠረት፥ ዕብራውያን ባሪያዎች ያሉአቸው ሁሉ ስድስት ዓመት ካገለገሉአቸው በኋላ በሰባተኛው ዓመት ነጻ እንዲያወጡአቸው አዘዝኩ፤ ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችሁ ሊታዘዙኝም ሆነ ቃሌን ሊሰሙ አልፈለጉም፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ አምላክ የምሆንበትና እነርሱም ሕዝቤ የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል፤


እናንተ ከእኔ ከአምላካችሁ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን አፍርሳችሁ ባዕዳን አማልክትን በማምለካችሁና በማገልገላችሁ ምክንያት መሆኑንም ይረዳሉ።”


“ሂድና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በመጀመሪያ በምድረ በዳ ምንም በማያበቅልበት ትከተሉኝ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ሙሽራይቱ ለሙሽራው የምታሳየውን ፍቅርና ታማኝነት ለኔም ታሳይ እንደ ነበረ አስታውሳለሁ።


ይህም የሚሆነው ፈጣሪሽ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንደ ባልሽ ስለሚሆንና ‘የምድር ሁሉ አምላክ’ ተብሎ የሚጠራው የእስራኤል ቅዱስ አዳኝሽ ስለ ሆነ ነው።


‘አይዞህ አትፍራ፥ አትደንግጥ፥ ቀኝ እጅህን ይዤ እረዳሃለሁ’ እያልኩ የማበረታታህ፥ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።”


ሰዎች ሕጎችን በመጣስ፥ ደንብን በመተላለፍና ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በማፍረስ ምድርን አርክሰዋል።


በወዳጅዋ ትከሻ ላይ ደገፍ ብላ ከበረሓ የምትመጣ ይህች ማን ናት? ዱሮ እናትህ አንተን አምጣ በወለደችበት በፖም ዛፍ ሥር ቀስቅሼ አስነሣሁህ።


ነገር ግን ዘወትር ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤ አንተም ቀኝ እጄን ትይዛለህ።


የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር እንደ ወጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ ሙሴ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ካኖራቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተ በቅርብ ጊዜ እንደ ቀድሞ አባቶችህ ትሞታለህ፤ ከዚያ በኋላ ይህ ሕዝብ ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳል። እኔንም በመተው በሚወርሰው ምድር የሚገኙትን ጣዖቶች ያመልካል።


እግዚአብሔር በሲና ካደረገው ቃል ኪዳን በተጨማሪ በሞአብ ምድር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር እንዲያደርግ ሙሴን ያዘዘው ተጨማሪ ቃል ኪዳን የሚከተለው ነው፦


እግዚአብሔር እንደዚህ ያለውን ሰው በዚህ የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው የእርግማን ቃል ኪዳን መሠረት ከእስራኤል ነገዶች መካከል አውጥቶ ያጠፋዋል።


እግዚአብሔር አምላካችን በሲና ተራራ ላይ ቃል ኪዳን አደረገ፤


ይህ ቃል ኪዳን እንደ ጋለ ምድጃ ከሆነችባቸው አገር ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ ለቀድሞ አባቶቻችሁ የሰጠሁት ነው፤ ለእኔ እንዲታዘዙና እኔ የምላቸውን ሁሉ እንዲፈጽሙ ነገርኳቸው፤ የሚታዘዙኝም ከሆነ እነርሱ ሕዝቤ እንደሚሆኑና እኔም አምላካቸው እንደምሆን ገለጥኩላቸው።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ራሴ የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር፥ ከባርነት ቤት ነጻ ባወጣኋቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር እንዲህ ስል ቃል ኪዳን ገብቼ ነበር።


እነርሱ እንዲከተሉት ካዘዝኳቸው መንገድ ወዲያውኑ ወጥተዋል፤ ከቀለጠ ወርቅ ጥጃ ሠርተውም ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለት ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን አምላካችን ይህ ነው’ ብለዋል።


በዚያን ጊዜ የመላው ዓለም ሕዝብ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፤ ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ ይህን ሁሉ ስለምን አደረገ? ለብርቱ ቊጣውስ ምክንያት የሆነው ነገር ምንድን ነው?’


ለቀድሞ አባቶቻቸው በመሐላ ቃል ኪዳን በገባሁላቸው መሠረት በማርና በወተት ወደ በለጸገችው ምድር አስገባቸዋለሁ፤ በዚያም በልተው በጠገቡና በወፈሩ ጊዜ እኔን ይተዋሉ፤ ቃል ኪዳኔንም አፍርሰው ሌሎች አማልክትን ያመልካሉ።


ለእርሱ ታማኞች አልነበሩም፤ የእርሱንም ቃል ኪዳን አላከበሩም።


ይህን ቃል ኪዳን የማይታዘዝ ሁሉ የተረገመ ይሁን።


አዛዡም የልጁን እጅ ይዞ ገለል አደረገውና “የምትነግረኝ ነገር ምንድን ነው?” ሲል ለብቻው ጠየቀው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios