አሞጽ 8:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መንግሥት የሚያሰሙት ዘፈን በዚያን ቀን ወደ ለቅሶ ይለወጣል፤ የብዙ ሰው ሬሳ በየቦታው ወድቆ ይገኛል፤ በዝምታም በየስፍራው ይጣላል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር፣ “በዚያ ቀን የቤተ መቅደሱ ዝማሬ ወደ ዋይታ ይለወጣል፤ እጅግ ብዙ የሆነ የሰው ሬሳ ወድቆ ይገኛል፤ ዝምታም ይሰፍናል” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን የመቅደሱ ዝማሬ ዋይታ ይሆናል፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ “የሰዎችም ሬሳ ይበዛል፥ በየስፍራውም ሁሉ በዝምታ ይጣላል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜም በመቅደሶቻቸው ዋይ ዋይ ይላሉ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በየስፍራው የሚወድቀው ሬሳ ይበዛልና፤ እነርሱም ይጠፋሉና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመቅደሱ ዝማሬ በዚያ ቀን ዋይታ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ የሰዎችም ሬሳ ይበዛል፥ በስፍራውም ሁሉ በዝምታ ይጣላል። |
በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም የሚለው ይህ ነው፥ “እርሱ በሚሞትበት ጊዜ ‘ዋይ! ወዮ! ወንድሜ ሆይ!’ እያሉ በማልቀስ አያዝኑለትም፤ እንዲሁም ‘ጌታዬ ሆይ! ንጉሤ ሆይ! ወዮ!’ እያለ የሚያለቅስለት አይኖርም።
የኢየሩሳሌም ከተማ ሽማግሌዎች ጸጥ ብለው በምድር ላይ ተቀመጡ፤ እነርሱ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነስንሰው ማቅ ለበሱ፤ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፉ።
ለአምላካችሁ የምታቀርቡት የእህልም ሆነ የወይን ጠጅ መባ ስለሌለ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች የሆናችሁ ካህናት! ኑና ማቅ ለብሳችሁ ሌሊቱን ሁሉ አልቅሱ! እናንተም በመሠዊያው ላይ የምታገለግሉ ዋይ! ዋይ! በሉ።
ከእንግዲህ ወዲህ አዲስ የወይን ጠጅ በአፋችሁ ስለማትቀምሱ፥ እናንተ ሰካራሞች ከእንቅልፋችሁ ነቅታችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የወይን ጠጅ መጠጣት የምታዘወትሩ ምርር ብላችሁ አልቅሱ።
ሙሴም አሮንን “እግዚአብሔር ‘በፊቴ ቀርቦ የሚያገለግለኝ ሁሉ ቅድስናዬን ያክብር፤ እኔም በሕዝቤ ፊት የተከበርኩ እሆናለሁ’ እያለ በተናገረበት ጊዜ ይህንኑ ማስጠንቀቁ ነበር” አለው። አሮንም መልስ ሳይሰጥ ዝም አለ።
“በግብጽ ምድር የላክሁትን ዐይነት መቅሠፍት ላክሁባችሁ፤ ጐልማሶቻችሁ በሰይፍ እንዲሞቱ፥ ፈረሶቻችሁም እንዲማረኩ አደረግሁ፤ በሰፈራችሁ በሞቱ ሰዎች የበድን ግማት አፍንጫችሁን ሞላሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
ስለዚህ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በየመንገዱና በየአደባባዩ ዋይታና ለቅሶ ይሰማል፤ ገበሬዎች እንኳ ለለቅሶ ይጠራሉ፤ ከሙሾ አውጪዎችም ጋር ስለ ሞቱ ሰዎች ያለቅሳሉ፤
ከዝሆን ጥርስ በተሠሩ አልጋዎች ላይ ትተኛላችሁ፤ ከበግ መንጋ የጠቦት ሥጋ፥ ከከብት መንጋ የጥጃ ሥጋ እየበላችሁ በድንክ አልጋ ላይ ታርፋላችሁ!
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር “የእስራኤልን ሕዝብ ትዕቢት ጠልቼአለሁ፤ የተዋቡ ቤተ መንግሥቶቻቸውን ተጸይፌአለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ከተማይቱንና በእርስዋ የሚኖሩትን ሁሉ ለጠላት አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል።
የዓመት በዓል ደስታችሁን ወደ ሐዘን፥ ዘፈናችሁንም ወደ ለቅሶ እለውጠዋለሁ፤ አንድ ብቻ የሆነ ልጃቸው ሞቶባቸው እንደሚያለቅሱ ወላጆች ጠጒራችሁን ተላጭታችሁ ማቅ እንድትለብሱ አደርጋለሁ፤ የዚያ ቀን ፍጻሜ የመረረ ይሆናል።
ፈረሰኞች ወደፊት እየገፉ የሚያብረቀርቅ ሰይፋቸውንና የሚያብለጨልጭ ጦራቸውን ያነሣሉ፤ ብዙ ሰዎች ስለ ተገደሉ ሬሳዎች ተከምረዋል፤ ከሬሳውም ብዛት የተነሣ በዚያ የሚያልፍ ሰው ሁሉ ይደናቀፋል።
የእግዚአብሔር ፍርድ ቀን ስለ ቀረበ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመሥዋዕት እንደሚታረድ እንስሳ አሳልፎ ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው፤ ይሁዳን የሚበዘብዙ ጠላቶችንም ለይቶ አዘጋጅቶአል።