Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አሞጽ 6:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዝሆን ጥርስ በተሠሩ አልጋዎች ላይ ትተኛላችሁ፤ ከበግ መንጋ የጠቦት ሥጋ፥ ከከብት መንጋ የጥጃ ሥጋ እየበላችሁ በድንክ አልጋ ላይ ታርፋላችሁ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በዝኆን ጥርስ ባጌጠ ዐልጋ ላይ ለምትተኙ፤ በድንክ ዐልጋችሁ ላይ ለምትዝናኑ፣ ከበጎች መንጋ ጠቦትን፣ ከሠቡትም ጥጃን ለምትበሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከዝሆን ጥርስ በተሠራ አልጋ ላይ ለምትተኙ፥ በምንጣፋችሁም ላይ ተደላድላችሁ ለምትቀመጡ፥ ከበጎችም መንጋ ጠቦትን ከጋጥም ውስጥ ጥጃን ለምትበሉ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከዝ​ሆን ጥርስ በተ​ሠራ አልጋ ላይ ለሚ​ተኙ፥ በም​ን​ጣ​ፋ​ቸው ደስ ለሚ​ሰኙ፥ ከበ​ጎ​ችም መንጋ ጠቦ​ትን፥ ከጋ​ጥም ውስጥ ጥጃን ለሚ​መ​ገቡ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከዝሆን ጥርስ በተሠራ አልጋ ላይ ለምትተኙ፥ በምንጣፋችሁም ላይ ተደላድላችሁ ለምትቀመጡ፥ ከበጎችም መንጋ ጠቦትን ከጋጥም ውስጥ ጥጃን ለምትበሉ፥

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 6:4
18 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ምሳ ለመብላት ተቀመጡ፤ በሚመገቡበትም ጊዜ እስማኤላውያን ነጋዴዎችን በሩቅ አዩ፤ እነርሱም በግመሎቻቸው ቅመማ ቅመም፥ በለሳን፥ ከርቤም ጭነው ከገለዓድ ወደ ግብጽ የሚጓዙ ነበሩ።


የአትክልት ቦታውም ከነጭ ጥጥ በፍታ በተሠሩ ሰማያዊ ቀለም ባላቸው መጋረጃዎች የተጌጠ ነበር፤ መጋረጃዎቹም ከሐምራዊ በፍታ በተሠሩና የብር ቀለበት በተበጀላቸው ገመዶች በዕብነ በረድ ምሰሶዎች ላይ ተንጠልጥለው ነበር፤ ከወርቅና ከብር የተሠሩ ድንክ አልጋዎችም ነጭና ቀይ፥ ቢጫና ሰማያዊ ቀለማትን በሚፈነጥቅ የዕብነ በረድ ወለል ላይ ተደርድረው ነበረ።


አእምሮአቸው ክፉ ሐሳብን እያፈለቀ ከዐይነ ስባቸው የሚወጡት ዐይኖቻቸው አፍጥጠው ይመለከታሉ።


እናንተ ግን ጥሪውን በመቀበል ፈንታ በዓል አደረጋችሁ፤ የምትበሉትንም በግና በሬ ዐረዳችሁ፤ ወይን ጠጅም ጠጥታችሁ “ነገ እንሞታለን ዛሬ እንብላ እንጠጣ!” አላችሁ።


ከለምለሙ ሸለቆ በላይ ላለችው የሰማርያ ከተማ ወዮላት! መሪዎችዋ በመጠጥ የተሞሉ ሰካራሞች ናቸው ነገር ግን እነርሱ ደርቆ እንደሚረግፍ አበባ ይሆናሉ።


“ሰዎች ወደሚደሰቱበት ግብዣ ቤትም አትግባ፤ ለመብላትና ለመጠጣትም ከእነርሱ ጋር አትቀመጥ።


የእኅትሽ የሰዶም በደል ይህ ነው፤ እርስዋና መንደሮችዋ ኲራት ተሰምቶአቸው ነበር። የተትረፈረፈ ምግብና የተዝናና ኑሮ ቢኖራቸውም ችግረኞችንና ድኾችን አይረዱም ነበር።


በተዋቡም ድንክ አልጋዎች ላይ በፊት ለፊታቸው ተቀመጡ፤ እኔ የሰጠኋቸው ዕጣንና የወይራ ዘይት ሳይቀር ብዙ መልካም ነገሮችን በጠረጴዛ ላይ ደረደሩ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሰማርያ የሚኖሩ እስራኤላውያን ከአልጋና ከድንክ አልጋ ቊራጭ ጋር ያመልጣሉ፤ ይኸውም እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ ሁለት እግርና የጆሮ ቊራጭ ለማስጣል እንደሚችለው ዐይነት ነው።”


በቤተ መንግሥት የሚያሰሙት ዘፈን በዚያን ቀን ወደ ለቅሶ ይለወጣል፤ የብዙ ሰው ሬሳ በየቦታው ወድቆ ይገኛል፤ በዝምታም በየስፍራው ይጣላል።”


ሀብታሞቻችሁ በግፍ የተሞሉ ናቸው፤ የከተማይቱ ነዋሪዎችም ሐሰትን ይናገራሉ፤ በአንደበቶቻቸውም ይሸነግላሉ።


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ቀይ ከፋይና ቀጭን ልብስ የሚለብስ አንድ ሀብታም ሰው ነበር፤ እርሱም በየቀኑ በቅንጦት ይኖር ነበር።


በምቾትና በደስታ በመኖር ልባችሁን ለዕርድ እንደ ተዘጋጀ ከብት አወፍራችኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos