እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
አሞጽ 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በይሁዳ ምድር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ያቃጥላል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢየሩሳሌምን ምሽጎች እንዲበላ፣ በይሁዳ ላይ እሳት እሰድዳለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በይሁዳ ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በይሁዳ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ የኢየሩሳሌምንም መሠረቶች ትበላለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም አዳራሾች ትበላለች። |
እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
ነገር ግን ለእኔ መታዘዝና ሰንበትንም የተቀደሰ ቀን አድርገው ማክበር ይገባቸዋል፤ በዚህ ዕለት በኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው መግባት የለባቸውም፤ ትእዛዜን ባለመቀበል ይህን ቢያደርጉ ግን የኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች በእሳት እንዲጋዩ አደርጋለሁ፤ የኢየሩሳሌም ቤተ መንግሥቶችም በእሳት ይነዳሉ፤ እሳቱንም ሊያጠፋ የሚችል የለም።’ ”
ይህች ከተማ እንድትጠፋ ወስኛለሁ፤ ፈጽሞም ምሕረት አላደርግላትም፤ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
“የእስራኤል ሕዝብ ለራሳቸው ታላላቅ ቤተ መንግሥቶች ሠርተዋል፤ እኔን ፈጣሪአቸውን ግን ረስተዋል፤ የይሁዳም ሕዝብ ብዙ የተመሸጉ ከተሞችን ሠርተዋል፤ ስለዚህ ከተሞቻቸውንና ምሽጎቻቸውን የሚያቃጥል እሳት እልክባቸዋለሁ።”
የክረምቱንና የበጋውን ወራት የሚያሳልፉባቸውን ቤቶች ሁሉ እደመስሳለሁ፤ በዝሆን ጥርስ አጊጠው የተሠሩ ቤቶች ሁሉ ይፈርሳሉ፤ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ይወድማሉ።”
ጌታ እግዚአብሔር የገለጠልኝ ሌላውም ራእይ ይህ ነው፤ እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር የእሳት ቅጣት ፍርድ አስተላለፈ፤ እሳቱም ባሕሩን በልቶ ካደረቀው በኋላ ምድርን ማቃጠል ጀመረ።