Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አሞጽ 3:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህ ጠላት አገራቸውን ይከባል፤ ምሽጎቻቸውንም አፈራርሶ ቤቶቻቸውን ይዘርፋል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጠላት ምድሪቱን ይወርራል፤ ምሽጎቻችሁን ያፈርሳል፤ ድንኳኖቻችሁን ይዘርፋል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ምድሪቱን በዙርያዋ ጠላት ይከባታል፤ ምሽግሽንም ከአንቺ ያፈርሳል፥ የንጉሥ ቅጥሮችሽም ይበዘበዛሉ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እስከ ጢሮስ በአ​ለው ዙሪ​ያሽ ድረስ ምድ​ርሽ ይጠ​ፋል፥ ብር​ታ​ት​ሽ​ንም ከአ​ንቺ ያወ​ር​ዳል፤ ሀገ​ሮ​ች​ሽም ይበ​ዘ​በ​ዛሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በምድሪቱ ዙሪያ ጠላት ይመጣል፥ ብርታትሽንም ከአንቺ ያወርዳል፥ አዳራሾችሽንም ይበዘበዛሉ።

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 3:11
17 Referencias Cruzadas  

የቀሩትም የያዕቆብ ልጆች ወደሞቱት ሰዎች ቤት እየገቡ እኅታቸው የተደፈረችበትን ከተማ በሙሉ ዘረፉ።


የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር እስራኤልን ወረረ፤ ምናሔም በአገሩ መንግሥት ላይ ሥልጣኑን እንዲያጸናለትና እንዲደግፈው ለመማጠን ሠላሳ አራት ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር እጅ መንሻ አድርጎ ለቲግላት ፐሌሴር ሰጠው።


የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ዒዮን፥ አቤልቤትማዕካ፥ ያኖሐ፥ ቄዴሽና ሐጾር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች፥ እንዲሁም የገለዓድን፥ የገሊላንና የንፍታሌምን ግዛቶች በመውረር ሕዝቡን ወደ አሦር ማርኮ የወሰደውም ይኸው ፋቁሔ በነገሠበት ዘመን ነበር።


ቤተ መቅደሱንና የኢየሩሳሌምን ከተማ ከነቤተ መንግሥት ሕንጻዎችና ከነሀብትዋ አቃጠለ፤ የከተማይቱንም የቅጽር ግንብ አፈራረሰ፤


ሀብቱ ሁሉ ተሟጦ ስለሚያልቅ የሚቀምሰው ነገር አያገኝም።


ስለዚህ በይሁዳ ምድር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ያቃጥላል።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነዚህ ሕዝቦች መልካም ነገር ማድረግን አያውቁም፤ በዐመፅና በግፍ በተወሰደ ንብረት ምሽጋቸውን ይሞላሉ፤


የክረምቱንና የበጋውን ወራት የሚያሳልፉባቸውን ቤቶች ሁሉ እደመስሳለሁ፤ በዝሆን ጥርስ አጊጠው የተሠሩ ቤቶች ሁሉ ይፈርሳሉ፤ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ይወድማሉ።”


የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በእናንተ ላይ የሌላ ሕዝብ ኀይል አስነሣባችኋለሁ፤ እርሱም በሰሜን ከሐማት መግቢያ በር ጀምሮ በደቡብ እስከ አረባ ሸለቆ ድረስ ዘልቆ ያስጨንቃችኋል።”


የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር “የእስራኤልን ሕዝብ ትዕቢት ጠልቼአለሁ፤ የተዋቡ ቤተ መንግሥቶቻቸውን ተጸይፌአለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ከተማይቱንና በእርስዋ የሚኖሩትን ሁሉ ለጠላት አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos