ሐዋርያት ሥራ 9:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ጴጥሮስ ተነሥቶ ከመልእክተኞቹ ጋር መጣ፤ በደረሰም ጊዜ በሰገነቱ ላይ ወዳለው ክፍል ወሰዱት፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ሁሉ በዙሪያው ቆመው እያለቀሱ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር በሕይወት ሳለች የሠራቻቸውን ቀሚሶችና ልብሶች ያሳዩት ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጴጥሮስም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋራ ሄደ፤ እዚያ በደረሰ ጊዜም ሰገነት ላይ ወዳለው ክፍል አወጡት። መበለቶቹም ሁሉ ዶርቃ ከእነርሱ ጋራ በነበረችበት ጊዜ ያደረገቻቸውን ቀሚሶችና ልብሶች እያሳዩት ዙሪያውን ከብበው ያለቅሱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጴጥሮስም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር መጣ፤ በደረሰም ጊዜ በሰገነት አወጡት፤ መበለቶችም ሁሉ እያለቀሱ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር ሳለች ያደረገቻቸውን ቀሚሶችንና ልብሶችን ሁሉ እያሳዩት በፊቱ ቆሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጴጥሮስም ተነሥቶ አብሮአቸው ሄደ፤ በደረሰም ጊዜ ወደ ሰገነት አወጡት፤ ባልቴቶችም ሁሉ ወደ እርሱ መጥተው በፊቱ ቆሙ፤ ያለቅሱላትም ነበር፤ ዶርቃስም በሕይወት ሳለች የሠራችውን ቀሚሱንና መጐናጸፊያውን አሳዩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር መጣ፤ በደረሰም ጊዜ በሰገነት አወጡት መበለቶችም ሁሉ እያለቀሱ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር ሳለች ያደረገቻቸውን ቀሚሶችንና ልብሶችን ሁሉ እያሳዩት በፊቱ ቆሙ። |
ኢየሱስም “እናንተ የማታምኑ ጠማማ ትውልድ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጁን ወደ እኔ አምጡት!” አላቸው።
ኢየሱስም፥ “ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ለሙሴ በተሰጠው ሕግ፥ በነቢያትና በመዝሙር መጻሕፍት ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም አለበት ብዬ የነገርኳችሁ ቃል ይህ ነው” አላቸው።
እኔ አብሬአቸው በነበርኩ ጊዜ በሰጠኸኝ ስምህ ጠብቄአቸዋለሁ፤ እኔ ጠበቅኋቸው፤ ስለዚህ የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ከዚያ ከጥፋት ልጅ በቀር ከቶ ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።
ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ወደሚኖሩበት ሰገነት ላይ ወጡ፤ እነርሱም “ጴጥሮስ፥ ዮሐንስ፥ ያዕቆብ፥ እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ ቶማስ፥ በርተሎሜዎስ፥ ማቴዎስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ቀናተኛው ስምዖንና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ” ናቸው።
‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው’ የሚለውን የጌታ ኢየሱስን ቃል በማስታወስ፥ በእጃችን እየሠራን ደካሞችን መርዳት እንደሚገባን በብዙ መንገድ አሳይቻችኋለሁ።”
ከጥቂት ጊዜ በኋላ የአማኞች ቊጥር እየበዛ ሲሄድ የግሪክ ቋንቋ የሚናገሩ አይሁድ የይሁዳ አገር ተወላጆች በሆኑት አይሁድ ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ ያጒረመረሙትም በየቀኑ ይታደል በነበረው ርዳታ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች ችላ ይሉባቸው ስለ ነበር ነው።
በአምላካችንና በአባታችን ፊት እምነታችሁ የሚሠራውን፥ ለፍቅር የምታደርጉትንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ተስፋ በትዕግሥት መጠባበቃችሁን ሳናቋርጥ እናስታውሳለን።
በእርግጥ መበለት የሆነችና ብቻዋን የምትኖር፥ ተስፋዋን በእግዚአብሔር ላይ አድርጋ ሌሊትና ቀን የእግዚአብሔርን ርዳታ በመለመን በጸሎት ጸንታ ትኖራለች።