2 ጢሞቴዎስ 1:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተሰጠህን መልካም ዐደራ ጠብቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተሰጠህን መልካሙን ዐደራ በእኛ ውስጥ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ መልካሙን አደራ ጠብቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ። |
ይህም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም፤ እናንተ ግን፥ እርሱ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነና በውስጣችሁም ስላለ ታውቁታላችሁ።
ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ ቢኖር ኢየሱስ ክርስቶስን ከሞት ያስነሣው አምላክ በውስጣችሁ በሚኖረው መንፈሱ አማካይነት ለሟች ሥጋችሁ ሕይወትን ይሰጠዋል።
እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ የሚኖር ከሆነ በመንፈስ ፈቃድ እንጂ በሥጋ ፈቃድ አትኖሩም፤ የክርስቶስ መንፈስ የሌለውም ሰው የክርስቶስ ወገን አይደለም።
ሰውነታችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን ታውቁ የለምን? እንግዲህ እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ እንጂ የራሳችሁ አይደላችሁም።
የወንጌልን ቃል ያለ ግዴታ በፈቃዴ ባበሥር የድካም ዋጋ ይኖረኛል፤ በግዴታ ባደርገው ግን በዐደራ የተሰጠኝን ኀላፊነት ፈጸምኩ እንጂ ሌላ ያደረግኹት ነገር አለ ማለት አይደለም።
ከእንግዲህ ወዲህ እኛ ማንንም ሰው በሥጋዊ አመለካከት አንመለከትም፤ ከዚህ በፊት ክርስቶስንም የተመለከትነው እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋዊ አመለካከት ከሆነ ለወደፊቱ ግን ይህን አናደርግም።
እንዲያውም እግዚአብሔር ጴጥሮስን ለአይሁድ የምሥራቹን ቃል እንዲያበሥር በተላከው ዐይነት እኔንም የምሥራቹን ቃል ለአሕዛብ እንዳበሥር እንዳደረገኝ ተገነዘቡ፤
ኢዮስጦስ ተብሎም የሚጠራው ኢያሱ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው ከሚሠሩት ሰዎች መካከል የአይሁድ ወገኖች የሆኑት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል።
እውነተኛው ትምህርት ግን የሚገኘው ስለተመሰገነው እግዚአብሔር ከሚያበሥረው ክቡር ወንጌል ነው፤ ይህም ወንጌል ለእኔ በዐደራ የተሰጠኝ ነው።
ይህን መከራ የምቀበለውም በዚህ ምክንያት ነው፤ ነገር ግን ማንን እንዳመንኩ ስለማውቅ አላፍርበትም፤ የተሰጠኝንም ዐደራ እስከዚያ ቀን ድረስ መጠበቅ እንደምችል ተረድቼአለሁ።
ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።