Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 8:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ ቢኖር ኢየሱስ ክርስቶስን ከሞት ያስነሣው አምላክ በውስጣችሁ በሚኖረው መንፈሱ አማካይነት ለሟች ሥጋችሁ ሕይወትን ይሰጠዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የርሱ መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፣ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው፣ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈሱ ሟች ለሆነው ሰውነታችሁ ሕይወትን ይሰጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፥ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ፥ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈሱ አማካይነት፥ ለሟች አካላቶቻችሁ ሕይወትን ይሰጠዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው እርሱ አድ​ሮ​ባ​ችሁ ባለ መን​ፈሱ ለሟች ሰው​ነ​ታ​ችሁ ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 8:11
37 Referencias Cruzadas  

ጌታ ኢየሱስን ከሞት ያስነሣ አምላክ እኛንም ከኢየሱስ ጋር እንደሚያስነሣንና ከእናንተም ጋር በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን።


የኢየሱስ ሕይወት በሟች ሰውነታችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋኑ ስለ ኢየሱስ ሁልጊዜ ለሞት ተላልፈን እንሰጣለን።


እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ የሚኖር ከሆነ በመንፈስ ፈቃድ እንጂ በሥጋ ፈቃድ አትኖሩም፤ የክርስቶስ መንፈስ የሌለውም ሰው የክርስቶስ ወገን አይደለም።


እግዚአብሔር ጌታ ኢየሱስን ከሞት አስነሥቶታል፤ እኛንም በኀይሉ ከሞት ያስነሣል።


በኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኘውን ሕይወት የሚሰጥ የመንፈስ ቅዱስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶኛል።


እርሱ ይህን የተዋረደውን ሰውነታችንን በመለወጥ የእርሱን ክቡር ሰውነት እንዲመስል ያደርገዋል፤ ይህንንም የሚያደርገው ሁሉን በሥልጣኑ ሥር ለማድረግ በሚያስችለው ኀይል ነው።


አብ የሞቱትን እንደሚያስነሣና ሕይወትን እንደሚሰጣቸው፥ ወልድም እንዲሁ ለፈለገው ሰው ሕይወትን ይሰጠዋል።


እግዚአብሔር ግን የሞትን ኀይል አስወግዶ ከሞት አስነሣው፤ ስለዚህም ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለም።


በበደላችን የሞትን ብንሆንም እንኳ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር እንድንኖር አድርጎናል፤ እናንተም የዳናችሁት በጸጋው ነው።


እስትንፋሴን በእነርሱ ውስጥ አገባለሁ፤ በሕይወትም እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤ በገዛ ምድራቸውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይህን የተናገርኩና የማደርገውም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ነገር ግን ሦስት ቀን ተኩል ካለፈ በኋላ ሕይወት የሚሰጥ እስትንፋስ ከእግዚአብሔር መጥቶ ወደ ሬሳዎቹ ገባ፤ በእግራቸውም ቆሙ፤ ያዩአቸውም ሰዎች እጅግ ፈሩ።


ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።


ይህም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም፤ እናንተ ግን፥ እርሱ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነና በውስጣችሁም ስላለ ታውቁታላችሁ።


እኔም ሕያው ነኝ፤ ሞቼ ነበር፤ ነገር ግን እነሆ፥ ለዘለዓለም ሕያው ነኝ፤ በሞትና በሲኦል ላይ ሥልጣን አለኝ።


እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በኢየሱስ አማካይነት እርሱን ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ትተማመናላችሁ።


የሞቱት ሰዎች ከሞት ካልተነሡ ክርስቶስም ከሞት አልተነሣም ማለት ነው።


ሙታንህ ተነሥተው ሕያዋን ይሆናሉ፤ እናንተ በመቃብር ውስጥ የምትኖሩ፥ ተነሥታችሁ የደስታ መዝሙር ዘምሩ! አንጸባራቂው ጠል ምድርን እንደሚያድስ እግዚአብሔርም ከሞቱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን ተነሥተው በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል።


ስለዚህ ኃጢአት በሚሞተው ሰውነታችሁ ላይ ሥልጣን እንዲኖረውና ለሥጋ ምኞትም ተገዢ እንዲያደርጋችሁ አትፍቀዱለት።


ታላቁን የበጎች እረኛ ጌታችንን ኢየሱስን በዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ደም ከሞት ያስነሣው የሰላም አምላክ


በዚህ እንደ ምድራዊ ድንኳን በሆነው ሥጋችን ውስጥ ስንኖር ከብደን እንቃትታለን፤ የምንቃትተውም ሞት በሕይወት እንዲለወጥ ሰማያዊውን አካል በበለጠ እንድንለብስ ነው እንጂ ከዚህ ከምድራዊ ሥጋችን ለመለየት በመፈለግ አይደለም።


ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚኖሩ አሁን ኲነኔ የለባቸውም።


ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ! በሕይወታችን ግዴታ አለብን፤ ነገር ግን ይህ ግዴታ በሥጋ ፈቃድ ለመኖር አይደለም።


በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ተባባሪዎቼ ለሆኑት ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤


ከእኔ ጋር ታስረው ለነበሩና በሐዋርያትም መካከል ታዋቂዎች ለነበሩት አይሁድ ዘመዶቼ፥ ለአንድሮኒቆስና ለዩኒያስ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱ በክርስቶስ በማመን እኔን ይቀድሙኛል።


በክርስቶስ ሥራ ተባባሪያችን ለሆነው ለዑርባኖስና ለምወደውም ለእስጣኩስ ሰላምታ አቅርቡልኝ።


በክርስቶስ መሆኑ ተፈትኖ ለተመሰከረለት ለአጴሊስ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ ከአርስጦቡሎስ ቤተሰብ ለሆኑትም ሰላምታ አቅርቡልኝ፤


ሥጋውን ለማስደሰት የሚዘራ ከሥጋው ሞትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ከመንፈስ የዘለዓለም ሕይወትን ያጭዳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios