ንጉሡም አቢሳንና ወንድሙን ኢዮአብን “ይህ እናንተን አይመለከታችሁም፤ እግዚአብሔር አዞት ቢረግመኝ ‘ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?’ ብሎ ለመጠየቅ መብት የሚኖረው ማን ነው?” አላቸው።
2 ሳሙኤል 3:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም እንኳ እኔ እግዚአብሔር መርጦ የሾመኝ ንጉሥ ብሆን ዛሬ ደካማነት ተሰምቶኛል፤ እነዚህ የጸሩያ ልጆች በእኔ ላይ እጅግ የበረቱ ዐመፀኞች ሆነውብኛል፤ እነዚህን ነፍሰ ገዳዮች እግዚአብሔር ራሱ የሚገባቸውን ቅጣት ይስጣቸው!” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፣ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። እግዚአብሔር ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፥ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። ጌታ ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እርሱም በንጉሡ ዘንድ የተሾመ እንደ ሆነ አታውቁምን? እነዚህም ሰዎች የሦርህያ ልጆች በርትተውብኛል፤ እግዚአብሔርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ዛሬ ምንም ለመንገሥ የተቀባሁ ብሆን ደካማ ነኝ፥ እነዚህም ሰዎች የጽሩያም ልጆች በርትተውብኛል፥ እግዚአብሔር ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት አላቸው። |
ንጉሡም አቢሳንና ወንድሙን ኢዮአብን “ይህ እናንተን አይመለከታችሁም፤ እግዚአብሔር አዞት ቢረግመኝ ‘ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?’ ብሎ ለመጠየቅ መብት የሚኖረው ማን ነው?” አላቸው።
እንዲሁም ለዐማሳ ሲናገር “አንተም ለእኔ የሥጋ ዘመድ ነህ፤ ከአሁን ጀምሮ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ አደርግሃለሁ፤ ይህንንም ባላደርግ እግዚአብሔር በሞት ይቅጣኝ!” ብላችሁ ንገሩት ሲል አዘዛቸው።
ዳዊት ግን አቢሳንና ወንድሙን ኢዮአብን “ይህን አሳብ እንድታቀርቡ የጠየቃችሁ ማን ነው? ችግር ልታመጡብኝ ትፈልጋላችሁን? እነሆ፥ አሁን የእስራኤል ንጉሥ እኔ ነኝ፤ ደግሞም በዛሬው ዕለት ማንም እስራኤላዊ በሞት አይቀጣም” አላቸው።
አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ ስለ ገደላቸው ስለ እነዚያ ሰዎች ደም እግዚአብሔር ኢዮአብን ይቀጣዋል፤ ኢዮአብ ከእርሱ የተሻሉትን ሁለት ንጹሓን ሰዎች ገድሎአል፤ እነርሱም የእስራኤል ጦር አዛዥ አበኔርና የይሁዳ ጦር አዛዥ ዐማሣ ነበሩ።
አንተ ግን እርሱንም ከቅጣት ነጻ አታድርገው፤ ባለህ ጥበብ ምን መደረግ እንዳለበት አንተ ራስህ ታውቃለህ፤ በሞት የሚቀጣ መሆኑንም አትዘንጋ።”
ዳዊት “ልጄ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር የሚሠራው ቤተ መቅደስ እጅግ የተዋበና በዓለም ዝነኛ መሆን ይገባዋል፤ ነገር ግን እርሱ ገና ልጅና በዕውቀትም ያልበሰለ በመሆኑ፥ እኔ ሁሉን ነገር አዘጋጅለታለሁ” ሲል በልቡ አሰበ፤ ስለዚህም ዳዊት ከመሞቱ በፊት ብዙ የቤት መሥሪያ ዕቃዎችን አዘጋጀ።
ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ ሲል አስታወቀ፤ “እነሆ እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና የሥራ ልምድ የሌለው ነው፤ ይህ የሚሠራው ቤት፥ ቤተ መንግሥት ሳይሆን እግዚአብሔር አምላካችን የሚመለክበት ቤተ መቅደስ ስለ ሆነ መከናወን ያለበት ሥራ እጅግ ከባድ ነው።
ዘግየት ብሎም ኢዮርብዓም የማይረቡ ወሮበሎችን ሰበሰበ፤ እነርሱም በዕድሜው ማነስና በዕውቀት ያልበሰለ በመሆኑ ሊቋቋማቸው የማይችለውን የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምን በረቱበት።
ረጋ እንዲል፤ እንዳይፈራ፥ በእሳት ተቀጣጥሎ እንደሚነድ እንደ ግንድ ጢስ በሆኑት በሬዚንና በሶርያው በሬማልያ ልጅ ምክንያት እንዳይሸበር ንገረው።
ስለዚህ ዳንኤል ተይዞ መጥቶ ወደ አንበሶች ጒድጓድ እንዲጣል ንጉሡ አዘዘ፤ ዳንኤልንም “ሁልጊዜ በታማኝነት የምታገለግለው አምላክህ ያድንህ” አለው።
ቃላችሁን ባትጠብቁ ግን እግዚአብሔርን የምታሳዝኑ ሆናችሁ እንዳትገኙ አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ሰለ ኃጢአታችሁም ቅጣት የሚደርስባችሁ መሆኑንም አትዘንጉ።
ባለሥልጣን ለአንተ መልካም እንዲያደርግ የተሾመ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፤ ባለሥልጣን ሰይፍ የታጠቀው በከንቱ ስላልሆነ ክፉ አድራጊ ከሆንክ ባለሥልጣንን ፍራ፤ እርሱ ክፉ አድራጊዎችን በመቅጣትና የእግዚአብሔርን በቀል በማሳየት እግዚአብሔርን ያገለግላል።
እንዲሁም እግዚአብሔር የሴኬም ሰዎች ስለ ክፋታቸው ዋጋ የሆነውን መከራ እንዲቀበሉ አደረገ፤ በዚህ አኳኋን የጌዴዎን ልጅ ኢዮአታም በረገማቸው ጊዜ በእነርሱ ላይ እንደሚደርስባቸው የተናገረው ሁሉ ተፈጸመ።