Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 101:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በምድሪቱ የሚገኙትን ክፉዎች ሰዎች በየዕለቱ ጸጥ አሰኛለሁ፤ ከእግዚአብሔርም ከተማ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ አጠፋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በምድሪቱ ላይ ያሉትን ክፉዎች ሁሉ፣ በየማለዳው አጠፋቸዋለሁ፤ ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ፣ ከእግዚአብሔር ከተማ እደመስሳቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ዓመፃ የሚያደርጉትን ሁሉ ከጌታ ከተማ አጠፋቸው ዘንድ፥ የምድርን ክፉዎች ሁሉ በማለዳ አጠፋቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ጠላ​ቶቼ ሁል​ጊዜ ይሰ​ድ​ቡ​ኛል፥ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝም ተማ​ማ​ሉ​ብኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 101:8
16 Referencias Cruzadas  

እርሱ የክፉዎችን ኀይል ይሰብራል፤ የጻድቃን ኀይል ግን እየጨመረ ይሄዳል።


መንግሥት የሚጸናው በፍትሕ ስለ ሆነ ክፉ ሥራ በመሪዎች ዘንድ የተጠላ ነው።


በፍርድ ዙፋን ላይ የተቀመጠ ንጉሥ ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ አበጥሮ የሚያውቅ ዐይን አለው።


እግዚአብሔር ያደረገውን ሰምተናል፤ አሁንም ሁሉን ቻይ ጌታ የራሱ በሆነችው ከተማ ያደረገውን በዐይናችን አየን፤ እርሱ ከተማይቱን ለዘለዓለም ጸንታ እንድትኖር ያደርጋታል።


እናንተ ፍትሕን የምትጸየፉና ትክክለኛውን ነገር ሁሉ የምታጣምሙ የያዕቆብ ልጆች መሪዎች፥ የእስራኤል ሕዝብ አለቆች ይህን ስሙ፤


የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር አይኖሩም፤ ነገር ግን ተገደው ወደ ግብጽ ይመለሳሉ፤ ወደ አሦርም ሄደው በሥርዓት ንጹሕ ያልሆነ ምግብ ይበላሉ።


ብልኅ ንጉሥ ዐመፀኞችን ለይቶ ያውቃቸዋል፤ ያለ ምሕረትም ይቀጣቸዋል።


በሰሜን በኩል የምትገኘው፥ በከፍታዋና በውበትዋ የምትደነቀው፥ የጽዮን ተራራ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች፤ እርስዋም በምድር ላሉ ሁሉ ደስታን ታጐናጽፋለች።


ጅረቶችዋ የልዑል እግዚአብሔርን ቅዱስ ማደሪያ፥ የአምላክን ከተማ የሚያስደስቱ አንዲት ወንዝ አለች።


ጸያፍ የሆነ ነገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ርኲሰትን የሚያደርግና ውሸት የሚናገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ወደ እርስዋ የሚገቡ ስሞቻቸው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፉ ብቻ ናቸው።


አንተ እንደ ጐሽ ቀንድ ከፍ አደረግኸኝ፤ በትኲስ ዘይትም ቀባኸኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios