5 ከንጉሥ ፊት ክፉ ሰዎችን አስወግድ፤ መንግሥቱም በፍትሕ ጸንታ ትኖራለች።
5 ክፉን ከንጉሥ ፊት አርቅ፤ ዙፋኑም በጽድቅ ትጸናለች።
5 ከንጉሥ ፊት ክፉ ሰዎችን አርቅ፥ ዙፋኑም በጽድቅ ትጸናለች።
ኢዮአብ እነዚህን ሰዎች በመግደሉ በእርሱ ላይ የተፈጸመበት ቅጣት በእርሱና በዘሮቹ ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር፤ በዙፋኑ ላይ ለሚቀመጡት ለዳዊት ዘሮች ግን የእግዚአብሔር ሰላም ለዘለዓለም አይለያቸው።”
እኔን ግን እግዚአብሔር ይባርከኛል፤ የዳዊት መንግሥትም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።”
ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ሺምዒን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ ሺምዒን ገደለው፤ በዚህም ዐይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ።
ስለዚህም ሃማን መርዶክዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው እንጨት ላይ ተሰቀለ፤ ከዚያም በኋላ የንጉሡ ቊጣ በረደ።
መንግሥት የሚጸናው በፍትሕ ስለ ሆነ ክፉ ሥራ በመሪዎች ዘንድ የተጠላ ነው።
ቸርነትና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ መንግሥቱም በእውነተኛነት ላይ ጸንቶ ይኖራል።
በፍርድ ዙፋን ላይ የተቀመጠ ንጉሥ ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ አበጥሮ የሚያውቅ ዐይን አለው።
በንጉሥ ፊት በምትቆምበት ጊዜ ዝነኛ ለመሆን አትሞክር፤ ወደ ታላላቅ ሰዎችም ደረጃ ከፍ ለማለት አትፈልግ።
አንድ ንጉሥ ለድኾች በቅን የሚፈርድ ከሆነ ለረዥም ዘመን ያስተዳድራል።
በዚያን ጊዜ አንድ መንግሥት በዘለዓለማዊ ፍቅር ይመሠረታል፤ በዙፋኑም ላይ ከዳዊት ዘር አንድ ታማኝ የሆነ፥ ፍትሕን የሚፈልግና ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ፈጣን የሆነ ንጉሥ ይቀመጥበታል።
ለንጉሣዊ ሥልጣኑ ወሰን የለውም፤ መንግሥቱም ዘለዓለማዊ ሰላም የሰፈነበት ይሆናል፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፥ እውነትና ፍትሕ የሰፈነበት መንግሥት በዳዊት ዙፋን ላይ ተመሥርቶ እንዲጸና ያደርገዋል፤ የሠራዊት አምላክ ቅናት ይህን ለማድረግ ወስኖአል።